ለአንድ ሀገር ኢንቨስትመንት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። ሀገሮችም ለእዚህ የኢኮኖሚ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ይሰራሉ።በተለይ የሥራ እድል በመፍጠር፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በማሳደግ ፣የቴክኖሎጂና እውቅት ሽግግር በመሳብ በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
ኢትዮጵያም ለእዚህ ዘርፍ በከፍተኛ ትኩረት ቆይታለች። ሁሉም ክልሎች እንዲሁም ከተማ አስተዳደ ሮች ለዘርፉ የተለያዩ ማበረታቻዎችን በማዘጋጀት ባለሀ ብቶችን በመሳብ ተጠቃሚ ለመሆን እየሠሩ ናቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢንቨስትመንት ኮሚሽንም ከተማዋ ያላትን ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ በመጠቀም እንዲሁም የተለያዩ ማበረታቻዎችን በማዘጋጀት ባለሀብቶች በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ እንዲሰማሩ እያደረገች ትገኛለች። ሀገሪቱ ባለፉት ዓመታት የሰላም እና መረጋጋት ችግር ቢስተዋልባትም ከተማዋ ግን አንጻራዊ በሆነ መልኩ የባለሀብቶች ፍላጎት ሆና ቆይታለች። በእነዚህ ዓመታትም የከተ ማዋ የኢንቨስትመንት ፍሰት መጨመሩን የከተማዋ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ይገልጻሉ። ከተማዋ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎር ሜሽን አሳካዋለሁ ያለችውን ግብም ከወዲሁ እያሳካች መሆኗን ይናገራሉ።
ከተማዋ ምንም እንኳ የቦታ እጥረት ለዘርፉ ትልቅ ማነቆ ቢሆንም በጠባብ ቦታ ሰፊ የሥራ እድል የሚፈጥሩ እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚስቡ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን በመምረጥ እየሰራች መሆኗን ኮሚሽነሩ ጠቅሰው፣ያለውን መሬት በአግባቡ ለመጠቀም እየተሠራ ነው ይላሉ።
ከአቶ አብዱልፈታ ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
አዲስ ዘመን፡- እንደሚታወቀው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ርቋት ቆይቷል።ይህም በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ላይም አሉታዊ ተጽእኖ አሳድሮ ቆይቷል። የአዲስ አበባ ከተማ ግን ከሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች አኳያ ስትታይ አንጻራዊ በሆነ መልኩ ሰላምና መረጋጋት አልራቃትም። ከዚህ አኳያ ከተማዋ ተጠቃሚ ሆናለችና በኢንቨስትመንት በኩል ባለፉት ዓመታት ምን ያህል ተጠቃሚ ሆናለች ?
አቶ አብዱልፈታ፡- ከተማዋ እንደሚታወቀው የሀገሪቱ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ መዲና እንዲሁም የዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ ናት።ባለፉት ጊዜያት በተለይ ከ2006 እና 2007 ጀምሮ ሀገሪቱ በከፍተኛ አለመረጋጋት ውስጥ ቆይታለች።በተለይ ከ2007 ምርጫ በኋላ በየክልሎቹ አመጾች ተከስተዋል፤ይህም ውድመቶችን አስከትሏል። አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዚህ አንጻር እንደተጠቀሰው አንጻራዊ በሆነ መልኩ ሰላምና መረጋጋቷን ጠብቃ ቆይታለች።
ሰላምና መረጋጋት ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ከፍ ተኛ ፋይዳ ይኖረዋል። በዚህ ረገድ ከተማዋ ሰላምና መረጋጋት የታየባት መሆኑ እንዲዚሁም የኢኮኖሚና የፓለቲካ ማእክል መሆኗ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንድትሆን አርገዋታል።በርካታ ኢንቨስተሮች በየክልሉ በኢንቨስትመንታቸው ላይ አደጋ ሲከሰትና ስጋት ሲያድ ርባቸው ሰላምና መረጋጋት ወደአለበት አካባቢ መሂድን ይመርጣሉ ። በዚህ የተነሳም አዲስ አበባ ላይ ከፍተኛ የሆነ የኢንቨስትመንት ፍላጎት እየታየ ነው።
የከተማዋ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በመሰረታዊነት አሳካቸዋለሁ ያላቸው ግቦች አሉት። ከእነዚህ ውስጥ አንዱና የመጀመሪያው ኢንቨስትመንቱን በማስፋፋት የሀገራችንን ሥራ አጥ ቁጥር እንዲቀንስ ማድረግ የሚለው ነው። በሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት አለ።ይህን እጥረት ሊቀንሱ የሚችሉ የኢንቨስትመንት መስኮችን ማስፋፋት ሌላው ነው።በከተማችን ያለው የኢንቨስትመንት ፍላጎት ከፍተኛ ቢሆንም እነዚህንና የመሳሰሉ አላማዎችን ሊያሳኩ በሚችሉ ዘርፎች ላይ ቅድሚያ ሰጥተን እየሰራን ነው።
ከተማዋ የተረጋጋችና ሰላማዊ በመሆኗ ከሌሎች አካባቢዎች አንጻር ሲታይ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ሆናለች።
አዲስ ዘመን፡- ተመራጭ ከመሆኗ ጋር በተያያዘ ለታየው የኢንቨስትመንት ፍሰት አብነት ቢጠቅሱልኝ ?
