
– የፊቼ ጫምባላላ በዓልን ከክልሉ ሀብቶች ጋር በማጣመር ቱሪዝምን ማሳደግ ይገባል
ሃዋሳ፡- የፊቼ ጫምባላላ በዓልን በሲዳማ ክልል የቱሪዝም መስህብ መሆን የሚችሉ ሀብቶች ጋር በማቀናጀት የዘርፉን እንቅስቃሴ ማሳደግ ይገባል ሲል የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ ።
የቱሪዝም ሚኒስትር ወይዘሮ ሰላማዊት ካሳ በሲዳማ የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጫምባላላ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሲዳማ ክልል በተለያዩ ሀብቶች የታደለ ነው፡፡ ፊቼ ጫምባላላ በዓልን ከእነዚህ ሀብቶች ጋር በማቀናጀት ተጠቃሚነትን ማሳደግ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
ፊቼ ጫምባላላ ሀገራችን ከታደለቻቸው የማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱ ነው ያሉት ሚኒስትሯ ፤ይህ በዓል በአግባቡ ለምቶ የሚጠበቅበትም ጥቅም መስጠት ይኖርበታል ነው ያሉት።
በዓሉ በሲዳማ አባቶች ተጠብቆ የተለያዩ እሴቶችን በማንፀባረቅ እዚህ ደርሷል ያሉት ሚኒስትሯ፤ የፍቼ ጫምባላላ ባለው ትውፊታዊ ይዘትና ማህበራዊ እሴት ሌላው ዓለምን በማስደመም ጭምር በዓለም የተባበሩት መንግሥታት የትምህርትና የባህል ድርጅት ዩኔስኮ መመዝገቡን አውስተዋል።
ሚኒስትሯ፤ ኢትዮጵያ ያሏት የባህልና የተፈጥሮ ብዝሀ ሀብቶች መድመቂያ ብቻ ሳይሆኑ እንደ ሀገር ለምናደርገው ቀጣዩ የብልፅግና ጉዟችን ስንቅ እንደሆኑ አመልክተው፤ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እነዚህ ባህሎች እና የቱሪዝም ሀብቶች ተጠብቀው እንዲቆዩ የማድረግና የማልማት ኃላፊነት አለበት፡፡ ይህንንም ለማስቀጠል ከክልሉ ጋር አብሮ እንደሚሠራም ገልፀዋል።
በበዓሉ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ስለ ጊዜ የሚረዳ ሕዝብ ጥልቅ ፍልስፍና ያለው እንደሆነ ገልፀው፤ የሲዳማ ሕዝብ የጥልቅ እውቀትና የፍልስፍና ውጤት ባለቤት መሆኑን ተናግረዋል። ፊቼ ጫምባላላ በዓል የዚህ ሕዝብ ውጤት ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ እያለፈች ድሎቿን እያሳካች ብልፅግና አይቀሬ መሆኑን በተግባር እያረጋገጠች ያለች ሀገር መሆኗን አመልክተው፤ ኢትዮጵያ እያሳካች ባለችው የብልፅግና ጉዞ ውስጥ የሲዳማ ሕዝብ አይተኬ ሚናውን እየተጫወተ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው እንደተናገሩት፣ የፊቼ ጫምባላላ በዓል የፍቅር ተምሳሌት በዓል ነው፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች ከሲዳማ ሕዝቦች ጋር እጅግ በጣም የተጋመደ የተቀላቀለ፣ በአንድነት የኖረ ሕዝብ ነው፤ ሁለቱ የክልል ሕዝቦች አብሮነታቸውን ይበልጥ በማጠናከር ለጋራ ዕድገት በጋራ ይሠራሉ ብለዋል፡፡
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ፣ በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቦታ ያለው፣ የፊቼ ጫምባላላ በዓል ከአዲስ ዘመን መለወጫነት ባሻገር ቂምና ቁርሾ የሚወገድበት ይቅርታ የሚሰፍንበት የሰላም ፣ የፍቅርና የአብሮነት እሴቶችን የያዘ ታላቅ በዓል መሆኑን ገልፀዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ የሶማሌ እና ሲዳማ ክልል ሕዝቦች ዘመናት ያስቆጠረ ታሪካዊ ትስስር ያላቸው መሆኑን ጠቅሰው፣ በዓሉን የሶማሌ ክልል ሕዝብም በጋራ የሚያከብረው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሲዳማ ዘመን መለወጫ (ፊቼ ጨምባላላ) በዓል በሃዋሳ ከተማ ሶሬሶ ጉዱማሌ ከተለያዩ አጎራባች አካባቢዎች የመጡ የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ባህሉን በሚገልፁ ክንዋኔዎች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
አንፃር አስተዋጽኦ ማድረጉን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ ከተመረተበት ሥፍራ አንድ እንቁላል በስምንት ብር ዋጋ ሲቀርብ እንደነበርና አሁን ላይ ከዶሮ መኖ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ አንድ እንቁላል ከ11 ብር ከ50 ሣንቲም እስከ 13 ብር እየቀረበ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
እንቁላል አሁን እየቀረበ ባለው ዋጋ መቅረብ አለበት ብሎ ኮሚሽኑ እንደማያምን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ ከዋጋ ጋር የተያያዘውን ጉዳይ በምክትል ከንቲባ የሚመራ በየሳምንቱና በየአስራ አምስት ቀን የሚገመግም ኮሚሽኑን ጨምሮ ግበረኃይል ተቋቁሞ እየሠራ እንደሆነና ኮሚሽኑም በእያንዳንዱ ክፍለ ከተማ ውስጥ በቀን ምን ያህል እንቁላል እየተመረተ እንደሚቀርብ ሪፖርት እንደሚያቀርብ አስረድተዋል፡፡
አንድ እንቁላል ዋጋው እስከ 20 ብር መድረሱ የመሸጫ ዋጋው እንዳልሆነ፣ ከምርት ጋርም እንደማይያያዝና ችግሩ ሰው ሠራሽ መሆኑን ገልፀዋል። በ13 ብር ሂሣብ የሚረከብ ነጋዴ ከአንድ ብር በላይ አትርፎ መሸጥ እንደሌለበት ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት፡፡
እንቁላል አሁን ካለው የመሸጫ ዋጋም ዝቅ ባለ ዋጋ መቅረብ እንዳለበት ጠቅሰው፤ ከመኖ ግብዓት ጋር የሚያያዝ መሆኑንና በዚህ ላይ መሥራት እንደሚገባና መኖ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በኮሚሽኑ በኩል እየተሠራ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ወደ 210 የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች መኖራቸውንና ከዚህ ውስጥ ለግብርና ወደ 87 ቦታዎች መዘጋጀታቸውን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ አገልግሎት ለሚሰጡበት ቦታ እንደማይከፍሉና ወጪያቸው ትራንስፖርት ብቻ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ አኳያ አምራቾች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ይገባቸዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡ በየሱቁ ከዋጋ በላይ እየቀረበ ያለውን ሕገወጥ ነው ብለዋል፡፡
ሰሚራ በርሀ
አዲስ ዘመን መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም