አንዳንድ ወገኖች ሃሳብን በነፃ የመግለጽ ነፃነትን ሊገድብ ይችላል በሚል ሲሟገቱበት ከርመዋል። ሌሎች የሥጋት ደረጃቸውን ከፍ አድርገው አሁን በሥራ ላይ ካለውና እንደአፋኝ ከሚታየው የጸረ ሽብር አዋጅ ጋር መሳ ለመሳ ያስቀምጡታል፤ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የተረቀቀውን አዋጅ። ይህም ሆኖ አዋጁ ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ዕለት ጸድቆ የአገር ሕግ ሆኗል። በተጨማሪም ፓርላማው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅንም የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በአብላጫ ድምጽ ማጽደቁ ተሰምቷል። ተሻሽለው ወደጸደቁት አዋጆች ዝርዝር ከማለፌ በፊት ስለአዋጆቹ ጥቅል ሀሳቦችን ላንሳ።
የሕግ አውጪው እሳቤ
የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን መከላከል አዋጅ
በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት ዕውቅና ከተሰጣቸው መብቶች አንዱ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ነው። ይህ መብት በሕገ-መንግሥቱ ብቻ ሳይሆን ሕገ- መንግሥቱን ለመተርጐም እንደ አጋዥ ተደርገው በሚቆጠሩና የሀገራችን የሕግ ሥርዓት አካል በሆኑት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶችም የተካተተ ነው። ሕገ-መንግሥቱንና እነዚህን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣ እንዲሁም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን በማክበር ረገድ ጥሩ ሥም ያላቸውን ሀገራት ልምድም ስንመለከት ይህ መብት ፍፁም የሆነ መብት ሳይሆን፣ ገደብ ሊጣልበት የሚችል መብት መሆኑን እንረዳለን።
በመብቱ ላይ የሚጣለውን ገደብ ዓላማ፣ የገደቡን አስፈላጊነትና ተመጣጣኝነትን በጥንቃቄ መርምሮና አመዛዝኖ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ በሕግ ገደብ ማስቀመጥ በዴሞክራሲያዊ ሀገራት ተቀባይነት ያለውና የተለመደ አሠራር ነው። በሀገራችን ያለው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን የማጠናከር እንቅስቃሴም ከዚህ ልምድና አሠራር ውጪ ሊሆን አይችልም። በተለይም አሁን ካለው ፖለቲካዊ ነፃነት ጋር እየተበራከተ የመጣው የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ሥርጭት መፍትሔ ካልተበጀለት ለሀገራዊ ሠላምና ደህንነት እንዲሁም ለለውጥ እንቅስቃሴው ዘላቂነት ትልቅ አደጋ መሆኑ ግልፅ ነው።
የኤክሳይዝ ታክስን በተመለከተ፣
የኤክሳይዝ ታክስ ውስን (specific)፣ በዋጋ ላይ የተመሰረተ (ad valorem) ወይም ሁለቱንም የቀላቀለ ታክስ ሆኖ ሊቀረጽ ይችላል። ታክሱ በአገር ውስጥ በሚመረቱ ዕቃዎች ላይ ብቻ ሳይሆን ከውጭ በሚገቡ ተመሳሳይ ዕቃዎችም ላይ ይጣላል። በመሆኑም ታክሱ በአገር ውስጥ በሚመረቱ እና ከውጭ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ እኩል መጣል አለበት። ይህ መርህ ከዓለም ንግድ ድርጅት የታሪፍ እና ንግድ አጠቃላይ ስምምነት አንቀጽ 3 የሚመነጭ ነው። በዚህ አንቀጽ ድንጋጌ መሠረት ከጉምሩክ ታሪፍ በስተቀር ሌሎች ታክሶች ለአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ከለላ እንዳይሰጡ በአገር ውስጥ በሚመረቱ እና ከውጭ በሚገቡ ተመሳሳይ ምርቶች ላይ እኩል መጣል ይኖርባቸዋል። በረቂቅ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ መሠረት ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች የቀረጥ ማስከፈያ መሠረት የጉምሩክ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እና የጉምሩክ ቀረጥ ድምር ሲሆን፣ በአገር ውስጥ ለሚመረቱ ዕቃዎች ደግሞ የመሸጫ ዋጋ ነው።