አቶ አብዱልፈታ፡-ኮሚሽኑ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የኢንቨስተሮችን ቁጥር ከነበረ በት 40 ሺ ወደ ሀምሳ ሺ ለማድረስ አቅዶ ነበር። ስለዚህ በየዓመቱ የታየውን ፍሰት ስንመለከት ከአንድ ነጥብ አምስት በላይ እየጨመረ ነው የመጣው። ይህም ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዳችንን በከፍተኛ ደረጃ እያሳካን ስለመሆኑ ያመለክታል።
ያለፈውን ዓመት አፈጻጸም ብቻ ብንመለከት ከ2ሺ 500 በላይ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደዋል።እስከ አሁን ወደ 40 ሺ ኢንቨስተሮች የኢንቨስ ትመንት ፈቃድ ወስደው እየሰሩ ናቸው። በአጠቃላይ ሲታይ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ከአቀድነው በላይ እየሄደ ነው።
አፈጻጸሙ በሚፈለገው መስክ ከመምጣት አንጻር ውስንነት አለበት። የሚመጣው ኢንቨስትመንት ሰፊ መሬት የሚጠይቅ ነው። አዲስ አበባ ደግሞ እንደሚታወቀው ሰፊ የመሬት እጥረት ያለበት ከተማ ነው። መሬት የራሱ የሆነ ባውነደሪ አለው። ኢንቨስትመንት ደግሞ በአብዛኛው በመሬት ላይ የሚካሄድ ነው፤ በተለይ በታዳጊ ሀገሮች የሚካሄድ ኢንቨስትመንት በመሬት ላይ ጥገኛ ነው።
ስለዚህ ውስን መሬት ነገር ግን ሰፊ ሰራተኛ የሚቀ ጥሩ እና የውጭ ምንዛሬ የሚያሳድጉ ፣የውጭ ምንዛሬ ወጪን የሚያድኑ እና ቴክኖሎጂ እድገትን በሚያመጡ መስኮች ላይ ቅድሚያ ሰጥተን እየሰራን ነው።
አዲስ ዘመን፡- የመሬት እጥረቱን እንዴት መፍታት ይቻላል ብለው ያምናሉ?
