’
አዲስ አበባ፡- በ2012 ዓ.ም አዲስ ዓመት ኢትዮጵያዊያን የልብ መታደስ አድርገው በይቅርታና በሰጥቶ መቀበል መርህ ሁሉንም ልዩነቶች ወደ መቀራረብ ብሎም ወደ ፍጹም መተማመን በማምጣት አንድነታቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የሃይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ።
የሃይማኖት አባቶቹ በዛሬው የ2012 ዓ.ም አዲሱን ዓመት አስመልክተው ቡራኬ በሰጡበት ወቅት እንዳስታወቁት ኢትዮጵያዊያን በይቅርታና በሰጥቶ መቀበል መርህ ልዩነቶችን ሁሉ ማጥበብ ይገባል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አብነ ማቲያስ ባስተላለፉት መልዕክት አዲስ የዘመን መለወጫ አዲስ ሊሆን የሚችለው ልቦናችን ሲታደስ እንደሆነ ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት የተስተዋሉ የመለያየት ፣ መገዳደል፣ ወገንን ማፈናቀልና አብያተ ሃይማኖትን መዳፈር የእርጅና ምልክቶች ናቸውና ከአሮጌው ዘመን ጋር ማለፍ ይገባቸዋል ብለዋል። በምትካቸውም አንድነት፣ መፈቃቀር፣ መተዛዘን መቻቻልና መከባባር፣ መተማመ ንና አብሮነት ሊበለጽጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
እግዚአብሄር የፍጥረታት መታደስን የሚወድ አምላክ እንደሆነ በሥነ ፍጥረት ብቻ ሳይሆን በቅዱስ ቃሉም ‹‹በልባችሁ በመታደስ ተለወጡ›› በማለት የሰው ልጅ መታደስ እንዳለበት ማስተማሩን ያስታወሱት ፓትርያሪኩ በአስተሳሰብ፣ በሥራ፣ በአኗኗር ከልብ የሆነ መታደስ ሊኖረን ይገባል ብለዋል።
‹‹የኢትዮጵያን ህዳሴ እናበሥራለን›› የሚለው መልካም ምኞታችን ከቃላት አልፎ ተግባራዊ እንዲሆን ከሁሉም በፊት ይቅርታና እውነተኛ መግባባት በሁሉም ወገኖች ሊፈጸም እንደሚገባ መክረዋል።በሀሳብ መቀራረብና በሰጥቶ መቀበል መርህ እየተቻቻሉ መሄድን አዋጭ ባህል አድርገን መጓዝ ካልቻልን መቼም ቢሆን ለችግራችን መፍትሄ አናገኝም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነ ኢየሱስ ሱራፌል በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት አዲሱን የ2012 ዓ.ም መልካም ነገርን በማቀድና በመስራት ብሎም በመፈጸም ልባችንን ከፍተን በፍቅር፣ በይቅርታ፣ በአንድነትና በህብረት መጀመር እንደሚገባ አሳስበዋል።
አዲሱ ዓመት በእግዚአብሄር እርዳታና በዜጎች ቀና ልብ ከችግር፣ ከጥላቻ ከመለያየትና እርስበእርስ ከመጠፋፋት የምንታቀብበት፤ የመረጋጋት፣ የማስተ ዋል፣ የመደጋገፍና በአንድ አምላክ የተፈጠርን ወንድማማቾችና የአንድ ሀገር ልጆች መሆናችንን አውቀን ከጥፋት መንገድ የምንወጣበት እንዲሆን አስገንዝበዋል።
ለወጣቶች ባስተላለፉት መልዕክትም ለውጡን ለማደናቀፍ ከሚፈልጉ ሃይሎች ጋር በተባበረና የአባቶችን ምክር በመሰነቅ ሀገርንና ህዝብን ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።
በዚህ ዓውድ ዓመት ሁሉም ሰው ባለው አቅም በየአካባቢው የተፈናቀሉ፣ የተቸገሩትና አቅማቸው የደከመን በመርዳትና በጎ ነገሮችን ሁሉ በማድረግ የደስታ በዓልን አብረው እንዲያከብሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንትና የዑላማ ሰብሳቢ ቀዳሚ ሙፍቲ የክቡር ዶክተር ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ባስተላለፉት መልዕክትም አሁን ሀገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ሰላማችንን ለማረጋገጥ በአዲሱ ዓመት ሰዎች ስለአንድነት፣ ስለመተባበርና ፍቅር መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ቀዳሚ ሙፍቲው የሃይማኖት ነብዩ አለይቲ ሰላት ወሰላም ‹‹በሌላ ከመገምገማችሁ በፊት ነፍሳችሁን ገምግሙ፤ ነፍሳችሁን ሰልሉ ››ማለታቸውን በማስታወስ ሰው በየቀኑ፣ በየወሩና በየዓመቱ ሥራውን እንዴት እንዳሳለፈ በመገምገም አካሄዱን ማስተካከል እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።
