አዲስ አበባ፡- የሀገር መከላከያ አመራሩም ሆነ ሠራዊቱ የኮሮና ቫይረስን እንደ አንድ ትልቅ ሀገራዊ አደጋና ጠላት አይቶ ለቫይረሱ የሚጋብዙ ሁኔታዎችን ተከታትሎ ለመቆጣጠርና ለማስፈጸም እየሰራ መሆኑን የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ፡፡
ሠራዊቱ የህዳሴ ግድብን በየትኛውም መልኩ መጠበቅ እንደሚችል ገለጹ።
ሜጀር ጀነራል ብርሃኑ ጁላ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፣የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ ካምፕ ባለባቸው ቦታዎች በካምፕ እንዲቆይ ተደርጓል።
በመከላከያና በእዞች፣በጦር ክፍሎች ደረጃ ኮሚቴዎች ከላይ እስከ ታችኛው አደረጃጀት ድረስ መቋቋማቸውን ጀነራል ብርሃኑ ጠቅሰው፣ሠራዊቱ ለመዝናናት፤ ለዘመድ እና ለቤተሰብ ጥየቃ ፈቃድ ወስዶ የሚሄድበት ሁኔታ እንዲወሰን መደረጉን ተናግረዋል። የሰላም አስከባሪ ዝውውሩን (ፒስ ኪፒንግ ሮቴሽን) ለጊዜው እንዲቆም መደረጉንም ጠቅሰዋል።
አመራሩም ሆነ ሠራዊቱ ኮሮና ቫይረስን እንደ
አንድ ትልቅ ሀገራዊ አደጋና ጠላት አይቶ ለዛ የሚጋብዙ ሁኔታዎችን ተከታትሎ እንዲቆጣጠርና እንዲያስፈጽም እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣የሰራዊቱ እንቅስቃሴዎች እንዲወሰኑ፤ ከቦታ ቦታ የኃይል ንቅናቄ እንዲቋረጥ ፤ ጽዳትና ንጽህና በየካምፑ በከፍተኛ ደረጃ እንዲጠበቅ መደረጉን ጀነራሉ አመልክተዋል።
በመከላከያ ውስጥ በተለያየ ደረጃ ያሉ ሆስፒታሎችና በየክፍሉ ያሉ የጤና ባለሙያዎች የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመግታት በልዩ ትኩረት እየሰሩ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ምክትል ኤታማዦር ሹሙ የአገር መከላከያ ሠራዊት የህዳሴው ግድብን በየትኛውም መልኩ መጠበቅ እንደሚችልም አስገንዝበዋል።ግድቡ ለመከላከያ ሠራዊት የሀገር ሉአላዊነት ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፣ግድቡን በማንኛውም መልኩ ይጠብቀዋል ብለዋል።
እንደ ጀነራሉ ገለጻ፤ መከላከያ ሰራዊት ሕይወቱን ለሀገር ሰጥቶ ገንዘቡን የሚሰስት ኃይል አይደለም።የግደቡ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለግንባታው የሚያደርጉትን መዋጮ አላቋረጡም።በሀገሪቱ ለግድቡ ከፍተኛ ገንዘብ ካዋጡ ተቋማት ግንባር ቀደሙ መከላከያ ነው።
‹‹የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል በታላቁ ሕዳሴ ግደብ ዙሪያ የሚመጣ ማናቸውም አይነት ተቃርኖ በኢትዮጵያ ሕልውና ላይ የተቃጣ አደጋ አድርጎ ይወስደዋል›› ያሉት ጀነራሉ፣ኢትዮጵያ በአባይ ውሃ ላይ ግድብ ከሰራች ግብጽ ጦርነት ትከፍታለች የሚለው በንጉሱም በደርግም ዘመን ሲባል እንደኖረ ተናግረዋል።የኢትዮጵያ ጥያቄ የመልማት እና የተፈጥሮ ሀብቷን የመጠቀም መሆኑን ጠቅሰው፣ከዚህ ውጭ ግብጽን የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላትም አስታውቀዋል።ሁለቱን ሀገራት ወደ ጦርነት ውስጥ ሊያስገባ የሚችል ምንም አይነት መሰረታዊ ምክንያት እንደሌለም ገልጸዋል።
የግብጽ መሪዎች፤ ፖለቲከኞች፤ ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ላይ ከሚሰነዝሩት የተሳሳተ የጥላቻ ቅስቀሳና ከተዛባ ፕሮፓጋንዳቸው መውጣት እንዳለባቸው አስገንዝበው፣ ‹‹ወንድማማች ሕዝብ ነን።ለሁላችንም የሚበጀው ተቀምጦ መነጋገርና መደራደር ብቻ ነው።››ሲሉም አስታውቀዋል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 22/2012
ወንድወሰን መኮንን
Woah! I’m really loving the template/theme of this website.
It’s simple, yet effective. A lot of times it’s
challenging to get that “perfect balance” between usability and
appearance. I must say that you’ve done a fantastic job with
this. Additionally, the blog loads extremely fast for me
on Opera. Superb Blog!