እንደምን ሰነበታችሁ! እንኳን በጤና ተገናኘን!
የኢንቨስትመንት የሕግ ማዕቀፎች በባህሪያቸው ፈጥነው ከሚሻሻሉ ሕግጋት ጎራ ይመደባሉ። ሕጎቹ በየጊዜው የሚፈጠሩትን ተለዋዋጭ አገራዊ፣ አካባቢ ያዊና ዓለማዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ ክለሳ ይደረግባቸዋል።
በኢትዮጵያም የነፃ ገበያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ መተግበር ከጀመረበት 1984 ዓ.ም ጀምሮ አሁን በሥራ ላይ እስከሚገኘው የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 769/ 2004 ድረስ አራት የኢንቨስትመንት አዋጆች ወጥተዋል።
እነዚህ አዋጆችና ተከትለዋቸው የወጡት የማስፈጸሚያ ደንቦች በየዘመናቸው የነበረውን የኢኮኖሚ ሁኔታና የልማት ግቦችን መሰረት አድርገው የተሰናዱ ነበሩ። ሕጎቹ ከኢንቨስትመንት ፖሊሲው ጋር መልካም ቅንጅት በመፍጠርም የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላስመዘገበው እመርታ የበኩላቸውን ሚና ተወጥተዋል። በተለይም ኢንቨስትመንትን መሳብ፣ ማበረታታት፣ ማስተዳደርና መጠበቅን ሁነኛ ዓላማቸው በማድረግ የተሻለ የሕግ ማዕቀፍና ከባቢ እንዲኖር አስችለዋል።
በዚህም አገሪቱ በየዓመቱ የሚያድግ የኢንቨስትመንት ፍሰት አስመዝግባለች። በተለይም ባለፉት አምስት ዓመታት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰት በአራት እጥፍ አድጓል። ይበልጡኑም እ.ኤ.አ በ2018 ዓ.ም ብቻ 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገራት የአምስተኛነት ደረጃን መያዟን ነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከአንድ ወር በፊት ያወጣው መረጃ የሚያሳየው።
ያም ሆኖ አገሪቱ ካላት ኢንቨስትመንትን የመሳብ እምቅ አቅምና በቀደሙት ጊዜያት የተዘነጉ ወሳኝ ሴክተሮች ያሏት ከመሆኑ አንጻር ሲታይ ውጤቱ የእፍኝ ያክል እንጂ የሚያጠግብ አይደለም። እናም የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ ከሁሉ አስቀድሞ የፖሊሲ ከባቢውንና የሕግ ማዕቀፎችን መፈተሽ ስለሚያስፈልግ በሥራ ላይ ያለውን አዋጅና ደንብ የሚያሻሽል የሕግ ረቂቅ በፓርላማው ጠረጴዛ ላይ ይገኛል።
አስፈጻሚው አካል ሕጉ እንዲጸድቅለት ለፓርላማው ባቀረበበት ወቅት ሕጉን ለማሻሻል ምክንያት ናቸው ያላቸውን ጉዳዮች አስቀምጧል። መንግሥት ካቀረበው ማብራሪያ ለመገንዘብ እንደሚቻለው በሥራ ላይ ያለው ሕግ በአገሪቱ በኢኮኖሚው ዘርፍ እየተካሄዱ ካሉ ለውጦች ጋር እንዲናበብ ማድረግ አስፈልጓል።
በተለይም የአገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች በግሉ ዘርፍ ሊሳተፉ የሚችሉባቸውን የኢንቨስትመንት ሥራዎች በመከለስ የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚ ዕድገትና ተወዳዳሪነት፣ በሥራ ፈጠራ እንዲሁም በቴክኖሎጂና ክህሎት ሽግግር ላይ ያለውን ሚና የማሳደግ ዓላማን ሰንቋል።