ረቂቅ አዋጁ የኤክሳይዝ ታክስ መርሆዎችን፣ የአገሮችን መልካም ተሞክሮ መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን፣ አሁን በሥራ ላይ ያለው የኤክሳይዝ አዋጅ የታክስ መሠረት የማምረቻ ወጪ ነው። በረቂቅ አዋጁ የታክስ መሠረቱ ወደ መሸጫ ዋጋ መቀየሩ ግልጽነትን የሚያሰፍን እና የታክስ ስወራን ለመከላከል ከፍተኛ እገዛ ማድረግ በሚያስችለው ሁኔታ የተቀረጸ ነው። ረቂቅ አዋጁ የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ምርት እና ንግድ ላይ ለመሰማራት አስቀድሞ መመዘገብን የሚጠይቅ በመሆኑ የተሻለ ቁጥጥር ለማድረግ ያስችላል።
የኤክሳይዝ ታክስ ኢኮኖሚው ከደረሰበት ደረጃ የተጣጣመ በማድረግ የኤክሳይዝ ታክስ የሚጣልባቸው ምርቶች መከለስ፣
ከኅብረተሰቡ ጤና አንጻር ከSpecific እና Ad Valorem አንዱ ወይም ሁለቱ የሚጣሉባቸው ዕቃዎች መለየትና በተለየው አግባብ መሠረት እንዲጣል በማድረግ በምርቶቹ መጠቀም ሊከሰት የሚችለውን የጤና ችግር መቀነስ፣
የታክሱ መሠረት በማምረቻ ወጪ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ሲፈጠሩ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመቅረፍ በታክስ ከፋዩ ያለውን የተገማችነት ችግር ለመቅረፍ ብሎም ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ፣
በወጪ ንግድ ላይ እየተፈጠረ ያለውን በግብዓት ላይ የተከፈለውን የኤክሳይዝ ታክስ አመላለስ ችግር በመቅረፍ ለወጪ ንግድ አመቺ ሁኔታ መፍጠር፣
የኤክሳይዝ ታክስ ተደራራቢነትን ማስቀረት (ታክሱ የሚጣለው ኤክሳይዝ ታክስ በሚጣልበት ምርት ወይም አገልግሎት በመጨረሻ ምርቱ ላይ እንዲሆን ለማድረግ) ያለመ ነው።
ኤክሳይዝ ታክስ የሚጣልባቸው ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች የሚከተሉት ባሕሪያት ሊኖራቸው ይገባል።
1. የዕቃዎቹ ወይም የአገልግሎቶቹ ምርት፣ ስርጭት እና ሽያጭ በታክስ ሰብሳቢው መስሪያ ቤት የቅርብ ክትትል ሊደረግበት የሚችል በዚህ ሂደት ለታክስ ስወራ ያለው ተጋላጭነት አነስተኛ መሆን፣
2. ለዕቃዎቹ ወይም ለአገልግሎቶቹ ያለው ፍላጎት ለዋጋ ያለው ተለጣጭነት (Demand is price-inelastic) አነስተኛ መሆን፣
3. ዕቃው ወይም አገልግሎቱ የቅንጦት መሆን፣
4. ዕቃው ወይም አገልግሎቱ በጤና ወይም በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያስከትል መሆኑ፣ናቸው።
አዋጆቹ ይዘውት የመጡት ማሻሻያዎች፣
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሐሙስ ዕለቱ አስቸኳይ ስብሰባው የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን በተመለከተ የቀረበ አዋጅን አጽድቋል።
የምክር ቤቱ የሕግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቅድሚያ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበው ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ላይ መክሯል።
አዋጁ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ለማህበራዊ ስምሪት፣ ለፖለቲካ መረጋጋት፣ ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሰብዓዊ ክብር እና ለብዝሃነት ጠንቅ መሆኑን በመገንዘብ በተለይም በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በኅብረተሰቡ መካከል ያሉ መልካም እሴቶች በጥላቻ ንግግሮችና በሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ እየተሸረሸሩና ለሀገርም ስጋት እየደቀኑ በመሆናቸው እንዲሁም እነዚህን ችግሮች አሁን ባሉት ሕጎች መፍታት የማይቻል በመሆኑ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
የጥላቻ ንግግር እና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ዴሞክራሲያዊ ውይይት እና ክርክር ለማድረግ እንቅፋት በመሆኑ ከብሔር እና ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ የጥላቻ ንግግር እና ሃሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨትን እንዲሁም ዘርን፣ ጾታን እና አካል ጉዳተኝነትን መሠረት በማድረግ የሚደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እና ሃሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ተገልጿል።