አቶ አብዱልፈታ፡- እኛ አሁን ባለው ሁኔታ አንዱ መሰረታዊ ማነቆ አርገን የምንወስደው የመሬት እጥረትን ነው። ይህን የመሬት እጥረት ለመፍታት በአንድ በኩል ያሉትን ቦታዎች በቁጠባ እና አዋጭ በሆነ መስክ ላይ በማዋል ለመስራት እየተንቀሳቀስን ነው።የኢንቨስትመንት ተልእኮውን ሊያሳኩ በሚችሉ የሀገራችን መሰረታዊ ችግር የሚፈቱ ገበያውን የሚያ ረጋጉ ምርቶችንና አገልግሎቶችን እንደዚሁም የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ ዘርፎች ላይ ትኩረት አርገን እየሰራን ነው።
በአዲስ አበባ ላይ ከፍተኛ የሥራ ፈላጊ ቁጥር አለ። ስለዚህ ይህን ሊይዝ በሚችል የኢንቨስትመንት መስክ ላይ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ውስን መሬት በማቅረብ እንፈታዋለን።
ሰፊ ቦታ የያዙ የኢንቨስትመንት መስኮች ወደሌላ ቦታ እንዲሄዱ በማድረግም የመሬት ችግሩን ለመፍታት ይሰራል።
ከተማዋ በጣም ብዙ ህዝብ ይኖርባታል።ስለዚህ ብክለት የሚያስከትሉ የኢንቨስትመንት መስኮች ወደሌላ አካባቢ እንዲሄዱ ለማድረግ ከባለሀብቶች በጋራ ይሰራል። ይህን የማመቻቸት ሥራ ወደፊት የሚከናወን ይሆናል።
አዲስ ዘመን፡- ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄዱ ይሰራል ሲባል ምን ማለት ነው ?
አቶ አብዱልፈታ፡- ክልሎች አካባቢ ከፍተኛ የኢንቨስትመንተ ፍላጎት አለ።ስለዚህ ከክልሎች ጋር በመስራት በተለይ ሰፊ ቦታ የሚፈልጉ የኢንቨስትመንት መስኮች ወደ ክልሎች ጭምር ሄደው ሊያለሙ የሚችሉ በት እድል አለ።
እኛ በዋናነት ትኩረት አርገን እንሰራለን ብለን ያሰብነው በሆቴል እና በቱሪዝም መስክ ያሉ ኢንቨስመንት መስኮች ላይ ነው። በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍም እንዲሁ ብዙ ቦታ የማይጠይቁ ግን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ ዘርፎች አሉ። ለምሳሌ አይሲቲን በመጠቀም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ ምርቶችን ማምረት የሚያስ ችሉ ኢንቨስትመንቶችን መውሰድ ይቻላል።
አዲስ ዘመን፡- ከሥራ እድል ፈጠራው አኳያ የአንድ ዓመት ምሳሌ በመውሰድ የከተ ማዋ ኢንቨስትመንት ያስ ገኘው የሥራ እድል ምን ያህል እንደሆነ ቢጠቅሱልኝ?
አቶ አብዱልፈታ፡- ኢንቨስት መንት ከፍተኛ ማበረታቻ ያለው ዘርፍ ነው። በተለይ በማኑፋክቸሪንግ፣ በሆ ቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ኢንቨስት የሚያደርጉ ባለሀብቶች ከቀረጥ ነጻ አስፈላጊውን የማምረቻ መሳሪያ ማስገባት ይችላሉ። ስለዚህ ይህ ድጋፍ በመሰረታዊነት የሚሰጠው ህዝቡ ማግኘት የሚገባውን ገቢ መስዋእት በማድረግ ነው። ከሚገኘው ገቢም መልማት የሚችለ ውን ጭምር በመቆጠብ የሚሰጥ ማበረታቻ ነው።
ኢንቨስትመንቱ ደግሞ እያደገና እየተስፋፋ ሲሄድ ህብረተሰቡ ይጠቀማል በማለት ነው። ኢንቨስትመንት መሳሪያዎቹ ከቀረጥ ነጻ ሲገቡ፣ መሬት ካለሊዝ ውድድር በምደባ ሲያገኝ፣ ከባንክ ብድር ሲገኝ ወለድ ቅናሽ ሲኖረው ፣ወዘተ በቀጣይ የሚያሰገኘው ጥቅም ታሳቢ ተደርጎ ነው።
ኢንቨስትመንት ይፈታል ተብሎ የሚጠበቀው ትልቅ ችግር የሥራ አድል በማስገኘት የሥራ አጡን ቁጥር መቀነስ ሲያስችል ነው። ስለዚህ እኛም ከኢንቨስትመንት አማራጮች ውስጥ ሰፊ የሥራ እድል ለሚፈጥሩ መስኮች ዘንድሮ ቅድሚያ እንሰጣለን። በዚህ ረገድ ባለፈው በጀት ዓመት ብቻ ከ17ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል ተፈጥሯል።በዚህ ዓመት ከዚህ በላይ የሥራ እድል መፍጠር የሚቻልበት ሁኔታ ይኖራል።
ኢንቨስትመንት እየተስፋፋ ሲሄድ የሀገሪቱን የሥራ አጥ ቁጥር ይቀንሳል።ህብረተሰቡ ገቢ ያገኛል፤የመሸመት አቅሙ ይጨምራል።በድምሩ ሲታይ ደግሞ የከተማዋ ንም የሀገሪቱንም ገቢ የማሳደግ አቅሙ ከፍተኛ ይሆናል።
አዲስ ዘመን – ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው አዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት ያላትን እምቅ አቅም በመጠቀም ይበልጥ ለመስራት ያላችሁ ዝግጁነት ምን ይመስላል ?