የኢንቨስትመንት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥርዓቱን ማዘመን፣ የኢንቨስትመንት ማነቆ ለሆኑ ጉዳዮች መፍትሔ በመስጠት የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲጨምር ማድረግ እንዲሁም የባለሀብቶች ቅሬታ የሚስተናገድበት ግልጽና ውጤታማ ሥርዓት ማበጀትም ለሕጉ መሻሻል ምክንያቶች ናቸው።
መንግሥት ብቻውን የሚሰማራባቸው መስኮች አለመኖርና የክርክሮቹ አውደ-ሙግት
አዲሱ አዋጅ በሥራ ላይ ያለውን ጨምሮ የቀድሞዎቹ የኢንቨስትመንት አዋጆችና ደንቦች ከነበራቸው አቀራረብ ለየት ያለ መልክ ይዞ ነው ብቅ ያለው።
ነባሩ የኢንቨስትመንት የሕግ ማዕቀፍ መንግሥት በብቸኝነት የሚሠራቸውን፤ የግሉ ዘርፍ ከመንግሥት ጋር በሽርክና የሚሰማራባቸውን፤ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉባቸውን እንዲሁም የውጭ ባለሀብቶች የሚሰማሩባቸውን የኢንቨስትመንት መስኮች ዝርዝር የያዘ ነው። ይህም በሕግ የአረቃቀቅ አነጋገር “Positive List” ሲስተም ይባላል።
የዚህ ዓይነቱ የህግ ማዕቀፍ በተለይም ከውጭ ባለሀብቶች ተሳትፎ አንጻር ሲታይ ውስንነቶች አሉበት። ይህንን ሥርዓት የሚከተል ሕግ የውጭ ኢንቨስተሮች የሚሳተፉባቸውን ዘርፎች በሙሉ አንጠፋጥፎ እንዲዘረዝር ይጠበቃል።
ነገር ግን በየጊዜው ተለዋዋጭ ሁኔታዎችና አዳዲስ የኢንቨስትመንትና የቴክኖሎጂ መስኮች በሚታዩበት በዚህ የዓለም አቀፍ መንደርተኝነት (Globalization) ወቅት የውጭ ባለሀብቶችን “መሳተፍ የምትችሉት በዚህ በዚህ ዘርፍ ብቻ ነው” ብሎ ግትር ማለት አዋጭነት የለውም።
በዚሁ መነሻ ይመስላል አዲሱ የኢንቨስትመንት የህግ ማዕቀፍ የውጭ ባለሀብቶች ሊሰማሩ የሚችሉባቸውን የኢንቨስትመንት መስኮች ዝርዝር (Positive List) ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ በተደረጉ የኢንቨስትመንት መስኮች (Negative List) የሚለውጥ ሆኖ ነው የተሰናዳው።
“Negative List” የሚባለው የኢንቨስትመንት መስኮች ዝርዝር አገሪቱ ካስቀመጠቻቸው የልማት የትኩረት አቅጣጫዎቿ በመሳነት የውጭ ባለሀብቶች እንዲሳተፉ የማትፈቅዳቸውን ውስን መስኮቿን ብቻ መርጣ ዝግ በማድረግ ከእነዚያ ውጪ ባሉ ዘርፎች ደግሞ የውጭ ባለሀብቶች እንዲሳተፉ የምትፈቅድበት ነው።
ይህ ዓይነቱ ሥርዓትም አገሪቱ ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ በምታደርጋቸው መስኮች ውስጥ የተለያዩ ዓይነት አቀራረቦችንም እንድትከተል ዕድል ይሰጣታል። ለአብነት ሙሉ በሙሉ እንድትከለክል፤ የባለቤትነት ገደብ እንድታስቀምጥ፤ ዝቅተኛ የኢንቨስትመንት የመሰማሪያ መስፈርቶችን እንዲሁም የመልካም ውጤት አፈጻጸም ቅድመ-ሁኔታዎችንም እንድታስቀምጥ የሚፈቅድላት ይሆናል።