እንዲሁም የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭትን በሕግ መከልከል አስፈላጊ በመሆኑ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱም ተነግሯል።
የምክር ቤቱ አባላትም በአዋጁ ላይ ያላቸውን ሃሳብ እና አስተያየት የገለጹ ሲሆን፣ ለአብነትም ይህ አዋጅ የዜጎችን ሃሳብ በነፃነት የመግለጽ መብት የሚጋፋ እንደሆነ አንስተዋል። የሕግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምላሽና ማብራሪያም ሰጥቶበታል።
በዚህም አዋጁ በሕገ-መንግሥቱ ላይ ከተቀመጠው የመናገር መብት ጋር እንደማይቃረን፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 29 (6) እና (7) ከተቀመጡት ገደቦች ውስጥም አንዱ ምክንያት ሰብአዊ ክብርን መጠበቅ ሲሆን፥ የጥላቻ ንግግር ሰብአዊ ክብርን የሚነካ ዋነኛው በመሆኑ ከተቀመጠው ገደብ ጋር የሚገናኝ መሆኑ ምላሽ ተሰጥቶበታል።
ምክር ቤቱ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ አዋጅን በ23 ተቃውሞ እና በ2 ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።
በተያያዘም የምክርቤቱ የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ተመልክቷል።
ቋሚ ኮሚቴው በሥራ ላይ ያለው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ለረጅም ጊዜ በሥራ ላይ የቆየ በመሆኑ እና የማምረቻ ወጪን መሠረት አድርጎ የሚሰላ በመሆኑ ግልፅነት የሚጎድለው መሆኑን አንስቷል።
ይህን ለማስቀረትም አዲሱ አዋጅ በመሸጫ ዋጋ ላይ እንዲሰላ በማድረግ ለከፋይ እና አስከፋዩ ግልፅነት የሚፈጥር መሆኑን አመላክቷል።
በተጨማሪም ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በአካባቢ ደህንነት ላይ እያስከተሉት ያለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ከተወሰነ ዓመት በላይ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ለመገደብ እንዲሁም ለጤና ጎጂ በሆኑ ምርቶች ላይ ያለውን የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔን በመፈተሽ ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አዋጁ መዘጋጀቱን ቋሚ ኮሚቴው አስታውቋል።
በረቂቅ አዋጁ ላይ በተደረጉ ማሻሻያዎች ላይም ቋሚ ኮሚቴው፥ ከ1 ሺህ 300 ሲሲ ያልበለጠ የፈረስ ጉልበት ያላቸው ተሽካርካሪዎች እና ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ኤክሳይዝ ታክስ አዲስ በሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ፣ ሙሉ በሙሉ ተበትነው የቀረቡ፣ በሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ እንዲገጣጠሙ፣ በከፊል ተበትነው የገቡ እና አዲስ ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ30 በመቶ ወደ 5 በመቶ ዝቅ እንዲል ማሻሻያ እንደተደረገበት አንስቷል።
በተጨማሪም ከ1 ዓመት እስከ ከ2 ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ80 በመቶ ወደ 55 በመቶ እንዲሁም፥ ከ2 ዓመት እስከ ከ4 ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ130 በመቶ ወደ 105 በመቶ ዝቅ እንዲል ማሻሻያ ተደርጎበታል።
ከ4 እስከ 7 ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ230 በመቶ ወደ 205 በመቶ ዝቅ እንዲል ማሻሻያ መደረጉ ተጠቅሷል።
ከ7 ዓመት በላይ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ430 በመቶ ወደ 405 በመቶ ዝቅ እንዲል ማሻሻያ መደረጉም ነው የተነሳው።
ይህ ማሻሻያ መካከለኛ የገቢ ደረጃ ላይ የሚገኘው የኅብረተሰብ ክፍልን ተጠቃሚ ለማድረግ ታስቦ መዘጋጀቱንም ቋሚ ኮሚቴው ገልጿል።