አቶ አብዱልፈታ፡- የከተማዋ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በጣም ቀልጣፋ አገልግሎት ከሚሰጡ ተቋማት አንዱ ነው።ይህ ግብረ መልስ እኛ ያልነው ሳይሆን ተገልጋዮቹ የሚያነሱት ነው። ውልና ማስረጃ ከሚሰጠው አገልግሎት ቀጠሎ የሚጠቀስም ነው። እኛ ያስቀመጥነው ስታንዳርድ አለ። ከስታንዳርዱም አነስ ባለ ጊዜ አገልግሎቶችን እየጨረስን እንገኛለን።
ስለዚህ በዚህ በጀት ዓመትም ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ አሰራሮችን እንዘረጋለን ።አንዱ በኦንላይን የኢንቨስትመንት ፈቃድ የሚሰጥበት አሰራር ይሆናል። ለባለሀብቱ ከገንዘብ በላይ ጊዜ በጣም ውድ ነው።ስለዚህ ባለሀብቱ ባለበት ቦታ ሆኖ የኢንቨስትመንት ፈቃድ የሚያገኝበትን አሰራር ለመዘርጋት እንቅስቃሴ እያደረግን ነው።
ከዚህ ባሻገርም ኢንቨስትመንቶች በጥናት ላይ ተመስርተው እንዲካሄዱ ለማደረግም እንሰራለን፡ ፤ኢንቨስት ያደረገ ደግሞ እስከ መጨረሻው ውጤታማ በሆነ መንገድ ኢንቨስትመንቱ ተጠናቆ ወደ ሥራ የሚገባበትን ሂደት ማቀላጠፍ ይኖርብናል። ለእዚህም በእውቀት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ ማድረግ ይኖርብናል ማለት ነው።
ስለዚህ ይህን ከተለያየ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይም ከኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን የአዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስትመንት መልካም እድሎችና ተግዳሮቶች እንዲሁም ቅድሚያ የሚሰጣቸው ኢንቨስትመንቶች በሚል አንድ ጥናት እያሰራን ነው።ሰለዚህ በአዲስ አበባ ላይ መልካም እድሎች ምንድን ናቸው፤ ተግዳሮቶቹስ ምንድን ናቸው እንዴትስ ነው ልንፈታቸው የሚገባው ለአዲስ አበባስ በጣም ጥሩ ኢንቨስትመንት የሚባለው የቱ ነው፤ ካለው ሶሾዮ ኢኮኖሚክ ሁኔታ አኳያ የከተማ አስተዳደሩ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ ኢንቨስትመንቶች የትኞቹ ናቸው የሚለውን ለማወቅ የሚያስችል ጥናት ማስጠናት ጀምረናል።በዚህ ጥናት ላይ በመመስረት አሰራሩን ለማዘመን ይሰራል።
አሁን አጠቃላይ ኢንቨስትመንቱ ዘመናዊ በሆነ መልኩ እንዲስተናገድ እየተደረገ ነው። ይህን ይበልጥ ለማዘመን ነው ጥናት ማድረግ ያስፈለገው።ባለሀብቱ ሁሉንም አገልግሎቶች በኦን ላይን ማግኘት የሚችልበትን አሰራር ለመዘርጋት እንቅስቃሴ እያደረግን ነው። ይህም አሁን ከደረስንበት ደረጃ አኳያ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት አሁን ካለውም ለማሻሻል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ያለው ።
አዲስ ዘመን፡- ወደኋላ ልመልሶት እና ከተማዋ በሆቴል ዘርፍ ላይ ይበልጥ መሰራት ይኖርባታል ተብሎ ይታሰባልና የሆቴሎቹ ደረጃ እና በመሳሰሉት ላይ ለውጥ ይኖራል ተብሎ ይታሰባል ?
