የመንገድ ግንባታ ለማካሄድ ወደ ስራ ሲገባ ከሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች አንዱ የወሰን ማስከበር ነው::ወሰን በወቅቱ ተከብሮ ተቋራጮች ወደ ግንባታ ካልገቡ የመንገድ ልማቱን ያጓትታል፤ይህ በመሆኑም ልማቱን ሲጠይቁ የኖሩ ወገኖች ምላሽ ይዘገያል::መንግስትም ለተጨማሪ ወጪ ይዳርጋል::
ወሰን ማስከበር ላይ እክል የሚጀምረው ከካሳ ተመን አዘገጃጀት ነው ሲሉ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የመንገድ ወሰን ማስከበር ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጄ አየለ ይገልጻሉ:: ባለስልጣኑ በሁሉም ክልሎችና ወረዳዎች መንገድ በሚሰራበት ወቅት በመንገዱ ክልል ውስጥ ለሰፈሩ ንብረቶች ፣ለግለሰቦችም ሆነ ለተቋማት ካሳ ከፍሎ ማስነሳት እንደሚጠበቅበት ያመለክታሉ::
ካሳ ለመክፈል በቅድሚያ ኮሚቴ እንደሚቋቋም ጠቅሰው፣ዋነኛው ችግር የሚመነጨው ከዚህ ነው ይላሉ::‹‹ኮሚቴው ሲቋቋም ከየትኛው የሥራ ክፍል መውጣት እንዳለበት ይታወቃል:: ኮሚቴውን የሚያዘጋጁት የወረዳ አስተዳደሮች እና ለከተማ መንገድ የከተማ የከንቲባ ፅህፈት ቤቶች ተገቢው የሞያ ስብጥር ያላቸውን አባላት መምረጥ አለባቸው››የሚሉት ዳይሬክተሩ ፣ለሥራው የሚመጥኑ በቂ ክህሎት ያላቸው ሰዎችን ከየቦታው አለመምረጥ በአንዳንዶች ላይ እንደሚስተዋል ያመለክታሉ::
‹‹የሰዎች ንብረት ሲነሳ የብዙዎች ስሜት ይነካል፤ አንዳንዶች ከአካባቢያቸው ይፈናቀላሉ:: ሥራው ጊዜ የማይሰጥ በጣም ሰፊና ውስብስብ ነው::››ያሉት ዳይሬክተሩ፣ በደንብ አስተካክሎ በተገቢው ፍጥነት እና ጥራት መስራት ካልተቻለ ህብረተሰቡ ላይ ቅሬታ እንደሚፈጠር ይናገራሉ::የሚመደቡት ሰዎች ይህንን ተረድተው መደበኛ ሥራ አድርገው በቋሚነት የሚሰሩ አለመሆናቸው በሁሉም ክልሎች የታየ አሳሳቢ ችግር ነው ይላሉ::
እንደ አቶ ደረጄ ገለፃ፤ የመንገዱን ጥቅም በመንገር ህብረተሰቡን ለማሳመን የሚችሉ፤ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደሮች ተገቢው ካሳ እንደሚከፈል ለማሳወቅ የማይቸገሩ እና ከህብረተሰቡ ጋር የሚግባቡ የኮሚቴ አባላት መመረጥ ቢኖርባቸውም፣ የሚፈፀመው በተቃራኒው ነው:: እንደውም በየአካባቢው ኮሚቴዎች ላይ ተፅዕኖ ይፈጥራል::
ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ለሥራው በቂ ትኩረት አይሰጡም:: ኮሚቴዎች ላይ ተጨማሪ ሥራዎች ይጫንባቸዋል:: ተመን ካልተሰራ ግምት ካልታወቀ ካሳ መክፈል እንደማይቻል፤ ካሳ ካልተከፈለ እና ንብረት ካልተነሳ መንገዱ እንደማይሰራ አያስተውሉም፤ ስለዚህ ንብረት ገምቶ ሰነድ አዘጋጅቶ በፍጥነት መላክ ላይ አብዛኞቹ ኮሚቴዎች ላይ ሰፊ ችግር ይታያል::
