
አዲስ አበባ ፦ የፌደራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሙስናን ለመከላከልና ለመዋጋት የሚያስችላቸውን የሦስትዮሽ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራ ረሙ።
የፌደራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አየልኝ ሙሉዓለም እንደተናገሩት፤ ተቋማቱ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ መፈረማቸው ቀደም ሲል አብረው እየሠሩ እንዳልነበረ መወሰድ የለበትም።
የመግባቢያ ሰነዱ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ የሙስና መከላከልን፣ የሙስና ወንጀሎች መለየትን፣ ወንጀሎችን መመር መርን፣ ተጠርጣሪዎች መክሰስን፣ ማስቀጣት እንዲሁም በሙስና የተመዘበረውን ሀብትና ንብረት በማስመለስ ተቋማዊ ቅርፅ የተላበሰ አሠራር ለመፍጠር የሚያግዝ ነው።
በአንድ ተቋም የሚገኙ ለሌላው ተሰማሚ ተቋም አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በወቅቱ ለሚመለከተው አካል ማስተላለፍ የሚቻልበትን ሥርዓት ለመዘርጋት የሚ ያስችል መሆኑን የገለፁት ደግሞ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተኮላ አይፎክሩ ናቸው። በተቋማቱ መካከል የሚደረጉ የመረጃና የሙያዊ ድጋፍ ዓይነ ቶችን በግልፅ የሚያመላክት መሆኑንም ገልፀዋል።
የፌደራል ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በበኩላቸው፤ የመግባቢያ ሰነዱ እነዚህ ሦስት ተቋማት በሕግ የተሰጣቸውን ስልጣንና ኃላፊነት በመመርኮዝ የሚደረጉ ስርቆቶችና መሰል ብልሹ አሠራሮችን ለመከላከልና ለመዋጋት ተባብረው የድርሻቸውን በመወጣት የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። «እስከ ዛሬ የነበረውን አሠራር ወደ ተቋማዊ ቅርፅ በማምጣት የተሻለ ሥራ ለማከናወን እንደሚያግዝ እናምናለን» ብለዋል።
የጋራ መግባቢያ ሰነድ በሙስና መከ ላከል ሥራዎች ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ገልፀዋል። የመረጃ ልውውጦች፣ የሚዘጋጁ ወይም ሊቀረፁ ስለሚገባቸው የፀረ ሙስና ሕጎች፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች፣ አገር አቀፍ የሙስና ጥናትና ምርምር ውጤት አውደ ጥናቶችና ሴሚናሮች፣ የመፈፀም አቅም ግንባታ፣ ሙያዊ ምክክሮችና የተሞክሮዎች ልውውጥ እንዲሁም የሀብት ማሳወቅ፣ ማስመዝገብና ተያያዥ ሥራዎችና መሰል ሞያዊ መደጋገፎች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነው ተብሏል። በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወነውን የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ሥራ ዎች ውጤታማ በማድረጉ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረውም ተገ ልጿል።
አዲስ ዘመን ነሃሴ 11/2011
ዳንኤል ዘነበ