አቶ አብዱልፈታ፡- የሆቴሎቹን ደረጃ የሚሰጠው ራሱን የቻለ ተቋም አለ።እንደሚታወቀው ሆቴል ለቱሪዝም መስፋፋት ከፍተኛ ፋይዳ አለው ።ቱሪዝም ሲስፋፋ የውጭ ምንዛሬ ግኝቱ ያድጋል።ቱሪስቱ ብር ይዞ አይደለም የሚመጣው ፡የውጭ ምንዛሬ ነው ይዞ የሚመጣው።ስለዚህ የውጭ ምንዛሬ ግኝታችንን ያሳድጋል።ስለዚህ እኛ በተቻለ መጠን ባለኮከብ ሆቴሎችን ለማበረታት እንሰራለን።በዚህም ከአምስትና ከዚያ በላይ በሆኑት ሆቴሎች ላይ እንሰራለን።
ሁሉም ማበረታቻ ይደረግላቸዋል።ነገር ግን የተሻለ አቅም ያለው ሆቴል ሲመጣ ያለምንም ችግር የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሰጥተን መሬትም እናቀርባለን። በቅርቡም ወደ 11 ሆቴሎች ቦታ ቀርቦላቸው ወደ ትግበራ እንዲገቡ የከተማዋ ካቢኔ ውሳኔ አሳልፏል።አብዛኞቹ ሆቴሎችም የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ከውጭ ባለሀብቶች ጋር በሽርክና የሚገነቧቸው ናቸው።
ስለዚህ እነዚህ ሆቴሎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ትግበራ እንዲገቡ እየተሰራም ነው።የካፒታል መጠናቸውም በጣም ብዙ ነው።አንድ ሆቴል ብቻ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ያቀረበበት ሁኔታ አለ።በጣም ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ካፒታል ብሎ መውሰድ ይቻላል።ይህም የሆቴል ኢንዱስትሪውን በከፍተኛ ደረጃ ያሳድገዋል።
አሁንም እየቀረቡ ያሉ የሆቴል ልማት ጥያቄዎች አሉ።ለእነዚህ የሆቴል ልማት ጥያቄዎች የሚያስፈልገው ቦታ ከሌሎች እንደ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ካሉ ኢንቨስትመንቶች አኳያ ሲታይ በጣም ውስን ነው።የሚፈጥረው የኢኮኖሚክ ፋይዳ ግን በጣም ብዙ ነው።
ከተማዋን ዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ማእከል ለማድረግ እየተሠራ እንደመሆኑም ይህን ለማሳካት የሆቴሎች መገንባት ወሳኝ ይሆናል።ከተማ አስተዳደሩም በልዩ ሁኔታ ሆቴሎችን ለማስፋፋት እየሰራ ኢንቨስመንትን እየደገፈ ይገኛል።
አዲስ ዘመን፡- የከተማዋን ችግሮች የሚ ፈቱ የሚባሉ ኢንቨስትመንቶች አሉን ?