በሥራ ላይ ካለው አዋጅ አስቀድሞ የነበሩት ሦስቱም አዋጆች Negative List የሚባለውን የኢንቨስትመንት መስኮች ዝርዝር ሥርዓት ነበር የሚከተሉት። ሕጎቹ መንግሥት ብቻውን የሚሰማራባቸውን፤ ከመንግሥት ጋር በቅንጅት የሚከናወኑትን፣ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉትን እንዲሁም ከአገር ውስጥ ባለሀብቶች ጋር በቅንጅት የሚከናወኑትን መስኮች በመዘርዘር ከእነዚህ ውጪ ያሉትን በሙሉ የውጭ ባለሀብቶች እንዲሰማሩባቸው ይፈቅዱ ነበር።
የአሁኑ ረቂቅ ሕግም ተመሳሳይ አቀራረብ ተከትሎ ተዘጋጅቷል። ይሁንና አዲሱ ሕግ መንግሥት ብቻውን የሚሰማራባቸውን የኢንቨስትመንት መስኮች ያልያዘ በመሆኑ ከቀደሙቱ ፍጹም የተለየ ሆኗል።
በዚህም መሠረት በረቂቅ ደንቡ የሚዘረዘረው ከመንግሥት ወይም ከአገር ውስጥ ባለሀብት ጋር በጋራ የሚካሄዱ እንዲሁም ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉ የኢንቨስትመንት መስኮች ብቻ እንደሚሆኑ እና ከዚህ ውጪ ያሉ የኢንቨስትመንት መስኮች በሙሉ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት እንደሚሆኑ አዲሱ አዋጅ ይደነግጋል።
ይህም መንግሥት በወሳኝ የኢኮኖሚ አውታሮች በብቸኝነት በመሳተፍ ሞኖፖሊውን ተጠቅሞ የመሪነት ሚናውን መወጣት አለበት በሚሉት የልማታዊ መንግሥት ደቀ – መዛሙርትና በሊበራል አስተሳሰብ አቀንቃኞች መካከል እየተደረገ ላለው ክርክር ሁነኛ አውደ-ሙግት ሆኗል።
የሆነው ሆኖ ረቂቅ አዋጁ ከመንግሥት ጋር በቅንጅት የሚከናወኑ፣ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉና ከአገር ውስጥ ባለሀብቶች ጋር በቅንጅት የሚከናወኑ መስኮች ዝርዝር በቀጣይ በሚወጣ ደንብ እንደሚወሰን ይገልጻል። ይህ መደረጉ የግሉ ዘርፍ በአገሪቱ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ብሎም ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን ሚና ለማሳደግ እንደሚያግዝ ነው መንግሥት የሚገልጸው።
ለዚህ ደግሞ በመንግሥት የተያዙ ድርጅቶች በከፊል ለግሉ ሴክተር በሽያጭ ይተላለፋሉ። እነዚህ ድርጅቶች የተሰማሩባቸውን እንዲሁም ሌሎች ለግል ሴክተር ወይም ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ የሆኑ ዘርፎች ክፍት እንደሚደረጉም ነው እየተገለጸ ያለው። ይህ የሚፈጸምበት አዋጅም እየተዘጋጀ ነው።
ይህ ደግሞ በጥንቃቄ የሚፈጸም ከሆነ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲውን በአግባቡ ለመተግበር እንዲሁም የኢንቨስትመንት ሕጉን ከአፍሪካ አህጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጣና ግዴታዎችና ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ከምታደርገው ጥረት ጋር በተናበበ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ ያስችላል።
የአህያ ቄራ እንደማይከፈት ተስፋ አለን!
