ኮቪዲ 19 ወይም የኮሮና ቫይረስ በቻይና በሁዋን ግዛት መቀስቀሱ ከታወቀ ካለፉት አራት ወራት ወዲህ የመዛመት ፍጥነቱን ጨምሮ በ206 ሀገራት በመንሰራፋት 1ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን አጥቅቷል፡፡ የ50ሺ የሚበልጡ ሰዎችን ህይወት ነጥቋል፡፡ በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገራት በሽታ ተስፋፍቶ 6ሺ የሚጠጉ የአህጉሪቱን ነዋሪዎች በማጥቃት 225 የሚጠጉትን ለህልፈተ ህይወት ዳርጓል፡፡ በሀገራችንም የቫይረሱ ስርጭት እለት ተእለት እየጨመረ መጥቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት ለኮሮና ወረርሽኝ ምንም አይነት መድኃኒትም ሆነ ክትባት ያልተገኘለት በመሆኑ አዘውትሮ የግል ንጽህና መጠበቅ፤አካላዊና ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅና ከቤት አለመውጣት ዋነኛ የመከላከያ ዘዴዎች መሆናቸውን በተደጋጋሚ የህክምና ባለሙያዎች ሲገልጹ እየተሰሙ ነው፡፡ይሁን እንጂ እነዚህን የመከላከያ መንገዶች በአግባቡ ተገንዝቦ መተግበር ላይ ክፍተቶች እንዳሉ የህክምና ባለሙያዎችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በተደጋጋሚ ሲገልጹ እየተሰሙ ነው፡፡
መንግሥት የቫይረሱን ሥርጭት ለመከላከል ይረዳሉ በሚል ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ማኅበረሰቡ በበቂ ሁኔታ እየተገበራቸው አይደሉም ፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሰሞኑን እንደተናገሩት ፣ መደረግ ላለባቸው ጥንቃቄዎች ልዩ ትኩረት መስጠት ካልተቻለ፣ በሁለት አኃዝ ያለው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ቀስ በቀስ ወደ ሦስትና አራት አኃዞች ሊያድግ እንደሚችል ስጋታቸውን አስቀምጠዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ችግሩ ጎልቶ በሚታይባቸው የሀይማኖት ስፍራዎች ያለውን እውነታ ለመለወጥ መንግስት ከሀይማኖት መሪዎች ጋር ያደረጋቸው ውይይቶች ፍሬ አፍርተው ተቋማቱ ወረርሽኙን መከላከል የሚያስችሉ ውሳኔዎች ላይ መድረሳቸውና ይህንንም ለምእመኖቻቸው ማሳወቃቸው የሚያበረታታ ነው ፡፡
በተቋማቱ የተወሰዱት ውሳኔዎች በሽታውን በመከላከል ሂደት ውስጥ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ መተኪያ የሌለው ቢሆንም ውሳኔዎቻቸው ግን አሁንም ሙሉ በሙሉ እየተተገበሩ አይደለም ፡፡ ምእመኑ አሁንም ስለበሽታው ያለው ግንዛቤ የአደጋ ተጋላጭነቱን የሚጨምርና ሀገራዊ የመከላከል ስራውን የሚገዳደር እንደሆነ በአግባቡ ያስተዋለው አይመስልም ፡፡
ይህንን እውነታ ለመቀልበስ የእምነት ተቋማቱ የደረሱባቸውን ውሳኔዎች ተግባራዊ ሊያደርጉ የሚችሉ ጠንከር ያሉ የዲሲፕሊን እርምጃዎች መውሰድ ይጠበቅባቸዋል ፡፡ ካለባቸው የምእመኖቻቸውን ህይወት ከአደጋ የመጠበቅ ኃላፊነት አንጻር ውሳኔዎቻቸው የእምነት ተቋማቱን እስከመዝጋት የሚደርስ ሊሆን ይገባል ፡፡
የወረርሽኙ ስጋት በተመሳሳይ መልኩ በገበያ ሥፍራዎችና በትራንስፖርት አገልግሎቶች በስፋት እየተስተዋለ ነው ። ይህንን ችግርና ማኅበራዊ መዘናጋት ለማረም በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ ግንዛቤ ለማስጨበጥና ማኅበረሰቡን ለማንቃት በጎዳናዎች ላይ ጭምር በመዘዋወር መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ጥረት ቢደረግም፣ የታየው ውጤት ግን አነስተኛ እንደሆነ ተገምግሟል፡፡
እስካሁን ባለው የቫይረሱ ሥርጭት ከአዲስ አበባ ውጪ በኦሮሚያ (አዳማ) እና በአማራ ክልል (በባህር ዳር) መገኘቱን የመንግሥት መረጃ ያመለክታል።ይህን ሁኔታ ከወዲሁ መቆጣጠር ካልተቻለ የቫይረሱ ስርጭት ወደ አርሶ አደሩ ገብቶ የከፋ ጉዳት ማስከተሉ ስለማይቀር ከወዲሁ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል፡፡በዋነኝነት ግን ሁላችንም የኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ሞትና ተያያዥ ጉዳቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት ከቤት ባለመውጣት ፤ የግል ንጽህናንና ማህበራዊ ዕርቀትን በመጠበቅ ቫይረሱ የከፋ ጉዳት ሳይስከትል ልንቆጣጠረው ይገባል፡፡
አዲስ ዘመን መጋቢት 26/2012
በመዘናጋት ለከፋ ጉዳት እንዳንዳረግ