![](https://press.et/wp-content/uploads/2019/10/Untitled-63.png)
የደቡባዊ አፍሪካ አገራት የልማት ኮሚኒቲ አስራ ስድስት አባል አገራትን የያዘ ሲሆን በተያዘው የፈረንጆቹ ጥቅምት ወር መጨረሻ በሚያደርገው ስብሰባው በዚምባቡዌ ላይ በአውሮፓ ህብረትና በአሜሪካ የተጣለውን ማዕቀብ በመቃወም መግለጫ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአልጀዚራ ዘገባ ያሳያል። እአአ 2017 ላይ ለ38 ዓመት አገሪቱን ሲመሩ የነበሩት ሮበርት ሙጋቤ ስልጣን ከለቀቁበት ወቅት ጀምሮ ማዕቀቡ ዚምባቡዌ ላይ ተጥሎ ቆይቷል። የአውሮፓ ህብረት ማዕቀብ የጦር መሳሪያ ላይ፣ የንብረት ማንቀሳቀስና የጉዞ እገዳን ያካትታል። የአሜሪካ ማዕቀብ ደግሞ የገንዘብ እንቅስቃሴ እና በተመረጡ ባለስልጣናት ላይ የመንቀሳቀስ ገደብን ያካትታል።
ሮበርት ሙጋቤ አመጽ ከተደረገባቸው በኋላ በፍጥነት ወደ ዴሞክራሲ በመመለስ የተጣሉት ማዕቀቦች ይነሳሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር። የሙጋቤ ተተኪ ኤመርሰን ማናጋግዋ ግን ከሙጋቤ የበለጠ አምባገነን መሪ መሆናቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። በዚህ የተነሳም በእሳቸው ላይ ከኢኮኖሚያዊ ቀውስ የሚመነጭ ፀረ-መንግስት ተቃውሞዎች እየተበራከቱ ይገኛሉ። ለምሳሌ እአአ 2018 ነሐሴ ወር እና 2019 ጥር ወር ላይ ወታደሮች ሰላማዊ በሆኑ የፀረ-መንግስት ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በወሰዱት እርምጃ በርካታ ዜጎች እንደገደሉ ማስታወስ በቂ ነው። በምላሹም አሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት ቀደም ሲል በሀገሪቱ ላይ የጣሏቸውን ማዕቀቦች ማራዘማቸው እና የማናጋግዋ መንግስት የተቃውሞ ሰልፎችን እና የመገናኛ ብዙሀን ነፃነት የሚገድቡ ህጎችን እስኪያነሱ ድረስ ሁሉንም ማዕቀቦች ላለማንሳት ቃል ገብተዋል።
የደቡባዊ አፍሪካ አገራት የልማት ኮሚኒቲ “ህገ-ወጥ ማዕቀቦች በዚምባብዌ ኢኮኖሚ እና በክልሉ በአጠቃላይ አሉታዊ ተፅእኖ አላቸው” ብሏል። በአገሪቱ ውስጥ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ መልሶ ማቋቋም አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል። ሆኖም የደቡባዊ አፍሪካ አገራት ልማት ኮሚኒቲ ማዕቀቦቹን በመቃወም ላይ የሚገኘው የዜምባብዌያዊያን ዲሞክራሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት አሳስቦት እንዳልሆነ ይነገራል። የዚምባብዌያዊያን የአፍሪካ ብሔራዊ ህብረት – የአርበኞች ግንባር (ዜን-ፒኤፍ) የጭካኔ እንቅስቃሴዎችን ለመደበቅ ፍላጎት ስላለው እንደሆነ ይነገራል። የደቡባዊ አፍሪካ አገራት የልማት ኮሚኒቲ ተቃዋሚዎችን በማነሳሳት እና የዚምባብዌን መሠረታዊ የሆኑ ህገ-መንግስታዊ መብቶች ችላ ብሎ በማለፉ ሐራሬ የብጥብጥ አውድማ ከሆነች ሰነባብታለች። “ውጭ ባሉ ኃይሎች እየተደገፉ የሚገኙት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም” አገሪቱን አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
