የፀሀይ መውጣትና መግባት ዛሬን ለነገ እያቀበለ፤ ወቅቶችንም እያፈራረቀ በሰው ልጅ ተለክቶ ከተቀመጠው ዓመት ይደርሳል። አንደኛው ዓመት ሲብትም ሌላኛው ይጠባል፤ እንዲህ እንዲህ እያለም የሰው ልጅ ዕልፍ ዓመታትን ዘልቋል። ተፈጥሮ ለየፍጥረታቱ የተለያየ ጣዕም መስጠቷ፤ እዚህ ሲመሽ እዚያ እንዲነጋ አድርጓልና በእኛ መኸር ሌላው ዓለም አዲስ ዓመቱን ይቀበላል። በጎርጎሮሳዊያኑ የዘመን ቀመር መሰረትም ዛሬ ከሰዓታት በኋላ አንድ ዘመን ተጠናቆ ሌላኛው ይተካልና ለሚያከብሩት እንኳን ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ መልካም ምኞታችን ነው።
የፈረንጆቹ 2018 ቆጥሮ የተረከባቸውን ቀናት ለ2019 ሊያስረክብ ሰዓታት ብቻ ቀርተውታል። ከዚያ በፊት ግን በዓመቱ በዓለም ዙሪያ ከሆኑት ጥቂት የማይረሱ ጉዳዮችን ማስታወስ ይገባልና እነሆ። በፖለቲካው ዘርፍ የሁለቱ ኮሪያዎች ሰላማዊ መንገድን መከተል በዓመቱ ከታዩ ስኬታማ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳል። የክረምቱ ኦሊምፒክ ለሰላም መስፈን ምክንያት በመሆኑም በታሪክ ሲዘከር ይኖራል። የሰላዩ ሰርጊ ስክሪፓልና የልጁ ጉዳይም ሩሲያንና እንግሊዝን ፍጥጫ ውስጥ የከተተ ነበር። የሩሲያዊው ፕሬዚዳንት ለአራተኛ ጊዜ መመረጥ፣ የአሜሪካ ከኢራን ኒኩሌር ስምምነት መውጣት እንዲሁም የሳውዲ አረቢያው ጋዜጠኛ ግድያም ዓለምን በእጅጉ ያነጋገረ ጉዳይ ነው።
በጦርነት የሚማቅቁት ሶሪያዊያን አሁንም ስደትና ሞት እጣ ፋንታቸው ሲሆን፤ የመናዊያኑም በነበሩበት ሁኔታ ቀጥለዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህጻናት ምድሪቷን ሲቀላቀሉ በዚያው ልክ የሚሆኑት ቦታቸውን ለመጪዎቹ አስረክበው ወደማይቀረው ዓለም ሄደዋል። ከእነዚህ መካከልም የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ ኮፊ አናን፣ የፊዚክስ ሊቁ ስቴፈን ሃውኪንግ፣ … ተጠቃሽ ናቸው። ከበጋው ኦሊምፒክ ባሻገር የሩሲያው ዓለም ዋንጫም ስፖርታዊ ክንውኖች ናቸው። አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ሲተገበሩ በሳይንስና በሌሎች ዘርፎች ልቀው የተገኙ ለሽልማት በቅተዋል፤ በሰሩት ወንጀል ወህኒ የተበረከተላቸውም ብዙዎች ናቸው።
በየቀኑ አዲስ ክስተት የምታሳየው ዓለም ከዚህ በኋላም በርካታ ክፉና ደግ ነገሮችን ማስተናገዷ አይቀርም። ዛሬ በዋዜማው ላይ ሆነንም አዲሱ ዓመት መልካም መልካሙን የምንሰማበትና የምናይበት እንዲሆን ተመኝተን በዓሉ ላይ ትኩረታችንን እናድርግ። አዲስ ዓመትና ከሳምንት በፊት የሚያከብርበት የገና በዓል በፈረንጆቹ ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው ነው። በመሆኑም አከባበሩና ዝግጅቱ ረጅም ጊዜ ይወስዳል። መኖሪያ ቤቶች፣ የገበያ አዳራሾች እንዲሁም መስሪያ አካባቢዎችም ሳይቀር በመብራቶች፣ በገና ዛፎች እንዲሁም ለበዓሉ ድምቀት ሊሰጡ በሚችሉ ቁሳቁሶች ይደምቃል። በዓላት እንደየሃገሩ እና እንደየባህሉ በተለያዩ መንገዶች ይከበራልና በወፍ በረር የጥቂት ሃገራትን የበዓል አከባበር እንመልከት።
በግሪጎሪያን የቀን አቆጣጠር በምትመራው እንግሊዝ ዕለቱ የቤተሰብ አባላት ተሰባስበው ያሳልፉታል። «ቢግ ቤን» ብለው የሚጠሩት ግዙፉ ሰዓት የመጨረሻዎቹን 12 ሰከንዶች ቆጥሮ ሲጨርስ የለንደን ሰማይ በርችት ይደምቃል። የቤተሰብ አባላት ለበዓሉ የተዘጋጁ ምግብና መጠጦችን እየተቃመሱ ሞቅ ባለ መልኩ ያከብሩታል። በባህላቸው መሰረት በዕለቱ ወደቤት የሚገባው በፊት ለፊት በር ቢሆንም የሚወጣው ግን በኋላ በር ነው።
የራሳቸው የሆነ ባህል የሌላቸው አሜሪካዊያን ደግሞ ጣፋጭ ምግቦችን በማዘጋጀትና ወይን እና ሻምፓኝ የመሳሰሉ መጠጦችን በመጎንጨት ዕለቱን ያከብራሉ። ከዚህ ባሻገር በቤተሰብና ዘመድ አዝማድ መካከል የእግር ኳስና ሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮችንም ያከናውናሉ። ዴንማርካዊያን ከእኛ ጋር የሚቀራረብ የአዲስ ዓመት አቀባበል ልማድ አላቸው። «ጎመን ምንቸት ውጣ፤ የገንፎ ምንቸት ግባ» እንደሚባለው፤ በዋዜማው(በዛሬው ዕለት) ዓመቱን ሙሉ የተጠቀሙባቸውን ድስቶች ሰብስበው በራቸው ፊት ለፊት ይወረውራሉ፤ የተሰባበሩትን በመተውም ያልተሰበሩትን በዓመቱ እንዲቀጥሉ ያደርጋሉ። አዲሱን ዓመት የሚቀበሉትም በመጨረሻዎቹ 12 ሰከንዶች ወንበር ላይ ቆመው በመዝለል ነው።
በሉናር የቀን አቆጣጠር የሚመሩት ቻይናዊያን፤ አዲስ ዓመትን «ዩአን ታን» ብለው ይጠሩታል። በዕለቱ ከበሮ መሰል ታምቡር በመምታት ሴጣንን የማባረር ስርዓት የሚካሄድ ሲሆን፤ የቤተሰብ አባላትና ጓደኞችም በቀይ ማሸጊያ የተሸፈነ ስጦታ በመለዋወጥ በዓሉን ያሳልፋሉ። በቻይናዊያኑ ዘንድ የአዲስ ዓመት ክብረ በዓል ረጅም ሲሆን፤ ከ10-15 ለሆኑ ቀናት ይቆያል።
ጃፓን እስከ 1873 ድረስ በቻይናዊያኑ የዘመን ቀመር ስትመራ ቆይታ፤ ወደ ግሪጎሪያን የዘመን አቆጣጠር የቀየረች ሃገር ናት። ጃፓናዊያን ዕለቱን ወደ ሃይማኖት ስፍራዎች በመሄድ መልካም ዓመት እንዲሆንላቸው የሚጸልዩ ሲሆን፤ ለ180 ጊዜያት በመደወልም ሰይጣንን የማባረር ስነ-ስርዓት ያካሂዳሉ። ቤታቸውን በማሰማመርም «ሞቺስ» በመባል የሚጠራውን ከሩዝ የተዘጋጀ ኬክ ይመገባሉ።