በሲጋራ ላይ የተጣለው የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ በፓኬት በዋጋው 30 በመቶ እንዲሁም በፍሬ 5 ብር የነበረው በኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያው ተጨምሮ 8 ብር እንዲሆን መደረጉንም ነው የገለጸው።
በረቂቅ አዋጁ የታሸገ ውሃ ላይ ተጥሎ የነበረው ኤክሳይዝ ታክስ ከ15 በመቶ ወደ 10 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል።
በቴሌኮም አገልግሎቶች ላይ እንዲጣል በኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጁ ቀርቦ የነበረው የ5 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ እንዲወጣ ተደርጓል።
በተጨማሪም አዋጁ በማሻሻያው ከፀናበት ዕለት በፊት የባንክ ፍቃድ የተሰጣቸው እና አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለበት ዕለት አንስቶ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ኤክሳይዝ ታክስ የሚጣለው እና የሚሰበሰበው፥ በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 307/1995 በተሻሻለው ድንጋጌዎች መሠረት ይሆናል ተብሏል።
ከቅጣት ጋር ተያይዞ በረቂቅ አዋጁ ላይ የተቀመጠው ድንጋጌ ዝቅተኛውን የቅጣት ገደብ የማያስቀምጥ በመሆኑ አንቀጹ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ሰው ከ3 ዓመት እስከ 5 ዓመት የእስር ቅጣት እና ከ50 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲጣል በሚል ማሻሻያ እንደተደረገበትም ተገልጿል።
በረቂቅ አዋጁ ላይ የተወያየው ምክር ቤቱ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁን በ4 ተቃውሞ፣ በ7 ድምጸ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።
እንደማሳረጊያ
በተለይ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የጸደቀው አዋጅ ከሚነሱበት ትችቶች አንዱና ምናልባትም በዚህ ጹሑፍ አቅራቢ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ላልተገባ የትርጉም ክፍተት ሊጋለጥ ይችላል የሚለው ነገር ነው። የጥላቻ ንግግር ምንድነው? ሐሰተኛ መረጃ የሚባለው የቱ ነው? በመገናኛ ብዙኃን በቅንነት ከሚሰራ ስህተትስ በምን ይለያል? በመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ከተደነገገው የስም ማጥፋት ወንጀል ጋር ያለው ልዩነት በግልጽ የተቀመጠ ነው ወይ? አዋጁ መገናኛ ብዙኃን ትችት ለማቅረብ ካላቸው መብት ጋር እንዴት ይጣጣማል? በጠቅላላው አዋጁ ዜጎች ሃሳብን በነፃ የመግለጽ ነፃነታቸውን እንዳይገድብ ምን መደረግ አለበት?… የሚሉ ዐበይት ጉዳዮች አሁንም በዝርዝር መልስ የሚፈልጉ ናቸው።
በአጭሩ በአዋጁ አፈጻጸም ወቅት እነዚህ ነጥቦች በሚገባ ሊታዩም ይገባል። የዘርፉ ተዋንያንን ሥጋት ለመቅረፍ የሚረዱ ተከታታይ መድረኮችን በማዘጋጀት ቢያንስ የመተማመን መንፈስ እያደገ እንዲመጣ የሚመለከታቸው አካላት ብዙ ሊሰሩ ይገባል።
በሌላ በኩል የአዋጁን አሉታዊ ገጽታ ብቻ በማንጸባረቅና በማጉላት ሃሳብን በነፃ የመግለጽ ነፃነት ፈተና ላይ እንደወደቀ አስመስለው የሚከራከሩ ወገኖች አሉ። እነዚህ ወገኖች የተለየ ሃሳብ የመያዝ መብታቸውን እንደተጠበቀ ሆኖ የችግሩን ዙሪያ ገባውን ለማጤን የጥላቻ ንግግሮች እና ሐሰተኛ መረጃዎች በገፍ መለቀቅ እያስከተለ ያለውን አገራዊ ቀውስና አለመረጋጋት ሚዛን ላይ ሊያስቀምጡ እንደሚገባ ማስታወስ ተገቢ ይሆናል። (ማጣቀሻዎች፡- ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ከፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተገኙ መረጃዎች፣ የፋና ዘገባ…)
ይህ ዓምድ በተለያዩ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዜጎች ነፃ አስተያየታቸውን የሚሰጡበት ነው። በዓምዱ ላይ የሚወጡ ጽሑፎች የዝግጅት ክፍሉን አቋም አያመለክቱም።
አዲስ ዘመን ቅዳሜ የካቲት 7/2012
abebeferew@gmail.com
ፍሬው አበበ