የኦብነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አብዲራማን ማሃዲን ከድርጅቱ ሊቀመንበርነት አነሣ

አዲስ አበባ፡- የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ማዕከላዊ ኮሚቴ እያካሄደ በሚገኘው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ አብዲራህማን ማሃዲን ከድርጅቱ ሊቀ መንበርነት አንስቷል።

አብዲራህማን ማሃዲ ከድርጅቱ ሊቀመንበርነት ለመነሣታቸው የድርጅቱን አንድነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግባራትን ማከናወናቸው በምክንያትነት ተጠቅሷል።

ግንባሩ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ወደ ሀገር ከገባ ጊዜ አንስቶ ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ ለሕዝብ የገባው ቃል ተግባራዊ እንዳይሆንም በግላቸው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ተጠቁሟል።

ኦብነግ በወርሃ ነሐሴ 6 ቀን 2010 ዓ.ም ነበር መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ ወደ ሀገር የገባው። ማዕከላዊ ኮሚቴው እያካሄደ በሚገኘው መደበኛ ስብሰባ በቀጣይ ለሚካሄደው ጉባዔ የጉባዔ አደራጅ ኮሚቴ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ ዘመን ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You