አዲስ አበባ፡- ‹‹የባሌ ዞን አርሶ አደሮች ማለት ያለባቸው መንገድ ይሰራልን ሳይሆን እንዳትራቡ ስንዴ መጥታችሁ ውሰዱ ነው›› ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ ከእንግሊዝ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለማ መገርሳ ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ጊኒር ወረዳ ተገኝተው የዱረም ስንዴ የሚያመርቱ አርሶ አደሮችን ከትናንት በስቲያ ጎብኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉብኝቱ በኋላ እንደተናገሩት፤ የአካባቢው አርሶ አደር ከአንድ ሄክታር መሬት ከ80 በላይ ኩንታል ስንዴ በማምረት ላይ ነው፡፡ አገሪቱ ደግሞ ስንዴ ተቸግራ ከተለያዩ አገሮች በመግዛት ከውጭ ታስመጣለች፡፡ ስለዚህም ባሌዎች ማለት የሚጠበቅባቸው ይህ መንግሥት ከውጭ ማምጣት ይሻለዋል? ወይስ ከባሌ አርሶ አደር ገዝቶ ቢጠቀም የሚለውን ነው፡፡
‹‹ስለዚህም ሁለተኛ የመንገድ ጥያቄ እንዳታቀርቡ፤ ማለት ያለባችሁ ለምን ትራባላችሁ? እኛ ስንዴ አለንና መጥታችሁ ውሰዱ ነው ማለት ያለባችሁ›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣‹‹የባሌ ዞን ጊነር ወረዳ አርሶ አደር በወረዳዋ እየሰራ ያለውን ሥራ ከርቀት ሆነን ስንሰማ የነበረ ቢሆንም ዛሬ እነሆ በዓይናችን ማየት በመቻላችን በእጅጉ ተደስተናል፡፡ ይሁንና ይህ አካባቢ ሰፊ ምርት እያለው የመንገድ ችግር በመኖሩ ብቻ የገበያ ሁኔታ ባለመኖሩና ያመረታችሁትን በአግባቡ የሚገዛችሁ ባለመኖሩ ድካማችሁ ሁሉ ፍሬያማ መሆን አልቻለም›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ ግን ከአርሶ አደሩ ጋር በመነጋገራቸውና ማሳዎችንም በመጎብኘታቸው ችግር እንደሚፈታም አስረድተዋል፡፡
ከዚህ በኋላ አካባቢያቸውንም አገሪቱንም በማሳደግ የህዝብን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል እንዲቻል የአካባቢው ቄሮዎች የልማቱ ተሰላፊ ለመሆን ማምረትና ማልማት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል፤፡ መንግሥትም ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር እንደሚሰራ ጠቅሰው፣አገሪቱንም በጋራ በመሆን መለወጥና አንድነቷን ማስጠበቅ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤በግብርናው ብቻ ሳይሆን በቱሪዝሙም ባሌ ስመ ጥር ነው፡፡ በተወሰነ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለው የአየር ጻባይ ለውጥ ያስገርማል፡፡ እንዲህ አይነት እጅግ በጣም ቅዝቃዜና እጅግ በጣም ሙቀትን በተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ርቀት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንኳ ቢፈለግ ማግኘቱ ከባድ ነው፡፡
‹ከዚህ በኋላ እኛም መተኛት አንሻም፤ ሌት ተቀን ሰርተን አገራችንንና ህዝባችንን መለወጥ እንፈልጋለን፡፡ ዋና ዓላማችንም ልማት ሊሆን ይገባል፡፡ እናንተም ከጎናችን ሁኑ፤ ያኔ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን እንለውጣለን፡፡››ሲሉም ,አሰገንዝበዋል፡፡
ኦሮሞ ከጦርነት፣ ከመገፋፋት ወጥቶ አገርን ለመቀየር አንድነትን ማጠናከር እንደሚጠበቅበት ፣ማድረግም እንደሚችል ትልቅ እምነት እንዳላቸውም አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ያቀረባችሁትን ጥያቄ ምላሽ እንሰጥበታለን፡፡ የምናደርግላችሁ ደግሞ ለእናንተ ብቻ አስበን ሳይሆን ከእናንተ ለመጠቀምም ጭምር ነው፡፡ ብዙ ምርት አይተናል፡፡ ያን ለማጣጣምም ነው የምናግዛችሁ›› በማለት የአርሶ አደሮቹ ጥያቄ ምላሽ እንደሚያገኝ አረጋግጠዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው፤ ‹‹የኦሮሞ መሰረትና የታላቁ አገር ፈርጥና ጌጥ የሆነው ባሌ ከምንም በላይ የእነ ዋቆ ጉቱ፣ የእነ ድሬ ሺህ ሁሴን፣የብዙ ታጋዮች አገርና ትግል የተጠነሰሰበትና ዳር የደረሰበት መሆኑን ጠቅሰው፣ ‹‹በዚህ እንኮራባችኋለን›› ብለዋል፡፡
ግብርናን እንዴት ማዘመን እንደሚቻል ከባሌ መረዳታቸውን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያን ማዘመን ግብርናን ማዘመን ብሎም ወደ ኢንዱስትሪ መሻገር እንደሆነም አመልክተዋል፡፡ ስለዚህም የክልሉም ሆነ የፌዴራል መንግሥት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣና ድጋፍም እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡
የእንግሊዝ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚር ቶኒ ብሌር፣ በባሌ ዞን ተገኝተው የአርሶ አደሩን እንቅስቃሴ እንዲጎበኙ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ መጋበዛቸውን ጠቅሰው፤ህዝቡ አስደናቂ ችሎ ያለውና መለወጥ የሚፈልግ መሆኑን ማስተዋላቸውን ተናግረዋል፡፡ መልካምድሩን ያደነቁት ብሌር፣ የግብርና ልማቱ ለኢኮኖሚ እድገቱ የሚያግዝ እንደሆነና በግብርናው ዘርፍ የታየው የቴክኖሎጂው አጠቃቀምም መልካም መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ አገሪቱም በዘርፉ ትልቅ አቅም ያላት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
