ሰቆጣ:- በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በ2011-2012 የምርት ዘመን በተለያዩ ሰብሎች አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በተወሰኑ የዞኑ ወረዳዎች ቢዘንብም ከፍተኛ የሚባል ተጽዕኖ እንደማይኖረውም ገልጿል።
የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ገበየው ወርቁ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፣ በምሥራቅ አማራ በቂ ዝናብ እንደማይኖር ሜትሮሎጂ ቀድሞ በተነበየው መሰረት እጥረቱ ቢኖርም በተወሰኑ ወረዳዎች ግን የተሻለ ዝናብ በመኖሩ ጥሩ የእርሻ ሥራ ተከናውኗል። ምርት ሙሉ ለሙሉ ተሰብስቦ እስኪገባ ድረስ እርግጠኛ መሆን ባይቻልም በምርት ዘመኑ ለመሰብሰብ በዕቅድ የተያዘውን አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ኩንታል ለማሳካት ምርት የመሰብሰብ ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።እስካሁንም ከ60 በመቶ በላይ ምርት ተሰብስቧል።
እንደ አቶ ገበየው ገለጻ፣ በአካባቢው የአን በጣ መንጋ ተከስቶ ስለነበር ያንን ለመከላከል የተማሪዎችን ጉልበት በመጠቀም ጭምር ምርት የመሰብሰብ ሥራ ተከናውኗል። ምርት የመሰብሰቡ ሥራም በታህሣሥ አጋማሽ ላይ ይጠናቀቃል። በምርት ዘመኑ በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች ጋዝጊብላ፣ ደሃና፣ አበርገሌ፣ ሰቆጣ በከፊል እና ጻግቢጂ ወረዳ ውስጥ ሶስት ቀበሌዎች የተሻለ ዝናብ አግኝተዋል።
ሰሐላ ወረዳ በክረምቱ ለሶስት ቀናት ብቻ ነው ዝናብ ያገኘው።ዝቋላ ወረዳም ውስጥ ከአራት ቀበ ሌዎች በስተቀር አብዛኞቹ በተመሳሳይ እጥረት አጋጥ ሟቸዋል። በእነዚህ አካባቢዎች የታዩት ችግሮች በምርት ዘመኑ ዕቅድ ላይ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ይጠበቃል።
ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሌሎቹ የክልሉ አካባቢዎች በሚያሰጋ ሁኔታ ባያጋጥምም በዞኑ ደጋማው አካባቢ በሚገኙ ወረዳዎች በጋዝጊባላና ጻግቢጂ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ መዝነቡን የጠቆ ሙት አቶ ገበያው፣ ችግሩ ከፍተኛ አለመሆኑን አመል ክተዋል። በዞኑ በ2010/2011 የምርት ዘመን ዝናቡ ከፍተኛ እንደነበር፣
በረዶና ተባይ ተጨምሮበት ምርቱን በከፍተኛ ሁኔታ እንደቀነሰውም ጠቁመዋል። አቶ ገበያው እንዳሉት፣ የዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ከሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ዝናብ አጠር እንደሆነ ይታወቃል። ይሁን እንጂ የእንስሳት ሀብት ባለቤት ነው። በእንስሳቱም ሆነ በሰብሉ የተሻለ ገበያ አግኝቶ በሀብቱ ተጠቃሚ ለመሆን የመሰረተ ልማት አለመሟላት ወደኋላ እንዳስቀረውና ከተረጅነትም እንዳይላቀቅ እንዳደረገው ኃላፊው ይገልጻሉ።
አዲስ ዘመን ህዳር 25/2012
ለምለም መንግሥቱ