ተጨባጭ ያልሆነ ተመን
በካሳ ክፍያ ላይ ተጨባጭ ያልሆነ የዋጋ ተመን ይጠየቃል::በአዲስ አበባ እንኳን በሌለ ዋጋ ክልል ላይ ለካሬ ሜትር ከፍተኛ መጠን ያለው የካሳ ገንዘብ ይጠየቃል::በዓለም ታይቶ የማይታወቅ ምርት እንደሚገኝ ተደርጎ ተመን ይወጣል:: ተግባሩ ለተነሺው በማሰብ ሳይሆን ከጀርባው ሌላ ተልዕኮ ያለ ይመስላል:: ከአዋጅ፣ ከመመሪያ እና ከአሰራር ውጪ እንደተፈለገ ዋጋ መተመን እና ነገሩን መጠምዘዝ በጥቂት ሰው የሚፈፀም አይደለም:: ደላሎች እና ህብረተሰቡም የሚሳተፍበት በመሆኑ ጉዳዩ ውስብስብ ነው::
መሬት ውስጥ የተቀበረ በቀላሉ የማይታይ የውሃ ቱቦን ለመሳሰሉ ንብረቶች ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ካሳ ይጠይቃሉ ::ተመኑ እንደ ግለሰቦች ሁሉ እጅግ በጣም የተጋነነ መሆኑን ነው ያመለከቱት:: ጥያቄው ተጨማሪ ገንዘብ አግኝቶ ወረዳውን አሊያም ከተማውን ለመልማት ካለ ፍላጎት የተነሳ ሊሆን እንደሚችል ተናግረው፣ ባለስልጣኑ የሚተዳደረው በበጀት መሆኑ ሊታወቅ እንደሚገባ ያመለክታሉ::‹‹ እጅግ የተጋነነ ዋጋ መክፈል አይችልም፤ለምን የተጋነነ ዋጋ ይቀርባል›› የሚል ጥያቄ ሲያቀርብ ወረዳዎች ‹ለምን ጥያቄ ተነሳ› ብለው ጭራሽ ባለስልጣኑን ያስጨንቃሉ›› ይላሉ::
እንደ እሳቸው ማብራሪያ፤ህብረተሰቡን የማሳመን ትክክለኛ ፍትሃዊ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲከፈል ተባባሪ መሆን ከወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮቹ
ይጠበቃል::አስተዳደሮቹ የተሰጣቸውን የካሳ ግምት የማስቀመጥ ስልጣን ያለአግባብ ሲጠቀሙ ባለስልጣኑ የመከላከል ኃላፊነት ስላለበት ጥረት እያደረገ ነው:: ተቋሙ ህብረተሰቡ እየተበደለ መንገድ ይሰራ የሚል አቋም ፈፅሞ የለውም:: ለዚህም ተገቢውን በጀት ይዞ ይንቀሳቀሳል::ተገቢ ያልሆነ ካሳ እንዳይሰጥ የማድረግ ኃላፊነት ደግሞ አለበት:: ያም ቢሆን የተመን ጉዳይ ከወረዳ እና ከከተማ አስተዳደር ካልወጣ በጣም አስቸጋሪ ነው:: የብዙ ሰው እጅ ያለበት እና ፈታኝ ነው::
ቀደም ሲል በሚገነባው የመንገድ ክልል ውስጥ ያልገባ ንብረት ሳይቀር የሚገመትበት ሁኔታ ነበር:: መንገዱ ስንት ካሬ ሜትር ቦታ ይሸፈናል? መንገዱ ሥር የተካተተው የትኛው ቤት ነው? የሚለው በተለያየ መልኩ የሚጣራበትና የተለያዩ አካላትን ተጠያቂ የሚያደርግበት አሰራር ተዘርግቷል:: ስለዚህ የንብረቱን ቁጥር በሚመለከት መጨመር መቀነስ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል::
