ለሆድ ህመም የሚዳርጉን የተለያዩ መንስኤዎች አሉ። ብዙ ምግብ ከመብላት ጀምሮ እስከ አንጀት ካንሰር ድረስ የሆድ ህመም ብዙ መንስኤዎች አሉት። ለረጅም ጊዜ የሚቆይ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የሚመጣ የሆድ ህመም በዶክተር መታየት አለበት። አብዛኛውን ጊዜ ግን የሆድ ህመም በቤት መፍትሄዎች ሊቀረፍ የሚችል ቀላል ህመም ነው።
ስለዚህ ቤት ውስጥ እንዴት እራሳችንን ማከም እንችላለን? የምናደርገው መፍትሄ በሚታየን የህመም ስሜት አይነት ይወሰናል። የሆድ ህመም አይነቶችን ከነመፍትሄዎቻቸው እነሆ፦
መንስኤ፡ በጭንቀት ምክንያት የሚፈጠር የሆድ ህመም
መፍትሄ፡ ዎክ ወይም አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
ማብራሪያ፡ ትልቅ ንግግር ከማድረግዎ በፊት ወይም የሴት/ወንድ ጓደኛ የሚሆን ሰው ሊተዋወቁ ሲሄዱ በሚሰማዎት የጭንቀት ስሜት ሳቢያ የሆድ ህመም ሊሰማዎት ይችላል። በዚህ ጊዜ ዎክ ማድረግ፣ ከጓደኛ ጋር ማውራት ወይም በጥልቀት መተንፈስ ይረዳል።
መንስኤ፡ በሆድ ድርቀት ሳቢያ የሚፈጠር የሆድ ህመም
መፍትሄ፡ የገንዳ ውሃ ውስጥ 1.5 ኩባያ እንግሊዝ ጨው በማዋሃድ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ውሃ ውስጥ መተኛት
ማብራሪያ፡ እንደዚህ ማድረግ ሆድን ለማላላት ይረዳል። እንደ ሌላ አማራጭ ጨውን ቀጥታ ሆድ ላይ ማሸት ይችላሉ።
መንስኤ፡ የሆድ መሳሳብ
መፍትሄ፡ የናና ሻይ መጠጣት ወይም ሙቀት ያለው ፎጣ ሆድ ላይ ማስደገፍ።
ማብራሪያ፡ ናና ሻይ ሆድ እንዲላላ በማድረግ የመሳሳብ ስሜትን ይቀንሳል። በተጨማሪም ለ20 ደቂቃ ሙቀት ያለው ፎጣ ሆድ ላይ ማስደገፍ ይረዳል።
መንስኤ፡ ማቅለሽለሽ
መፍትሄ፡ ዝንጅብል
ማብራሪያ፡ ዝንጅብል የማቅለሽለሽ ስሜትን ለመቅነስ ይረዳል። በጥሬም ሆነ በሻይ መልክ መውሰድ ይቻላል።
መንስኤ፡ ቃር ስሜት
መፍትሄ፡ ጋቪስኮን መድሃኒት
ማብራሪያ፡ ጋቪስኮን የላይኛው የሆድ ክፍል ላይ የሚፈጠርን የህመም ስሜት ለማስታገስ ይረዳል። በማንኛውም ጊዜ ሊወስዱት ይችላሉ። የበሉትን ምግብ በመሸፈን የሆድ መነፋት እና የቃር ስሜትን ያስታግሳል።
መንስኤ፡ ተቅማጥ
መፍትሄ፡ ፈሳሽ አብዝቶ መጠጣት
ማብራሪያ፡ የተቅማጥ ዋነኛ መንስኤ ከሰውነት በፍጥነት ሊወገድ የሚገባው ፓቶጅን ነው። ተቅማጥ የሰውነት ፈሳሽ መጠንን ስለሚቀንስ ውሃ አብዝቶ መጠጣት ተገቢ ነው።
ምንጭ ጤነኛ ድረ ገፅ
አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ 29/2011