‹‹እኔ በጠቅላይ ሚኒስትሩም፣ በአገሪቱም ሆነ በኢትዮጵያና በባሌ ህዝብ አምናለሁ፤ መልካም የሆነ መልካምድርና ትልቅ አቅም ያለው ነው›› ሲሉ የእንግሊዙ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡
የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ፣ቴክኖሎጂን በመጠቀም በማምረት ላይ ያለው የባሌ አርሶ አደር ለኦሮሚያ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያውን ሁሉ ትልቅ ተስፋ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በስፍራው የተገኙ ከፍተኛ ባለስልጣናትም እንደኩሩባቸው ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እንደሚፈልጉም ተናግረዋል፡፡
አስቴር ኤልያስ
Geothermal HDPE Pipes in Iraq Elite Pipe Factory in Iraq is at the forefront of providing advanced geothermal HDPE pipes, designed specifically for efficient and sustainable geothermal energy systems. Our geothermal HDPE pipes are crafted to offer excellent heat resistance, flexibility, and longevity, making them perfect for ground-source heat pump systems and other geothermal applications. With a commitment to quality and innovation, Elite Pipe Factory stands out as one of the leading and most reliable manufacturers in Iraq. We ensure that our geothermal HDPE pipes meet the highest industry standards, offering superior performance and durability. Discover more about our geothermal solutions by visiting elitepipeiraq.com.
Bwer Company is a top supplier of weighbridge truck scales in Iraq, providing a complete range of solutions for accurate vehicle load measurement. Their services cover every aspect of truck scales, from truck scale installation and maintenance to calibration and repair. Bwer Company offers commercial truck scales, industrial truck scales, and axle weighbridge systems, tailored to meet the demands of heavy-duty applications. Bwer Company’s electronic truck scales and digital truck scales incorporate advanced technology, ensuring precise and reliable measurements. Their heavy-duty truck scales are engineered for rugged environments, making them suitable for industries such as logistics, agriculture, and construction. Whether you’re looking for truck scales for sale, rental, or lease, Bwer Company provides flexible options to match your needs, including truck scale parts, accessories, and software for enhanced performance. As trusted truck scale manufacturers, Bwer Company offers certified truck scale calibration services, ensuring compliance with industry standards. Their services include truck scale inspection, certification, and repair services, supporting the long-term reliability of your truck scale systems. With a team of experts, Bwer Company ensures seamless truck scale installation and maintenance, keeping your operations running smoothly. For more information on truck scale prices, installation costs, or to learn about their range of weighbridge truck scales and other products, visit Bwer Company’s website at bwerpipes.com.