ከ12 ዓመት በፊት የካሳ ክፍያ እንዳልነበረ ዳይሬክተሩ ያስታውሳሉ:: ‹‹በወቅቱ ስለካሳ ክፍያ አይታሰብም ነበር:: የካሳ ክፍያ አዋጁ 455/97 ከወጣ በኋላ ብዙዎች ጨመር ያለ ካሳ እንደሚያገኙ ሲያውቁ፤ ፍላጎቶች እያደጉ መጥተዋል:: ማፍረሻ ወጪው ከመገንቢያው የተሻለ መሆኑን ስለሚያውቁ ‹‹የተሻለ ግንዛቤ አለኝ የሚለው ሰው›› ይዞታው መንገድ እንደሚወጣበት ሲያውቅ እዛ ሄዶ ይሰፍራል:: አሁን ይህ ጉዳይ ፈታኝ ደረጃ ላይ ደርሷል‹‹ሲሉ ያብራራሉ::
የባለስልጣኑ ክፍተት
ባለስልጣኑ ንብረት ካነሳ በኋላ ለተቋራጮች ፕሮጀክቶችን መስጠት ነበረበት፤ በፊት ያ አሰራር አልነበረም:: አሁን መጀመሪያ ዲዛይን ይዘጋጃል፤ ያንን ተከትሎ ንብረት ለቀማ እና የማንሳት ሥራ ይሰራል:: የሥራ ተቋራጩ ሲገባ ብዙ ችግር ተቀርፈውለት ንብረት ተነስቶ ነፃ መሬት አግኝቶ እንዲሰማራ በተወሰኑ ፕሮጀክቶች ላይ እየተሞከረ ነው:: ቢያንስ ወሳኝ የተባሉትን ንብረቶች በማንሳት ለስራ ተቋራጩ ለማቅረብ ታቅዷል::
የህብረተሰቡ ግንዛቤ
ህብረተሰቡ የመንገድ ጥቅምን አስመልክቶ ግንዛቤ የለውም እንዳይባል ከክልልና ከዞን እንዲሁም ከየወረዳው አስተዳደሮች ‹‹መንገድ ይሰራልን›› የሚሉ የሃይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች የባለስልጣኑን ቢሮ ሲያጣብቡ ይውላሉ በማለት የሚናገሩት ዳይሬክተሩ፤ በቀጥታ ወደ መንገድ ሥራው ሲገባ ግን ችግር እንደሚያጋጥም ይጠቅሳሉ:: ‹‹መንገድ ይሰራልን የሚለው ህብረተሰብ ዞሮ የመንገድ ሥራው እንቅፋት ይሆናል:: ሁሉም ያለአግባብ መጠቀም ይፈልጋል:: በመንገዱ ልማት ለመጠቀም ሳይሆን ከጎን የሚገኘውን ጥቅም ታሳቢ መደረጉ ትልቅ ችግር እየፈጠረ ነው›› ይላሉ::
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ህብረተሰቡ ትብብር እያደረገ አይደለም:: ከመንገድ ሥራው ጥቅም ይልቅ ካሳ ላይ ትኩረት ተደርጓል:: አሁን ባለው ሁኔታ መንገድ የሚሰራበት እና የሚሰፋበት ቦታ ላይ በዘመቻ ቤት እየተሰራ እና ንብረት እየሰፈረ ነው፤ይህ ትልቅ ፈተና ሆኗል::ባለስልጣኑ ይህን የሚቆጣጠርበት ምንም አይነት መንገድ የለም:: የአካባቢው መስተዳድር ህጋዊውን እና ህገወጡን መለየት ይችላል::ህብረተሰቡን ግንዛቤ በማስጨበጥ ከሚገባው በላይ ጥያቄ እንዳያቀርብ የማድረግ ስራ የሚመለከታቸው አስተዳደሮች መስራት ቢኖርባቸውም፤ እየሰሩ አይደለም:: እንደውም ከጀርባ ሆነው ብዙ ነገር ሲፈፀም ይታያል::