አቶ አብዱልፈታ፡- የከተማዋን ኢንቨስትመንት አላማ ሊያሳኩ ይችላሉ ብለን ያሰብናቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ተለይተዋል።አንዱ እንደጠቀስኩት የሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ነው ።ሆቴል አና የቱሪዝም መስኮች የከተማዋን ችግር ብሎም የሀገሪቱን ችግር ይፈታሉ ተብሎ ይታሰባል።በአንድ በኩል የሥራ እድል ይፈጥራሉ።በግንባታ ሂደትም ከተጠናቀቁ በኋላም ከፍተኛ የሥራ እድልን ይፈጥራሉ። በሌላ መንገድ ደግሞ ሆቴሎች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛሉ።
በዚህ ረገድ ኢንቨስት ሲደረግና ሆቴሎች ሲስፋፉ ቱሪስቶች በስፋት ወደ ከተማዋ እና ሀገሪቱ ይመጣሉ፤ኮንፈረንሶች የሚካሄዱበት እድል ይሰፋል።ቱሪስቶች በስብሰባም ይሁን በጉብኝትና በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማዋ ሲመጡ የውጭ ምንዛሬ ክምችታችን በከፍተኛ ሁኔታ ያድጋል።
በመልሶ መጠቀም ላይ ይሰራል። አዲስ አበባ ከፍተኛ መጠን ያለው የቆሻሻ ክምችት ያለባት ከተማ ናት።ይህን ቆሻሻ ሰብስቦ ለእንደገና አገልግሎት የሚያውል ኢንቨስትመንት ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል።ይህ ኢንቨሰትመንት ለከተማዋ ውበትም አስተዋጽኦ ያደርጋል። በሌላ በኩል ደግሞ ቆሻሻውን ከመሰብሰብ አንስቶ እስከ ምርትና ስርጭት ድረስ ባለው ሰንሰለት የሚከፈተው የሥራ እድልም በጣም ሰፊ ነው።
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም ቢሆን በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኢንቨስትመንት ላይም በትኩረት ይሰራል።ባለችው ውስን ቦታም ቢሆን በዘርፉ በስፋት ይሰራል። በተለይ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በግብአትነት የሚጠቀሙ የኢንቨስትመንት መስኮች በልዩ ትኩረት ይሰራባቸዋል።
በግብርና አግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ በተለይ የግብርና ምርቱ በቅርቡ ከሌለ አዋጭ ነው ተብሎ አይገመትም።በመሆኑም የኢንዱስትሪ ኢንዱስትሪ ግንኙነት በመፍጠር የአንዱ ኢንዱስትሪ ምርት ለሌላው ግብአት የሚሆንበት እድል ሰፊ በመሆኑ በዚህ ዘርፍም የሚሰማሩ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስት ሪዎችም እንደከዚህ ቀደሙ ድጋፍ የሚያገኙና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ይሆናል።
ስለነዚህ ዘርፎች እኛ ድጋፍ እና ክትትል ስናደርግላቸው ያሉባቸውን ማነቆዎች ስንፈታ ቅድሚያ ለምንሰጣቸው ፕሮጀክቶች በልዩ ሁኔታ ድጋፍና ክትትል እናደርግላቸዋለን።በዚህ መንገድ ከየት ጀምረን እስከ የት መሄድ አለብን የሚለውን በቅደም ተከተል ማስቀመጥ ተችሏል ማለት ነው።
አዲስ ዘመን፡- የቆርቆስና የከተማዋ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች በእናንተ በኩል የሚታዩ ናቸው ?
አቶ አብዱልፈታ፡- በሌላ ነው የሚሰሩት።
አዲስ ዘመን፡- መንግሥት በተደጋጋሚ እንደገለጸው በቀጣይ የትኛውም የኢንቨስት መንት እና የመሳሰለው ኢኮኖሚያዊ እንቅስ ቃሴ ስኬት መለኪያው ያስገኘው የሥራ እድል እንደሚሆን ገልጧል።እናንተ ከዚህ አንጻር ያላችሁ ዝግጁነት ምን ይመስላል ?
