አውሮፓውያን አፍሪካን ለመቀራመት ወደ ጦርነት እየተጓዙ በነበረበት ወቅት በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር ውስጥ ቡቦኒክ የተባለ ወረርሽኝ ተከስቶ በአንድ ዓመት ጊዜ በከተማዋ ይኖሩ ከነበሩ ህዝቦች 15 በመቶ ገደማ ማጥፋቱ ይነገራል። በወቅቱ ሴኔጋልን ያስተዳድር የነበረው የፈረንሣይ ቅኝ ገዥ መንግስት በእንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ፤ የኳራንቲን ካምፖች ማቋቋም፤ አስገዳጅ ክትባቶች እና ቤቶችን እስከ ማቃጠል የደረሰ ርምጃ ወስዷል። ተመሳሳይ ወረርሽኝ በአፍሪካ አገራት ላይ እአአ ከ1855 እስከ 1859 ባለው ጊዜ ውስጥ የተከሰተ ሲሆን፤ በአፍሪካ የሚገኙ የአውሮፓ አስተዳዳሪዎች በቅኝ ግዛቶች ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ ርምጃ ወስደዋል። ለምሳሌ፤ በኬንያ ናይሮቢ “የንግድ አውራጃ” በሚባለው አካባቢ እአአ 1902 ወረርሽኝ የተከሰተ ሲሆን፤ ወረርሽኙ በሀይል እንዲገታ ተደርጓል።
በአህጉሪቱ ላይ ወረርሽኝ እንደሚከሰት አውሮፓውያን ከመምጣታቸው አስቀድሞ ተተንብዮ ነበር:: እናም አፍሪካውያን ምን ዓይነት አደጋ እንደሚገጥማቸው አያውቁም ነበር። በአሁኑ ወቅት ወረርሽኝ ለአፍሪካ ህመም እና ሞት ዋነኛው መንስኤ አይደለም። ሆኖም ግን፤ ቅኝ ገዥዎች ትተውት በሄዱት ቁስል ምክንያት የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚ በውጭ ጣልቃ ገብነት የተገነባ መሆንና ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ ፍልሰት በመብዛቱ ምርት እየቀነሰ መምጣት ስጋት እየፈጠረ ይገኛል። ቅኝ ገዥዎች በአካባቢዎቹ ላይ በወሰዷቸው ርምጃዎች ምክንያት ተወዳጅነት አልነበራቸውም። አፍሪካውያን ከቅኝ ገዥ ባለስልጣናት ጋር መተባበር አገራቸውን ማበላሸት መሆኑን በማወቃቸው ለነፃነታቸው እንዲታገሉ አድርጓቸዋል።
ከመቶ ዓመት በኋላ በዓለም ሌላ ወረርሽኝ ይመጣል ብሎ ያሰበ ሰው አልነበረም:: እ.ኤ.አ. 2019 የታህሳስ ወር መገባደጃ ላይ የኮሮና ቫይረስ ቻይና ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየ እና ስርጭቱም በዓለም ዙሪያ የተከሰተ ሲሆን፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በመግደሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች በከፍተኛ ደረጃ ነግሰዋል። የዓለም ጤና ድርጅትን እና የአለም የጤና ባለሙያዎች ምክር በመጣስ ብዙ ሀገራት የጉዞ እገዳዎች እያደረጉ ይገኛሉ።
የአፍሪካ መንግስታትም እንዲሁ በአህጉሪቱ ላይ ጠንካራ አቋም ከመውሰዳቸው በፊት ቫይረሱን ለመቆጣጠር እየተቸገሩ ነው። እንደሌላውና የተቀረው የዓለም ክፍል እንደሚያደርገው ኮሮና ከቻይና እንዳይመጣ በማድረግ ላይ ማተኮራቸው ተስተውሏል። በአህጉሪቱ በሙሉ ከቻይና ጋር የአየር ግንኙነቶች እንዲቋረጡ እየተደረገ ይገኛል። እንደ ኬንያ ባሉ አንዳንድ ሀገሮች ይህ ሁኔታ ፀረ-ቻይናዊ ስሜት እንዲበራከት ምክንያት እየሆነ መጥቷል።
እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ ቢያንስ 18 የአፍሪካ አገራት 14ቱ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራት በአጠቃላይ ወደ 200 የሚጠጉ የኮሮና ቫይረስ በሽታዎችን ሪፖርት ተደርገዋል። ሪፖርት የተደረጉባቸው ጉዳዮች ሲታዩ ከግብጽ ውጭ አብዛኞቹ ታማሚዎች የሚመጡት ከአውሮፓ ነው። የቫይረሱን ወደአፍሪካ መግባት ያሳወቀችው ቡርኪና ፋሶ ስትሆን፤ አንድ ባልና ሚስት ወደ ፈረንሳይ ከተጓዙ በኋላ በቫይረሱ ተይዘው እንደተመለሱ ተዘግቦ ነበር። ናይጄሪያ በ 44 ዓመቷ ጣሊያናዊት ምክንያት ቫይረሱ ወደ አገሯ ገብቷል። በካሜሩን እና በቶጎ የነበረው ሁኔታም ተመሳሳይ ሲሆን ከአውሮፓ አገራት ሲጓዙ የነበሩ ሰዎችን ይመለከታል። እንደ ዓለም ጤና ድርጅት ከሆነ በአሁኑ ጊዜ በአውሮፓ በሽታው በመጀመሪያ ከተገኘባት ቻይና የበለጠ ቁጥር ያላቸው ታማሚዎች እየተገኙ ነው።
ከአውሮፓ ጋር ረዥም ታሪካዊ ትስስር ላለው የአፍሪካ አህጉር እንደ ጉዞ እገዳዎች ያሉ ርምጃዎች መጣል አስቸጋሪ ይሆናል:: ምክንያቱም፤ አህጉሪቱ የምትኖረው በአውሮፓውያን ድጋፍና ብድር በመሆኑ ነው። ለምሳሌ፤ የኬንያ መንግሥት ባወጣው ዘገባ መሠረት ባለፈው ዓመት ከአውሮፓና ከቻይና የመጡ ሰዎች መድረሻ ነበረች። በእርግጥ ከአውሮፓ የመጡት ጎብኝዎች ቁጥር ከእስያ እና ከመካከለኛው ምስራቅ በእጥፍ እየጨመር ይገኛል። ከአፍሪካ ሀገራት መካከል ወደ ኬንያ የሚመጡ ጎብኝዎች ቁጥር 45 በመቶ አድጓል። ኬንያ በዓመት ከጎብኝዎች አንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ታገኛለች። ለዜጎቿም ከአንድ ሚሊዮን በላይ የስራ እድል ፈጥራለች።
በእርግጥ ከአውሮፓ የሚመጡትን ሰዎች ዜጎች በማገድ ረገድ ኡጋንዳ ጣሊያናውያን፤ ስፔናውያን፤ ጀርመኖች እና ፈረንሣዮች እንዳይመጡ የጠየቀች ሲሆን፤ በዚም ከስድስት ሺህ በላይ ጎብኚዎች እንዲመለሱ ተደርጓል። ቻይናውያን የሚሳተፉበትን ጨምሮ አለም አቀፍ ስብሰባዎችን አግደዋል። ኬንያም ተመሳሳይ እገዳ ጥላለች። ይህ ማለት ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ በጣም የሚፈለግ ገቢ ያስቀራል ማለት ነው:: በዚህም ምክንያት ኢኮኖሚያቸው ሊጎዳ እንደሚችል ተገምቷል። ሆኖም ጉዞዎች እና ቱሪዝም ለእድገት ቁልፍ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል ዋነኛው ሲሆን፤ አህጉሪቱ በጣለችው የጉዞ እገዳዎች ዘላቂነት ላይ ጥያቄዎች ቀርበዋል። ምንም እንኳን አፍሪካ በዓለም አቀፉ የቱሪዝም ገበያ ውስጥ በጣም ጥቂቱን ድርሻ ብትይዝም ኢንዱስትሪው አሁንም ቢሆን ከፍተኛ እንደሆነና እ.ኤ.አ. በ2018 ከአህጉሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚ 8 ነጥብ 5 ከመቶው በላይ የያዘ ሲሆን፤ ከ24 ሚሊዮን በላይ አፍሪካዊያንን ቀጥሮ እያስተዳደረ ይገኛል። ቫይረሱ በአሁኑ ጊዜ ከ 166 በላይ አገራት ውስጥ በመገኘቱ ከተነገረ በኋላ የኬንያ የትራንስፖርት ሚኒስትር በረራዎችን ከሁሉም አገራት ጋር ማቆም እንደማይቻል ተናግረዋል።
ምንጭ፡ አልጀዚራ ድረ ገፅ
አዲስ ዘመን መጋቢት 14 /2012
መርድ ክፍሉ