የደቡባዊ አፍሪካ አገራት የልማት ኮሚኒቲ አመራሮች በዚምባብዌ በመንግሥት ለተፈፀሙ ኃይል የተቀላቀለበት ድርጊቶች ተደጋግሞ ሲከሰቱ ለውጥ ባያመጣም የተወሰነ ምላሾች ሰጥተዋል። የዚን-ፒኤፍ ማንኛውም ተቃዋሚዎች ከውጭ ጣልቃ ገብነት የተገኙ ናቸው። የዚምባብዌ ዜጎች ተራማጅ አስተሳሰብን መቀበል እና ለእራሳቸው ቀላል ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማድረግ አይችሉም የሚል እምነት አለው።
አሁን በአገሪቱ ያለው ሁኔታ ዴሞክራሲያዊ ተቃራኒ የሆነ ነገር ለመፍጠር የውጭ ሀገር ድጋፍ ማግኘት፣ ለመለያየት በፖለቲካዊ ሁለትዮሽ መበታተን መፍጠር እና የዚምባብዌ ዜጎች ሙሉ የነፃነት እና የሕገ-መንግስታዊ ነጻነቶችን የማግኘት መብትን መካድ ነው። በተጨማሪም የደቡባዊ አፍሪካ አገራት የልማት ኮሚኒቲ የዚምባብዌን ውስብስብ ችግሮች ምንጭ የመረዳት አቅሙ በጣም አናሳ ነው። የዚምባብዌ ባለ ብዙ ገጽታ ያላቸው ችግሮች ከመቼውም ጊዜ የበለጠ እየጨመረ ካለው የፖለቲካ ሙቀቱ ጋር አድገዋል። የደቡባዊ አፍሪካ አገራት የልማት ኮሚኒቲ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቆጣጠር ወይም ለመፍታት ጠንካራ እና ተለዋዋጭ አካሄድ አልተከተለም።
የደቡባዊ አፍሪካ አገራት ልማት ኮሚኒቲ በቅርብ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሀይል እርምጃዎች ሲወሰዱ ያደረገው ነገር ምንድነው? የሰብአዊ መብት ተሟጋች ታትዳ ማማቤራራ፣ የኤ.ዲ.ኤን. የወጣቶች መሪ ፕሪንግ ካንቶንጋ፣ ኮሜዲያን ሳማንታ “ጎንዬይ” ኪራያ እና የዚምባብዌ ሆስፒታል የዶክተሮች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ፒተር ማጊቤይ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ታፍነው ተወስደዋል። የደቡባዊ አፍሪካ አገራት የልማት ኮሚኒቲ በፖለቲካ ተነሳሽነት የተያዙ ሰዎችን ወይም ሌሎች ባልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመ ወንጀል በግልጽ አያወግዝም።
የደቡባዊ አፍሪካ አገራት ልማት ኮሚኒቲ በተሻሻለው እና በሂደታዊው “ሁለተኛ ሪፐብሊክ” ከሚመሰረተው አምባገነናዊ መንግስት ጋር በይፋ እና በቋሚነት ገንዘብ በመመደብ በዜምባብዌ ውስጥ ካለው “የወንድማማች” ፖለቲካ በማጠናከር፣ የመገናኛ ብዙሃን እና የፀጥታ ጉዳዮች ማሻሻያ እውን የማድረግ አስፈላጊነት እየፈጠረ ይገኛል። እናም የዛኑ ፒ ኤፍ ውድቀቶች የመንግስት ሴክተር ብልሹነት እና አጠቃላይ ብቃት የጎደለው አሰራር እንዲያስተካክል ግፊት እየተደረገበት ይገኛል። በዋና ኦዲተር ጄኔራል ሚድሬድ ቺሪ እ.ኤ.አ. 2019 በሰኔ ወር የታተሙ የተለያዩ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት በመንግስት አካላት፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና በአካባቢ ባለስልጣናት በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ባክኗል። በእርግጠኝነት የምዕራባውያን ኃይሎች የዚምባብዌ መንግሥትን የሚጠይቁት ነገር በህዝቡ ላይ ለውጥ የሚያመጣ ነገር አይደለም። ነገር ግን የዚምባብዌ የሰብአዊ ፍላጎቶች፣ ነፃነቶች እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎች ሁልጊዜ እንዲካሄዱ ይፈልጋሉ። ስለዚህ ማንኛውም ሰው የዚምባብዌን መንግስት መተቸት ካለበት የደቡባዊ አፍሪካ አገራት የልማት ኮሚኒቲ አባ መሆን አለበት ።
አዲስ ዘመን ጥቅምት 10/2012
መርድ ክፍሉ