መፍትሔ
ወደ ፊት ‹‹ዞን እንሆናለን፤ እናድጋለን›› በሚል ሁሉም ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች ከነባሩ የመንገድ ስፋት በላይ መንገዱ እንዲጨምር ይፈልጋሉ፤መንገዶች ነባሩን ኮሪደር ብቻ ይዘው ሳይሰፉ እንዲቀጥሉ ማድረግ አንደኛው መፍትሄ መሆኑን ያመለክታሉ::ከወሰን ማስከበርና ካሳ ጋር የተያያዘው ትልቁ ችግር ያለው በከተሞች አካባቢ ነው፤እዚህ አካባቢ ያለውን ችግር ለመፍታት መንገዶች ከተማ በማይገቡበት ሁኔታ አዲስ መንገድ መስራት ሌላው አማራጭ ነው ይላሉ ::
ቀደም ሲል መንገድ ይሰራል ተብሎ መጀመሪያ የተነሺዎችና የንብረት ዝርዝር ይለቀማል:: ህብረተሰቡ እንዲወያይ ይደረጋል:: ልክ መንገዱ እንደሚሰራ ሲታወቅ ወዲያውኑ ተጠራርተው ብዙዎች ለመንገድ በታሰበው ቦታ ላይ ቤት የሚሰሩበትን ሁኔታ ለማስቀረትም ጥናት እየተካሄደ ነው:: ከዚህ ቀን ጀምሮ ንብረት ማስፈር አይቻልም ተብሎ የቁርጥ ቀን ለማዘጋጀት ታቅዷል::
በወረዳም ሆነ በከተማ በመንገዱ ላይ ያለው ንብረቱ ተቆጥሮ ተፈራርሞ ማስቀመጥን የሚጠይቅ በመሆኑ፤ በዚህ በኩልም መላ ታስቧል::ከኢትዮጵያ መረጃ እና ደህንነት ጋር በመተባበር የአየር ፎቶ ግራፍ በማንሳት ከመንገዱ ርቀት ምን ያህል ቤቶች እንዳሉ ማስረጃ በመያዝና በማጠናከር ለመስራት መታቀዱን ይናገራሉ::
ማስረጃ መሰብሰብ ላይ አሰራሩ መዘመን አለበት በሚል ተጨማሪ ጥናቶች እየተካሄዱ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ጥናቶቹ ሲጠናቀቁ አሁን የሚታዩት ችግሮች እንደሚቀረፉም ነው የጠቆሙት::በካሳ ክፍያ ላይ ‹‹የወረዳና የከተማ አስተዳደሮቹ በጀት ተመድቦላቸው ሃላፊነቱን ይውሰዱ፤ ራሳቸው ተጠያቂ ይሁኑ›› የሚል አማራጭ ሃሳብ መኖሩንም አቶ ደረጄ ይናገራሉ::
በኢትዮጵያ የመንገድ ግንባታ ውስጥ የፕሮጀክት መዘግየት የግድ እስከሚመስል ድረስ በሁሉም መንገዶች ላይ በእርግጥም ይስተዋላል:: ለመዘግየቱ የተለያዩ ምክንያቶች ቢጠቀሱም፣ የወሰን ማስከበር ችግር በዋነኛነት ተጠቃሹ ምክንያት ሆኖ ይገኛል:: ይህ በፕሮጀክት አፈፃፀም ላይ ከፍተኛ ጋሬጣ ሆኖ የቀጠለው የወሰን ማስከበር ችግር የተቆላለፈ በመሆኑ ችግሩን ለማቃለል የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ብቻውን ታግሎ የሚያሸንፈው አይሆንም::የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ ወሳኝነት አለው::
አዲስ ዘመን መጋቢት 22/2012
ምህረት ሞገስ
የብዙ ሰው እጅ ያለበት ፈታኝ ተግባር – የወሰን ማስከበር ትመና