ለዛሬው ይጠይቁልኝ አምድ በኢሜል አድራሻችን ከደረሰን ጥያቄ ውስጥ አንዱን አስተናግደናል:: ጥያቄው “ለመሆኑ በዓለም ላይ እንደአሁኑ ለአለም ህዝብ ስጋት የነበረ በሽታ ተከስቶ ያውቃል? መቼ?” የሚል ነው:: እኛም የተለያዩ ድረ ገፆችና መጽሐፎችን በማገላበጥ ያገኘነውን መረጃ እንደሚከተለው ይዘን ቀርበናል::
ዓለም በተለያዩ ወቅቶች በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ችግሮች ስትጠቃ መኖሯን የኋላ ታሪኮቻችን ያስታውሱናል:: ከሰው ሰራሽ ችግሮች ውስጥም ጦርነት ቀዳሚው ነው:: በዚህ ደግሞ አንደኛውና ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ትልቅ ምሳሌዎች ናቸው::
በሌላ በኩል በተፈጥሮ አደጋዎችም የበርካታ ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል:: ከነዚህ የሰውን ልጅ ህይወት ከቀጠፉ የተፈጥሮ አደጋዎች ውስጥም ግንባር ቀደሞቹ የበሽታ ወረርሽኞችና በየአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈጠሩ የተፈጥሮ አደጋዎች ሊጠቀሱ ይችላሉ::
ከዚህ ቀደም በዚህ ደረጃ በዓለም ላይ ከተከሰቱ ወረርሽኞች ውስጥ አንዱ “ስፓንሽ ፍሉ” በአገራችን ደግሞ የህዳር በሽታ እየተባለ የሚጠራው ወረርሽኝ አንዱ ነው:: በ1918 ዓ.ም የተከሰተው ይህ ወረርሽኝ በአለማችን 200 ሚሊየን የሚደርሱ ዜጎችን ህይወት መቅጠፉን መረጃዎች ያሳያሉ:: በወቅቱ የዓለማችን ሩብ ህዝብም በዚህ ቫይረስ ተይዞ እንደነበር መረጃዎቹ ይጠቁማሉ::
በወቅቱ እ.ኤ.አ ከ1914 ዓ.ም እስከ 1918 ድረስ የዘለቀውና የ15 ሚሊዮን ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የአንደኛው ጦርነት ማብቃት ሊታወጅ ጥቂት ሲቀረው የዓለም ህዝብ ሌላ ፍዳ ማስተናገድ ግድ ሆነበት፤ በሰው ሰራሽ ችግሮች (በዋነኝነት በጦርነት) ተወጥሮ የቆየው መላው የአለም ህዝብ በኢንፍሉዌንዛ በሽታ ከዳር እስከ ዳር ተጠቃ::
ወረርሽኙ እአአ በጥር ወር 1918 ዓ.ም በአንደኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ዋዜማ፣ በጦርነቱ ለመካፈል የአሜሪካ ወታደሮች ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ዝግጅት በሚያደርጉበት በካንሳስ በሚገኘው ፉንስተን የወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል፣ በሶስት ቀናት ብቻ 45 ሺህ የሚሆኑ ወታደሮችን አጠቃ፤ ወታደሮቹ አትላንቲክን አቋርጠው አውሮፓን እንደረገጡ በሽታውም አውሮፓ ደረሰ:: በሽታው በአውሮፓ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በፈረንሳይ ቢሆንም በጦርነቱ ምክንያት ለፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ ይሆናል በሚል ወረርሽኙ ለህዝብ ሳይገለጽ ተደብቆ ቆየ::
በሽታው ይፋ የሆነው እ.ኤ.አ በህዳር ወር 1918 ዓ.ም በስፔን መታየቱን ተከትሎ ነበር:: ስፔን በጦርነቱ ተካፋይ ባለመሆኗ በአገሪቱ የጦርነት ጊዜ ሳንሱር አልነበረም፤ በመሆኑም የበሽታው መስፋፋት ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን በማግኘቱ ወረርሽኙ እስፓኒሽ እንፍሉዌንዛ (ስፓኒሽ ፍሉ) የሚለውን ስያሜ አገኘ::
የበሽታው ምልክቶች ሳል፣ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ነስር፣ የጆሮና የአንጀት መድማት፣ ተቅማጥ፣ የአይን ማስለቀስና ውጋት ሲሆኑ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስም የአእምሮ ህመም ያስከትላል:: በሽታው ከኮሌራ ወይም ከፈንጣጣ በሽታዎች ጋር ተቀራራቢ ምልክቶችን ስለሚያሳይ ብዙ ያምታታ ነበር:: የበሽታው አማጪ ቫይረስ ባለመታወቁ መድሃኒትም ሆነ ማስታገሻ እንዳይገኝ አድርጎት ነበር::
በበሽታው ከተያዙት ውስጥ ከ10 እስከ 20 በመቶ የሚሆኑት ለሞት ተዳርገዋል:: የወረርሽኙን ጉዳት የከፋ ያደረገው አምራች ዜጎችን በከፍተኛ ሁኔታ በማጥቃቱ ነበር:: በበሽታው ከሞቱት መካከል ዕድሜያቸው ከ25 እስከ 34 ዓመት የሆኑ ወጣቶች አብዛኛውን ድርሻ ይወስዳሉ፤ በመሆኑም በሽታው ካደረሰው ሰብዓዊ ውድመት ባለፈ ጥሎት ያለፈው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠባሳ የከፋ ነበር::
በኢትዮጵያም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል:: በሽታው በአገራችን በተለይ በህዳር 12 ከፍተኛ ሞት በማስከተሉም ህዝቡ የህዳር በሽታ እያለ ይጠራዋል::
አዲስ ዘመን መጋቢት 25/2012
የህዳር በሽታ