አቶ አብዱልፈታ፡- ኢንቨስትመንት የሥራ እድል በመፍጠር ረገድ ተኪ የለውም። ለኢንቨስትመንት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ በቅድሚያ ኢንቨስትመንቱን እንገመግማለን።በዚህ ሂደትም ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው ለሥራ እድል ፈጠራ ነው።ለምን ያህል ዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል ፤ምን ያህል የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል፤ ወደ ሀገር ውስጥ የምናስገባቸውን ምርቶች የሚተካ ምርት ነውን ፤ ወደ ውጭ የሚላክ ምርት ነው የሚያመርተው የሚሉትን በዝርዝር ገምገመን አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግለት እንከታተላለን።
በዚህ ዓመትም አንዱ ኢንቨስትመንቱ ልዩ የትኩረት አቅጣጫ አርገን የያዝነው የሥራ እድል ፈጠራ ነው።በዚህም የሥራ እድል የሚፈጥሩ ዘርፎችን በልዩ ሁኔታ የማበረታት ሥራ ይሠራል።ስለዚህ ይህም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስቶ በክቡር ምክትል ከንቲባውም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት አንዱ የሪፎርሙ አካል ተደርጎ እየተሠራበት ነው።
ስለዚህ ኢንቨስትመንቱ የሥራ እድል በመፍጠር በኩል ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለን እናስባለን። ካለፈው ዓመትም በተሻለ ደረጃ በዓመቱ የሥራ እድል የሚፈጥሩ ዘርፎች ይስፋፋሉ። ወደ ተግባር እየገቡ ያሉ ዘርፎችም አሉ። በተለይ በዚህ ዓመት ብዙ የሥራ እድል እየፈጠሩ ያሉ መሬት ያልተመቻቸላቸው በኪራይ እየሰሩ ያሉ ኢንቨስትመንቶች አሉ። ለእነዚህ መሬት እንዲመቻች በማድረግ ኢንቨስትመንታቸውን እንዲያስፋፉ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
አንዱ በከተማዋ ያለው ተግዳሮት አንዳንዱ መሬት ይጠይቃል።መሬት ከተሰጠው በኋላ ግን ወደ ልማት ሳይገባ ዓመታትን ይወስዳል፡፤መሬት አጥሮ የሚያለማበትን ገንዘብ ይፈልጋል።እስከ አሁን ያለው አካሄድ ይህ ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ ገንዘብ ያለውና መሬት ያላገኘ ደግሞ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ አውጥቶ እየተከራየ የሚሰራ ባለሀብት አለ።
ይህን ማስተካከል መቻል አለብን።ይህን ለማስተካከል ገንዘብ ሳይኖው መሬት የወሰደው መቀ ማት አለበት፤ እየቀማን ነው። በሌላ መንገድ ደግሞ መቶ እና ሁለት መቶ ሺ እየከፈሉ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እየሰሩ ያሉ አሉ።እነዚህ ባለሀብቶች መሬት ብናመቻችላቸው በወር የሚከፍሉትን ገንዘብ ለኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ያውሉታል። በዚህ ሰፊ ምርት ማምረት ይችላሉ። በሌላ መንገድ ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር ይችላሉ።
ስለዚህ መሬት አቅርቦታችን በሥራ ላይ ያሉ ግን በኪራይ እየተሰቃዩ ያሉ ባለሀብቶችን ቀድመን መሬት አንዲያገኙ ለማድረግ እየሠራን ነው። እነዚህ ሥራዎች የሥራ እድል ፈጠራውን በከፍተኛ ደረጃ ያበረታታሉ።በመሆኑም በዓመቱ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ካለፈውም በበለጠ መልኩ የሥራ እድል ለመፍጠር ይሰራል።
አዲስ ዘመን፡- የሥራ እድሉ የሚፈጠር ላቸውን ዜጎች ብዛት መግለጽ ይቻላል? በግንባታ ወቅትና ከተጠናቀቀ በኋ ,ላ የሚፈጥረው የሥራ እድል ቢገለጽ ?
አቶ አብዱልፈታ፡-የሚፈጠረውን የሥራ እድል ካለፈው ዓመት በአሥ ር በመቶ እንጨምራለን ።
አዲስ ዘመን፡ – አሁንም ወደ መሬት ጉዳይ ልመለስና የከተማዋ መልሶ ልማት ለአንቨስትመንት የሚሆን መሬት በማስገኘት በኩል ምን ያህል አስተዋጽኦ እያደረገ ነው ?