በቀደመው ሕግ ያልነበሩ ነገር ግን አዲሱ አዋጅ ካካተታቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ማናቸውም ኢንቨስትመንቶች ለሕግ፣ ለሞራል፣ ለማህበረሰብ ጤና ወይም ደህንነት መቃረን እንደማይኖርባቸው የሚደነግገው ነው።
በአገራችን “በውጭ ባለሀብቶች የአህያ ቄራ ሊከፈት ነው” በሚል አንድ ሰሞን የመነጋገሪያ አጀንዳና የህዝቡንም ቁጣ የቀሰቀሰውን ጉዳይ አንዘነጋውም። ይህ ድንጋጌ መቀመጡ ታዲያ በግልጽ ያልተከለከሉ ነገር ግን እንዲህ ያሉ የማህበረሰቡን ሞራል የሚቃረኑ ወይም ጤናና ደህንነትን የሚያውኩ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል ስለሚያግዝ ይበል የሚያሰኝ ነው።
የውጭ ባለሀብቶች የቤትና የሕንፃ ባለቤቶች ይሆናሉ
መነጋገሪያ የሆነው ሌላው የአዲሱ አዋጅ ክፍል ደግሞ የኢንቨስትመንት ማበረታቻቸዎችን የተመለከተው ነው። ለኢንቨስትመንቶች የሚሰጡትን ማበረታቻዎች ዓይነትና መጠን የሚዘረዝር ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደሚወጣ አዋጁ በመርህ ደረጃ ቢያስቀምጥም በተለይም ለውጭ ባለሀብቶች እንደማበረታቻ የሚወሰዱ ጉዳዮችንም አካቷል።
የመጀመሪያው የውጭ ባለሀብቶች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደው ነው። የውጭ አገር ሰዎችን የሚመለከተው የፍትሐብሔር ሕጉ አንቀጽ 390 እና ተከታዮቹ ማንኛውም የውጭ አገር ሰው የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ሊሆን እንደማይችል በግልጽ ክልከላ አስቀምጧል።
አዲሱ የኢንቨስትመንት አዋጅ ግን የውጭ ባለሀብቶች ለኢንቨስትመንት ሥራቸው የሚያስፈልግ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት መሆን እንዲችሉ ፈቃድ ሰጥቷል። የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች የሚባሉት መሬት፣ ቤት እና ሕንፃ ሲሆኑ በኢትዮጵያ ሕግ በግል ባለቤትነት የሚያዙት የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ቤት እና ሕንፃ ናቸው።
በዚሁም መሰረት የውጭ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ለኢንቨስትመንት ሥራቸው የሚያስፈልግ የሕንፃ ባለቤት እንዲሆኑ አዋጁ ፈቅዷል። ረቂቅ ሕጉ የመኖሪያ ቤት ባለቤትነትን በተመለከተ ልዩ ድንጋጌ ያስቀመጠ ሲሆን፤ ይኸውም ከፍተኛ መጠን ያለው ኢንቨስትመንት ያላቸው የውጭ ባለሀብቶች የአንድ መኖሪያ ቤት ባለቤት እንደሚሆኑ ይደነግጋል።
ድንጋጌው የውጭ ባለሀብቶች ኢንቨስትመንታቸውን ለማስፋፋትና በአገሪቱ ውስጥም እምነት ጥለው መዋዕለ ነዋያቸውን እያፈሰሱ እንዲሰነብቱ የሚያደርግ መሆኑ ይታመናል። በተለይም የሪል ስቴት፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችና የመኖሪያ መንደር ግንባታዎች ያላቸው ሰፋፊ ኢንቨስትመነቶች ከዚህ ማዕቀፍ ተጠቃሚ መሆናቸው አይቀርም።
ይሁንና የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን የተቀመጠው “ከፍተኛ መጠን ያለው ኢንቨስትመንት” የሚለው መስፈርት አገላለጹ ለትርጉም የተጋለጠ እንዳይሆን፤ ለአሰራር እንቅፋት እንዳይፈጥርና ለመንግስት አካላት ያልተገባ ጥቅም ማግኛ ቀዳዳ እንዳይሆን በአዋጁ ወይም ይወጣል በተባለው ደንብ ውስጥ በግልጽ መቀመጥ ይኖርበታል።
ቻይናውያንና ቱርካውያን የጉልበት ሠራተኞችና አሽከርካሪዎችስ?
