የፍቺው መዘዝ

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፍቺ በልጆች ላይ ከባድ የስነ ልቦናና አካላዊ ጉዳት ያስከትላል። ወላጆቻቸው የተፋቱባቸው ልጆች ቁጡ ሊሆኑ፣ በጭንቀት ሊዋጡና የመንፈስ ጭንቀት ሊይዛቸው ይችላል። ባሕርያቸው ሊበላሽ ይችላል፤ በትምህርታቸው ወደኋላ ሊቀሩ ወይም ሊያቋርጡ ይችላሉ። በቀላሉ በበሽታ መ«ቃቱም እንዳለ ሆኖ። ከዚህም ሌላ ብዙ ልጆች፣ ወላጆቻቸው በመፋታታቸው ጥፋተኝነት ይሰማቸዋል፤ የተፋቱት በእነሱ ምክንያት እንደሆነ ወይም ፍቺውን ማስቀረት ይችሉ እንደ ነበር ያስባሉ።

ፍቺ፣ ልጆቹ ካደጉ በኋላም ተጽዕኖ ሊያደርግባቸው ይችላል፤ ወላጆቻቸው የተፋቱባቸው ልጆች በራሳቸው መተማመን እንዲሁም ሌሎችን ማመን ሊከብዳቸው ይችላል። በተጨማሪም እንዲህ ያሉት ልጆች ትዳር ከመሠረቱ በኋላ ችግር ሲያጋጥማቸው የመፋተታቸው አጋጣሚ ሰፊ ነው።

ለመፋታት የሚያስቡ አንዳንድ ሰዎች፣ ፍቺ ለልጆቻቸው የተሻለ እንደሆነ ቢሰማቸውም ጥናቶች ይህን አይደግፉም። የልጆች ደህንነት ባለሙያ የሆኑት ፔነሎፒ ሊክ “ፍቺ የልጆቹን ሕይወት ያተራምሰዋል” በማለት ጽፈዋል።

በዛሬው የተናጋሪው ዶሴ አምድ ላይ ስለፍቺ ልናወራ የወደድነው ወላጆቻቸው በፍቺ ተለያይተው እናት ባገባችው ባል የተነሳ የተለያዩ ጥቃቶች ስለደረሱባቸው ሕፃናት ታሪክ ልናካፈላችሁ በመሆኑ ነው። ይህን ታሪክ ከአዲስ አበባ ፖሊስ መዝገብ ቤት ያገኘን ሲሆን፤ ለማህበረሰቡ በሚያስተምር መልኩ ይቅረብ ብለው ፍቃዳቸውን ስለሰጡን ከልብ እናመሰግናለን።

የቀደመው ትዳር እሰጣ ገባ

ባልና ሚስቱ ንትርካቸው በዝቶ መግባባት ስለተሳናቸው ብንፋታ ልጆቻችን ደስተኛ ይሆናሉ ብለው ማሰብ ጀምረዋል። መለያየታቸው ልጆቹ በየቀኑ የሚሰሙት ጭቅጭቅ እንደሚቀርላቸው ቢያስቡም ልጆቹ የሚፈልጉት ነገር የተለያየ ሊሆን እንደሚችል አላሰቡም ነበር። ለመፋታት የሚያስቡት ወላጆች የልጆቻቸው ስሜትና ፍላጎትን ሳይጠብቁ፤ ይበልጡኑ ለደህንነታቸው ሳይጨነቁ አዲስ ሕይወት መጀመር ፈልገዋል።

የወላጆች ፍላጎት ይህ ቢሆንም ልጆቹ ግን በአብዛኛው ሕይወታቸው ባይቀየርና ከአባትና ከእናታቸው ጋር አብረው ቢኖሩ ይመርጡ ነበር። የልጆቹ ምርጫ ምንም ይሁን ምን ባልና ሚስቱ ወስነው ተፋቱ። ያን ጊዜ እልህና ንዴት የልጆቻቸውን የወደፊት ህይወት እንዳይመለከቱ አድርጓቸው ነበር። ከልጆቹ ሥነ ልቦና በላይም ደህንነታቸውን ስለመጠበቅ ምንም አላሰቡም ነበር። በዚህም ምክንያት ሚስት ያለምንም ማንገራገር ከባለቤቷ ጋር እያለች የጀመረችውን ግንኙነት በትዳር አጥብቃ ቀጠለች።

ተለያይቶ ልጅን ማሳደግ ያስከፈለው

አንዳንድ የተፋቱ ሰዎች ልጅ የማሳደግ ኃላፊነታቸውን እኩል በመጋራት፣ አብረው ቢኖሩ ኖሮ በሚያደርጉት መንገድ ልጃቸውን ለማሳደግ ይጥራሉ። ሆኖም የተፋቱ ወላጆች ለየብቻ ሆነው ልጃቸውን ማሳደግ ቀላል አይሆንላቸውም። የዛሬ ባለታሪኮቻችን ቤት የተከሰተውም ይህ ነበር። ባልና ሚስቱ እንደተለያዩ የማሰቢያ ጊዜ እንኳን ሳይወስዱ ነበር አዲስ የትዳር አጋር ወደመፈለግ የገቡት።