አሁን በሀገሪቱ ያለውን መከፋፈልና መገፋፋት ለማስቀረትም ሁሉም ዜጋ በጎ በጎ ነገር በማሰብ አንድነቱንና ህብረቱን ሊያጠናክር እንደሚገባም መክረዋል።የሀገሪቱን ገጽታ በመለወጥ ረገድም ከእኔ ምን ይጠበቃል? የሚል ኃላፊነት በመያዝ ሀገራዊ መንግስታዊና ህዝባዊ ተግባራትን ለማከናወን ዝግጁ መሆን እንደሚያስፈልግና ሁሉም ዜጋ ልቡን ገርቶ ለሀገርና ለወገን የሚበጅ መልካም ተግባራትን እንዲያከ ናውን አሳስበዋል።
አዲሱን ዓመት የፍቅር የሰላም የአንድነት እንዲሆን ሁሉም ሰው ፈጣሪውን በመፍራት ከጥፋት እንዲታቀብና አንድነት እና መረዳዳት የሰው ልጅን የሚያጠናክር በመሆኑ እያንዳንዱ ዜጋ ለአንድነቱና ለሰላሙ ተባባሪ በመሆን ዓመቱን በሰላምና በፍቅር እንዲያሳልፍ አሳስበዋል።
እንደግለሰብም ይሁን እንደህዝብ ባለፈው ዓመት ያከናወናቸውን መልካም ተግባራት ሁሉ አጠናክረን በመቀጠልና በማጎልበት በሌላ በኩል ያልጠቀሙንንና የጎዱንን ነገሮች በማራገፍ የአዲሱን ዓመት አዲስ ምዕራፍ መጀመር ከሰው ሁሉ የሚጠበቅ መሆኑን የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዚዳንት ቄስ ዮናስ ይገዙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በህዝቦች መካከል በብሄር፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ያሉትን ልዩነቶች እንደ ጸጋ በመቀበል የመቻቻልን መንፈስ በማጎልበት እንደአንድ ሀገር ህዝብ አብሮ ለመኖር ቁርጠኛ መሆን ከዜጎች ሁሉ እንደሚጠበቅም አሳስበዋል።
ያለፈውን መጥፎ ክስተት ሁሉ ወደኋላ ጥለን ምሳሌ መሆን የሚችል አዲስ ታሪክ ለመሥራት ሁሉም ጥረት ማድረግ እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
እግዚአብሄር የሰጠንን ይህችን ሀገር በሁሉም ዘርፍ ወደተሻለ የዕድገት ደረጃ በማሸጋገር ያደገች፣ የለማችና የበለጸገች ህዝቦቿም የሚኮሩባት ሀገር እንድትሆን ሁሉም በአንድነት እንዲነሳ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በአሁኑ ጊዜ ከመቼውም በላይ ለሀገራችን ሰላም በሚያሥፈልጋት ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻድቁ አብዶ ናቸው። በአዲሱ አመት ቂምና በቀል እንዲሁም ጥላቻ ተወግዶ በፍቅርና በመከባበር መኖር ለሰላም መጽናት አስፈላጊ እንደሆነም ጠቅሰዋል።
የሀይማኖት አባቶቹ አዲሱ ዓመት ለምድሪቱ አንድነትና ፍቅር የሚተጋበት ፣ ለሰላምና ብልጽግና የሚሠራበት፣ ከሚያለያዩ የክፋት ተግባርና አሉባልታ ይልቅ ስለአንድነት የምናስብበት፣ ለራሳችን ብቻ ከመኖር ይልቅ የተቸገሩ ወገኖቻችንን የምንረዳበት፣ የታመሙትን የምንጎበኝበትና ያዘኑትን የምናጽናናበት እንደሚሆን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አዲስ ዘመን መስከረም 1ቀን 2012 ዓ.ም
ኢያሱ መሰለ
These women on the phone have nothing else in mind but sex. You’ll notice that immediately when you call them and have them on the phone. And if you then also enter the code for the extensive chat with her that you get from them, you can also watch the hot sluts live during camsex. Come and watch camsex without registration and any monthly costs.