ሌላው የአዋጁ መሰረታዊ ጉዳይ የውጭ ዜጎችን የሥራ ቅጥርና ፈቃድን የተመለከተው ነው። እርግጥ ነው ከኢንቨስትመንት ዓላማዎች መካከል አንደኛው ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር በመሆኑ በኢንቨስትመንት ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ኢትዮጵያውያንን እንዲቀጥሩ ይጠበቃል።
ይሁንና ለሥራዎቹ አስፈላጊው የትምህርት ዝግጅት፣ ልምድና ችሎታ ያላቸው ኢትዮጵያውያን አለመገ ኘታቸው ሲረጋገጥ ኢንቨስተሮች በተቆጣጣሪነት፣ በአሰልጣኝነትና በሌሎች የቴክኒክ ሥራዎች ላይ የሚሰማሩ የውጭ አገር ዜጎችን መቅጠር እንዲችሉ አዲሱ ሕግ ይፈቅድላቸዋል።
እንዲሁም ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ የኦፕሬሽን ኃላፊና የፋይናንስ ኃላፊን ጨምሮ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት የሆኑ የውጭ ዜጎችን እንደ አስፈላጊነቱ መቅጠር እንዲችሉም ተፈቅዷል። በተጨማሪም የባለሀብቱ ወይም የሥራ ፈቃድ የተሰጠው (የተሰጣት) የውጭ ዜጋ የትዳር አጋር የሥራ ፈቃድ ሊሰጣት (ሊሰጠው) እንደሚችልም ሕጉ ያስቀምጣል።
ይህ ፈቃድ ግን ገደብም አለው። ከከፍተኛ የማኔጅመንት ሥራዎች ውጪ ያሉ የሙያ ወይም የቴክኒክ የሥራ መደቦች ላይ የተቀጠሩ የውጭ ዜጎች በተወሰነ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያውያን እንዲተኩ ግዴታ ተቀምጧል። ይህን ለመፈጸም ታዲያ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞችን በመመልመል የማሰልጠን ግዴታ በኢንቨስተሮች ላይ ተጥሏል።
ይህንን ኢትዮጵያውያንን የማሰልጠን ግዴታ ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ ደግሞ ለውጭ ዜጎች የሚሰጥ የሥራ ፈቃድ ዕድሳት ከማሰልጠን ጋር በተያያዘ ከተከናወኑ ተጨባጭ ሥራዎች ጋር እንዲያያዝ መደረጉ የአዋጁ በጎ ጎን ነው። ይሁንና “በተወሰነ ጊዜ ውስጥ” የሚለው አገላለጽ ግልጽነት የጎደለውና ለአዋጁ አተገባበርም እንቅፋት ስለሚሆን ከወዲሁ ተስተካክሎ መቀመጥ ይኖርበታል።
ይህ ድንጋጌ በአግባቡ በሥራ ላይ የሚውል ከሆነ በወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ግቦች ላይ እመርታዊ ለውጥ ለማስመዝገብ እንደሚያስችል እሙን ነው። የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግርም ያመጣል። ይሁንና ድንጋጌው ሌሎች መሰረታዊ ጉዳዮችንም ማካተት ይኖርበታል።
እርግጥ ነው የድንጋጌው ዓላማ የውጭ ዜጎችን የሥራ ቅጥርና ፈቃድን የተመለከተ ነው። ይሁንና በአሁኑ ወቅት በውጭ ኢንቨስትመንቶች (በተለይ በባቡር፣ በመንገድና በሕንፃ ግንባታ ላይ) ኢትዮጵያውያን ሊያከናውኗቸው የሚችሉ የጉልበት ሥራዎችን ጨምሮ የአሽከርካሪነትና ሌሎች የውጭ ዜጎችን የተለየ የቴክኒካል እውቀትና ልምድ የማይጠይቁ ሥራዎች ሁሉ ሳይቀሩ በውጭ ዜጎች ሲሠሩ እየተመለከትን ነው።