ከልጆቻቸው እኩል አዲሱን ቤታቸውን ለማድመቅ ስለሚጥሩ ልጆቹ ላይ የሚመጣውን ጫና ለመመልከት አልቻሉም ነበር። ልጆቹ ቁጡ መሆን ከመጀመራቸውም ባሻገር፣ በጭንቀት ሲዋጡና የመንፈስ ጭንቀት ሲይዛቸው ታይቷል። በፍቺው የተነሳ ባሕሪያቸው ሲበላሽ፤ በትምህርታቸው ወደኋላ ሲቀሩ ወይም ሊያቋርጡ ሲዳዱ፤ በቀላሉ በበሽታ ሲጠቁና ሲታመሙ እናት አዲሱን ቤቷን ለማድመቅ ደፋ ቀና ትል ስለነበር ልብ አላለቻቸውም ነበር።

ልጆቹ፣ ወላጆቻቸው በመፋታታቸው የደረሰባቸው የሥነልቦና ጫና ሳያንስ ራሳቸውን ጥፋተኛ አድርገው ማሰባቸውም ሌላው አስቸጋሪ ነገር ነበር። ወላጆቻቸው የተፋቱት በእነሱ ምክንያት እንደሆነ ወይም ፍቺውን ማስቀረት ይችሉ እንደነበር እያሰላሰሉ ራሳቸውን ሲያሰቃዩ ውለው ያድራሉ።

ልጆች ወላጆቻቸው ከተፋቱ የተቀበሉት መከራ

ልጆቹ በተለያየ መልኩ በሥነ ልቦና ተጎድተው ራሳቸውን እንደጥፋተኛ እየቆጠሩ ሲሰቃዩ ከመክረማቸው በላይ ጠባቂ አጥተው ያላሰቡት መከራ ይወርድባቸው ጀመር። መከታ የሆነው አባታቸውን ካጡ በኋላ ጠባቂ ተከላካይ አጥተዋል። እናታቸውም እልህና ንዴት በተቀላቀለበት ፍቅር መሰል ነገር ውስ_ ስላለች ልጆቿ ላይ እየደረሰ ስላለው ነገር ልብ ማለት አልቻለችም ።

ወትሮም ብልግና መገለጫው የሆነው ነውረኛው የልጆ– እንጀራ አባት ሕፃናቱን ለእኩይ ፍላጎቱ ማስፈፀሚያ ለማድረግ ይመለከታቸው ጀመር። የሚስቱ እሱ ላይ ያላት መተማመን መጨመር ልጆቹን እንደፈለገ ቢያደርግ በጥፋተኝነት ሊጠየቅ እንደማይችል አስቧል።

ልጆቹን በክፉ ሃሳብ የተመኘው ይህ ሰው ምቹ ቀንና ሰአት በመጠበቅ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው አቢሲኒያ ትምህርት ቤት አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ያሰበውን ተግባር ፈፀመ። እናት ሥራ አምሽታ የምትመጣበትን ቀን የተጠቀመው Yህ ሰው ጥር 01/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት ላይ የ10 ዓመቱን የሚስቱን ልጅ (የእንጀራ ልጁ) ላይ ግብረ ሰዶም ፈጸመበት።

እናቱ እያለች በፍቅርና በትህትና የሚመለከተው የአባቱ ምትክ እንደሆነ በሚያስበው ሰው ምን እየተፈፀመበት እንደሆነ እንኳን ያልገባው ሕፃን በእንጀራ አባቱ ግብረሰዶም ተፈፀመበት። Yህ አልበቃው ያለው እንጀራ አባት የወንዱን ልጅ ታላቅ ሴት ልጀ መፈለግ ጀመረ።

ወንድሟ አጥፍቶ እየተቀጣ የመሰላት ልጅ የወንድሟ ቅጣት ቀላል እንዲሆንለት እየፀለየች በነበረችበት መኝታ ክፍል ውስጥ እንጀራ አባቷ ያልተገባ አስተያየት ሲያያት ደነገጠች። በልቧ ማምለጥ ብትፈልግም በር ላይበመቆሙ የተነሳ ሳይሳካላት ቀረ። ያን ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ክፉ ጅራፉን ያሳረፈባት ልጅን በማስፈራራት ሲደጋገም እንደነበረ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የ13 ዓመቷን የሚስቱ ልጅ (የእንጀራ ልጁ) ላይ ሕጋዊ ሚስቱ የማትኖርበትን ጊዜ እየጠበቀ በተለያየ ሰዓትና ቀን ለማንም ብትናገሪ እገልሻለሁ በማለትና በማስፈራራት አፏን በጨርቅ እያፈነ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሲፈፅምባት ቆየ።