አቶ አብዱልፈታ፡- ከግዙፉ የለገሀር ፕሮጀክት አንስቶ ኢንቨስትመንቱ እየተካሄደ ያለው በመልሶ ልማት በሚገኝ መሬት ጭምር ነው።ሪፎርሙን ተከትሎ የመጣው አስተሳሰብ በመልሶ ማልማቱ አካባቢ ያለውን ህዝብ ጭምር የሚያለማም ይሆናል። የለገሀር ፕሮጀክት ከዚህ አንጻር ይጠቀሳል።ፕሮጀክቱ ከተማዋን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀይራል።የሥራ እድል ይፈጥራል፤ኢንቨስትመንቱ ራሱ የውጭ ምንዛሬ ይዞ ይመጣል።
ኢንቨስትመንቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የሚያስገኘው የውጭ ምንዛሬ እንዳለ ሆኖ ኢንቨስትመንቱ ራሱ አሁን የውጭ ምንዛሬ ይዞ መጥቷል፡፤ሌሎች አካባቢ ዎችም እንዲሁ እየለሙ ያሉት በመልሶ ልማቱ በተገኘ መሬት ነው።
ስለዚህ መልሶ ልማቱ ለኢንቨስትመንቱ ትልቅ እድል ይፈጥራል።ከዚህ በተጨማሪ አብዛኛዎቹ የኢንቨስትመንት መስኮች ደግሞ በማስፋፊያ አካባቢ ባሉ ክፍት ቦታዎች እየተካሄዱ ናቸው።ሁለቱንም በማቀናጀት መሀል ያለውን ክፍት ቦታ የአካባቢውም ህብረተሰብ ሊጠቀም በሚችልበት መንገድ ለኢንቨስትመንት እንዲውል ይደረጋል።ዳር ያለው ክፍት ቦታ ላይ እንዲሁ የአካባቢውን አርሶ አደር በማይጎዳና ይልቁንም በሚጠቅም መልኩ እንዲለማ ይደረጋል።
አዲስ ዘመን፡- የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ በከተማዋ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ስር ናቸው ወይስ በፌዴራል መንግሥት ስር ?
አቶ አብዱልፈታ፡- በፌዴራል መንግሥት ስር ናቸው።
አዲስ ዘመን፡- ጀሞ አካባቢ ያለው ሼድስ ?
አቶ አብዱልፈታ፡- እሱ በፓርክ ደረጃ የሚጠቀስ አይደለም፤ ሼድ ነው። እሱ በኛ ስር ነው።
አዲስ ዘመን፡- የኢንቨስትመንት ህግ ማሻሻያ እየተደረገ ነው። ማሻሻያው የኢንቨ ስትመንቱን ተግዳሮቶች ሊፈታ ይችላል ተብሎ ይታሰባል ?
አቶ አብዱልፈታ፡- እንደሚታወቀው የኢንቨስት መንት ህጉ በተደጋጋሚ ተሻሽሏል። አሁንም እንዲ ሻሻል እየተደረገ ነው።የኢንቨስትመንት አዋጁ በተለይ የውጭ ባለሀብቶችን በተሻለ መልኩ ሊስብ በሚችል መልኩ ከፓዘቲቭ ሊስቲንግ ወደ ነጌቲቭ ሊስቲንግ ሺፍት ያደረገ አዋጅ ማሻሻያ እየተደረገበት ነው።
ባለሀብቱ በእነዚህ ዘርፎች ይሰማራል ከማለት ይልቅ በእነዚህ ዘርፎች አይሰማራም ተብሎ ሲቀመጥ በሌሎች አዳዲስ የኢንቨስትመንት መስኮች የመሰማራት እድል እንዲኖረው ያደርጋል። በአዳዲስ ግኝቶችና ፈጠራዎች ባለሀብቱ እንዲሰማራ የሚያስችል ሁኔታን ይፈጥራል። አዳዲስ የኢንቨስት መንት አማራጮች ሲመጡ በቀላሉ ኢንቨስት ማድረግ የሚችልበት ሁኔታ ይፈጠራል።
ማሻሻያው የኢንቨስትመንቱን ማነቆዎች ሊፈታ የሚችል ነው። እኛም በዝርዝር ውይይት ያደረግንበት አዋጅ ነው። ሲጸድቅ ኢንቨስትመንቱን በማስፋፋት ረገድ ጥራት ያለው ኢንቨስትመንት ወደ ሀገራችን ኢንዲመጣ በማድረግ በኩል ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል። ስለዚህ ተግዳሮቶቹን እንዲፈታ ተደርጎ የተዘጋጀ ማሻሻያ ነው።
አዲስ ዘመን፡- ላደረጉልን ትብብር እናመሰግናለን።
አዲስ ዘመን መስከረም 6 / 2012
ኃይሉ ሣህለድንግል