ስለሆነም ባለሀብቶች ከተቆጣጣሪነት፣ ከአሰልጣ ኝነትና ከሌሎች የቴክኒክ ሥራዎች፤ ከዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ ከኦፕሬሽንና ከፋይናንስ ኃላፊ እንዲሁም ከከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት ውጪ ያሉ ሥራዎችን ኢትዮጵያውያንን በመቅጠር እንዲያሠሩ ግዴታ የሚጥል ግልጽ ድንጋጌ በአዋጁ ውስጥ መካተት ይኖርበታል።
ባለሀብቶች የውጭ ብድር እንዲያገኙ የመፈቀዱ በጎ ጎኖችና ስጋቶቹ
በውጭና የአገር ውስጥ ኢንቨስትመንቶች መካከል ትስስርን ማስፋት እንዲሁም የውጭ ካፒታል በመጠቀም የአገር ውስጥ ባለሀብቶችን ተወዳዳሪነት ማሳደግ የሚሉት አዲሱ አዋጅ በዓላማነት ከሰነቃቸው ጉዳዮች ውስጥ ይጠቀሳሉ።
ይህንን ዓላማ ለማሳካት ታዲያ ሕጉ ማንኛውም ባለሀብት ለኢንቨስትመንቱ የሚያስፈልገውን ብድር ከውጭ አገር አበዳሪዎች እንዲወስድ ፈቃድ ሰጥቷል። ከዚህም ሌላ ማንኛውም የውጭ ባለሀብት ለኢንቨስትመንቱ ዓላማ የሚውል የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ባንኮች መክፈት ይችላል። ይህ ዓይነቱ ዕርምጃ ከዚህ ቀደም በአገሪቱ የኢንቨስትመንት ሕግ ማዕቀፎች ያልተለመደ በመሆኑ የመነጋገሪያ ጉዳይ መሆኑ አልቀረም።
እርግጥ ነው ኢንቨስተሮች በራሳቸው መንገድ ለኢንቨስትመንታቸው የሚያስፈልጋቸውን ብድር ከውጭ አበዳሪዎች እንዲያገኙ ፈቃድ መሰጠቱ በአንድ በኩል በአገሪቱ ውስጥ በየጊዜው እየተከሰተ ኢኮኖሚውን ቅርቃር ውስጥ የሚከተውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመፍታት እንደሚያግዝ ግልጽ ነው።
በሌላ በኩልም የውጭ ምንዛሬ በዋናነት መንግሥት ብቻውን የተበዳሪነት ሸክሙን በጫንቃው ተሸክሞ የሚያመጣው በመሆኑ ይህንን ሸክሙን ያቀልለታል። በአገር ውስጥ ባለሀብቶች ዘንድ የሚፈጠረውን የኢንቨስትመንት ካፒታል ውስንነትንም እንደሚቀርፍ ይታመናል።
ይሁንና ይህ ዓይነቱ አካሄድ በአግባቡ ካልተመራ አጠቃላይ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውን አደጋ ላይ መጣሉ አይቀርም። ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ታዲያ አዲሱ አዋጅ የውጭ ብድር መውሰድ የሚፈልግ ባለሀብት የብድር ስምምነት ከመዋዋሉ በፊት ለብሔራዊ ባንክ በማቅረብ ማስፈቀድና አግባብነት ባለው መመሪያ መሠረት ማስመዝገብ እንዳለበት ግዴታ መጣሉ በበጎ ጎኑ የሚታይ ነው።
በደህና እንሰንብት!

አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 22/2012
በገብረ ክርስቶስ