ጀርመናዊያን የቀለጠ ብረት በውሃ ውስጥ በማንጠባጠብ ከሚሰጠው ቅርጽ አዲሱን ዓመት ይተነብያሉ። ዓመቱ በሚቀየርበት እኩለ ሌሊት ላይም ቤተሰብ ሁሉ በአንድ ተሰብስቦ መልካም ምኞታቸውን በመለዋወጥ የአዲስ ዓመት በዓልን ያከብራሉ። ስፔናዊያን ደግሞ አዲሱ ዓመት ሊበሰር በሚቀሩት 12 ሰከንዶች 12 የወይን ፍሬዎችን አንድ በአንድ ቶሎ ቶሎ በመመገብ ይቀበሉታል። ይህንን የሚያደርጉትም መልካም እድል እንደሚገጥማቸው በማመን ነው።
ኢትዮጵያን ከመሳሰሉ ጥቂት የዓለም ሃገራት በቀር የአብዛኛዎቹ የዘመን አቆጣጠር ተመሳሳይ በመሆኑ፤ በሰዓታት ልዩነት አዲስ ዓመትን ይቀበላሉ። እኛ ባናከብረውም ግን እኛን ያሉና መዳረሻቸውን ኢትዮጵያ ያደረጉ በርካታ የውጪ ሃገራት ዜጎችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ይገኛሉና፤ አዲሱ ዓመት መልካም ነገሮችን የሚያገኙበት እንዲሆን በድጋሚ እንመኛለን።
አዲስ ዘመን ታህሳስ 22/2011
ብርሃን ፈይሳ
Your positivity and optimism are contagious It’s impossible to read your blog without feeling uplifted and inspired Keep up the amazing work
Your writing style is so engaging and easy to follow I find myself reading through each post without even realizing I’ve reached the end
Your blog post was fantastic, thanks for the great content!
Your passion for what you do shines through in every post It’s truly inspiring to see someone doing what they love and excelling at it
Looking forward to your next post. Keep up the good work!
I always look forward to reading your posts, they never fail to brighten my day and educate me in some way Thank you!
Your ideas and insights are unique and thought-provoking I appreciate how you challenge your readers to see things from a different perspective
This is exactly what I needed to read today Your words have given me a new perspective and renewed hope Thank you
I couldn’t stop scrolling and reading, your content is truly one-of-a-kind. Thank you for all the time and effort you put into creating such amazing content.
Your blog always puts a smile on my face and makes me feel better about the world Thank you for being a source of light and positivity
Your blog is a ray of sunshine in a sometimes dark and dreary world Thank you for spreading positivity and light
Your blog is an oasis in a world filled with negativity and hate Thank you for providing a safe space for your readers to recharge and refuel
I admire how this blog promotes kindness and compassion towards ourselves and others We could all use a little more of that in our lives
I always leave this blog feeling inspired and motivated to make positive changes in my life Thank you for being a constant source of encouragement
I just wanted to take a moment to say how much I appreciate your blog posts. They’re always well-written, informative, and keep me coming back for more. Keep up the great work!
Your blog has quickly become one of my favorites I always look forward to your new posts and the insights they offer
Your blog stands out in a sea of generic and formulaic content Your unique voice and perspective are what keep me coming back for more
Главные новости мира https://ua-vestnik.com и страны: политика, экономика, спорт, культура, технологии. Оперативная информация, аналитика и эксклюзивные материалы для тех, кто следит за событиями в реальном времени.
Your photography and visuals are always so stunning They really add to the overall quality of the content