
አዲስ አበባ፦ የፋይናንስ ተቋማት ለማኑፋክቸሪን ዘረፉ ቅድሚያ እንሰጣለን ከማለት በዘለለ በተግባር መደገፍ የሚች ሉበት ሁኔታ መመቻቸት እንደነበረበት የፌዴራል አነስተኛ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አስፋው አበበ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት፣ የፋይናንስ ተቋማት ዘርፉን ሊያበረታቱና ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ አዳዲስ አሰራሮችን መንደፍ ይጠበቅባቸው የነበረ ቢሆንም እስከ አሁን ከንግግር የዘለለ ሥራ መስራት አልቻሉም።
እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ ሼድ፤ የኤሌክትሪክ ኃይልና ሌሎች አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች ቅድሚያ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ እንሰጣለን ይባላል ግን በሚባለው ልክ ዘርፉ ያለው ፋይዳ ምንድን ነው? ቅድሚያ ማግኘት ያለበት ማነው? የሚለውን በትክክል ተረድቶ ያንን ሊያግዝ የሚችል አሰራር መዘርጋት ላይ ክፍተት አለ፡፡
በሼድ፣ በመሰረተ ልማት፣ በጥሬ እቃና በፋይናንስ አቅርቦት ላይ አሁንም በሚፈለገው ደረጃ እየተሄደ አይደለም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በተለይ በማኑፋ ክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የሚገቡት የተለየ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡
ይህንን የተረዳ አመራርና ፈጻሚ የፋይናንስ ተቋማት መኖር ሲችል ብቻ ነው ፈጥነን የአነስተኛ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ለኢንዱስትሪው መዋቅር ከግብርና ቀጥሎ ተቀባይ መሆን የሚቻለው ብለዋል፡፡
አዲስ ዘመን ነሃሴ 29/2011
እፀገነት አክሊሉ