የዛሬ ሁለት ዓመት የሀገራችን ተጨባጭ እውነታ ለሰሚ የማይጥም ፤ ለወሬ የማይመች ፤ በቀጣይ ቀን ምን ሊሆን እንደሚችል በሙሉ አፍ ለመናገር የሚያስደፍር አልነበረም። ሀገር እንደ ሀገር መንታ መንገድ ላይ ቆማ ለዜጎች የተስፋ ጭላንጭል በማይታይበት ሁኔታ ህዝቦች በብዙ ስጋት እና ጭንቀት ውስጥ የነበሩበት ጊዜ ነበር።
በሀገሪቱ የነበረውን የፖለቲካ ሥርዓት በመቃወም በየቦታው የአመጽ እንቅስቃሴዎች የበዙበት፤ ዜጎች ለተሻለ የፖለቲካ ሥርዓት በየአደባባዩ የህይወት መስዋእት የሚከፍሉበት ፤ የለውጥ ፈላጊነት መንፈስ ከዳር እስከዳር ሀገሪቱን ያጥለቀለቀበት ፤ ይዘነው ከመጣናቸው የፖለቲካ አስተሳሰቦች አንጻር የለውጥ ፈላጊነት ስሜቱን በአግባቡ ሊመራ የሚችል ኃይል ከሌለ የሀገሪቱ እጣ ፋንታ የከፋ እንደሚሆን በሰፊው ይነገርበት የነበረበት ወቅት ነው።
በአንድ በኩል ለውጥ ፈላጊውና ትዕግስቱ የተሟጠጠው የህዝብ ኃይል በሌላ በኩል ይህን ለውጥ ፈላጊ ኃይል በኃይል ለመቀልበስ የተቻለውን ሁሉ እያደረገና ሥርዓቱን ለማስቀጠል የሚተጋው ሌላው ኃይል የመጨረሻው መስመር ላይ የተሰለፉበት ፤ በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው የለውጥ ኃይልም የውስጥ ትግሉን ወደ ግልጽ የአደባባይ ትግል የለወጠበት ወቅት ነበር።
የለውጥ ኃይሉ ትግሉን በአሸናፊነት መወጣቱን ያበሰረው የመጋቢት 17/2012 ዓ/ም የሌሊት አምስት ሰዓት ዜና ስጋት ፣ ጭንቀትና ሟርቱን በመቀልበስ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ አዲስ የተስፋ ምእራፍ መክፈት የቻለ ነበር። የመጨረሻው መጀመሪያ በመሆን በሀገሪቱ ሰፍኖ የነበረውን የመበታተን ሰጋት በመግፈፍ ሀገር እንደ ሀገር የምትቀጥልበትና ታላቅ ተሰፋ አብስሯል።
የለውጥ ኃይሉ ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ የማይታሰቡ የሚመስሉ የፖለቲካ ውሳኔዎች በየዕለቱ መሰማት የተለመደ ሆነ ። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያልተለመደና ሊሆን ይችላል ተብሎ የማይታሰበው የይቅርታ ፖለቲካ ከሀገር አልፎ መላውን ዓለም አስገርሟል። በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ሰፊ ስፍራ የነበረው የጠላትነት ፣ የመገዳደልና የመጠፋፋት የፖለቲካ አስተሳሰብ እንዲያበቃ ወደ አዲስ የፖለቲካ ሥርዓት የመሸጋገሪያ ድልድይ ሆኗል ።አስተሳሰቡ ያልተለመደ በመሆኑ አንዳንዶች የይቅርታውን መንገድ በማንቋሸሽ ብዙ እርምጃ አያራምድም ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ ይህ ዓይነቱ የፖለቲካ አስተሳሰብ ለሀገራችን የሚጠቅም አይደለም ፤ ይህ የመንግሥት አቅም ቢስነት መገለጫ ከመሆን ያለፈ አይደለም ሲሉም አዲሱን የፖለቲካ መንገድ ሲያብጠለጥሉ ተስተውሏል ።
ከዚህ እውነታ በመነሳትም መንግሥትን እንፈትነው በሚል ሀገርንና ህዝብን አደጋ ውስጥ ሊጨምሩ የሚችሉ በርካታ ሙከራዎች ተደርገዋል። የህዝቡን የለውጥ ፈላጊነት መንፈስ በመቀልበስ ህዝቡ ራሱ የለውጡ ስጋት እንዲሆንም ተሰርቷል። በግልጽና በስውር በመንቀሳቀስ የለውጥ ኃይሉን ለማዳከም ብዙ ተሞክሯል ።
በእነዚህ ሁለት ዓመታት የአገር ታላላቅ ባለውለታዎች በአደባባይ በጭካኔ ተገድለዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች ዜጎች ወጥተው መመለስ በማይችሉበት ሁኔታ በፍርሀትና በሞት ጭንቀት ተውጠው ቀናትን ለማሳለፍ ተገደዋል። አንዳንዶች ስለ « ነጻነት» እንታገላለን በሚሉ ኃይሎች በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ብቻ ታድነው ተገድለዋል። ይሁንና የለውጥ ኃይሉ በየወቅቱ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በልበ ሰፊነት፣ በትእግስትና አርቆ አሳቢነት ወደ መልካም አጋጣሚዎች በመለወጥ በህዝቡ ውስጥ የተፈጠረውን ተስፋ ከተስፋ በላይ እንዲሆን አድርጓል።
በሙስና በመልካም አስተዳደርና በተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ አደጋ ውስጥ የነበረውን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በመታደግ የዜጎችን ህይወት በተጨባጭ የለውጥ ተግባራትን አከናውኗል። የለውጥ ሀይሉ እና መላው ህዝባችን በሁለት ዓመታት የማይታሰቡ ተግዳሮቶች አሸንፈው በመውጣት ሊታሰቡ የማይችሉ ስኬቶችን አስመዝግቧል። ዛሬ ደግሞ የኮሮና ቫይረስ ተጨማሪ ተግዳሮት ሆኖ ከፊታችን ቆሟል። ይህም ተስፋ ያደረግነውን የብልጽግና ህይወት እስክንጨብጥ ገና ብዙ ተግዳሮቶች እንደሚጠብቁን ያሳያልና ከተግዳሮቶቻችን በላይ መሆን የሚያስችል ዝግጁነት በመፍጠር የለውጡን ፍሬ በአንድነት ለመቋደስ በበለጠ ትጋት መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 25/2012
አሁንም ተግዳሮቶችን አልፈን የለውጡን ፍሬ በጋራ እንቋደሳለን!