ወንዱ ልጅ በተፈፀመበት አስገድዶ መድፈር የተነሳ በጣም ሲታመመ ሐኪም ቤት የወሰደችው እናት ልጇ የሆነው ነገር ሲነገራት ነበር ከእንቅልፍ የመባነን ያህል የነቃችው። ይህ ሁሉ ሲሆን አለማጤኗ እጅግ ያስቆጫት እናት ጅብ ከሄደ ውሻ ጮ¡ የሚሉት ነገር ደርሶባት እጅግ በጣም ከባድ ሀዘን ውስጥ ወደቀች።

እያንዳንዱ ድርጊት በራስዋ _ፋት እንደተፈፀመ ብታውቅም ይህን የብልግና _ግ የሆነውን ሰው በሕግ ከመጠየቅ የሚያግዳት ሰው ባለመኖሩ ለፖሊስ አመልክታ በቁጥጥር ስር እንዲውል አስደረገችው ከረፈደ የነቃችው እናት ልጆቿ በሕክምና እንዲረዱ ካደረገች በºላ ለሥነልቦና ድጋፍ ወደቀድሞ ማንነታቸው እንዲመለሱ ጣረች።

የፖሊስ ምርመራ

ፖሊስ ማመልከቻው እንደደረሰው ጊዜ ሳያጠፋ በቦታው ተንቀሳቅሶ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አዋለው። ወንጀሉን እንዳልፈፀመ እየማለና እየተገዘተ ቢናገርም በሕፃናት ጉዳይ ድርድር የለም ያለው ፖሊስ እያዳፋ ይዞት ወደ ጣቢያ ይወስደዋል።

በሕክምናው ሂደት የመድፈር ወንጀል መፈፀሙ ከመረጋገጡም በላይ በልጆቹ አካል ክፍል ውስጥ በተደረገ የዘረመል ምርመራ የሰውየው የዘር ፍሬ በመገኘቱ የተነሳ ያለምንም ማንገራገር እሱ ስለማድረጉ ታወቀ። ሰውየው ማስረጃው ከተገኘ በኋሏ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ድርጊቱን ሙሉ በሙሉ ያላመነ በመሆኑ የሰው እና የሰነድ ማስጃዎቹን በመጨመር ወንጀለኛነቱ ተረጋገጠ።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚስቱ ልጆች (የእንጀራ ልጆቹ) በሆኑ የ10 እና የ13 ዓመት ወንድና ሴት ሕፃናት ላይ የግብረ-ሶዶም ጥቃትና የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ይህ ሰው የሕክምና ምርመራው የተጠቂዎቹ ቃል ተጨምሮበት መረጃው ተጠናቀረ። ፖሊስ ምርመራውን እንዳጠናቀቀ የዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት ላከ።

የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ

የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ሀብታሙ ገብረ ጊዮርጊስ ገብረስላሴ የተባለው ተከሳሽ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 631(1) (ለ) እና 4 (ሀ) እንዲሁም አንቀፅ 620(2) (ሀ) እና (ለ) ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፉ በሁለት ወንጀሎች ላይ ክስ ተመስርቶበታል ።

ተከሳሹ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው አቢሲኒያ ትምህርት ቤት አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ

ቤታቸው ውስጥ ጥር 01/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት ላይ የ10 ዓመቱን የሚስቱን ልጅ (የእንጀራ ልጁ) ላይ የግብረ ሰዶም የፈጸመበት እንዲሁም በሁለተኛ ክስ ላይ ደግሞ የ13 ዓመቷን የሚስቱ ልጅ (የአንጀራ ልጁ) ላይ ሕጋዊ ሚስቱ የማትኖርበትን ጊዜ እየጠበቀ በተለያየ ሰዓትና ቀን ለማንም ብትናገሪ እገልሻለሁ በማለትና በማስፈራራት አፏን በጨርቅ እያፈነ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ይፈፅምባት እንደነበር የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ያስረዳል።

የዐቃቤ ሕግን ክስ የተመለከተው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 7ኛ ምድብ ወንጀል ችሎት ለተከሳሽ ክሱ ተነቦለት የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ድርጊቱን ሙሉ በሙሉ ያላመነ በመሆኑ ዐቃቤ ሕግ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎቹን አቅርቦ አሰምቷል:: በዚህም መሠረት ፍርድ ቤቱ እንዲከላከል የሰጠውን ብይን ተከትሎ ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግን ማስረጃዎች ማስተባበል ባለመቻሉ በተከሰሰበት ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ በሚል የጥፋተኝነት ውሳኔ ሊተላለፍበት ችሏል::

ውሳኔ

ዐቃቤ ሕግን ክስ የተመለከተው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 7ኛ ምድብ ወንጀል ችሎት ለተከሳሽ ክሱ ተነቦለት የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ድርጊቱን ሙሉ በሙሉ ያላመነ በመሆኑ ዐቃቤ ሕግ የሰው እና የሰነድ ማስጃዎቹን አቅርቦ አሰምቷል፡፡

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ እንዲከላከል የሰጠውን ብይን ተከትሎ ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግን ማስረጃዎች ማስተባበል ባለመቻሉ በተከሰሰበት ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ በሚል የጥፋተኝነት ውሳኔ ሊተላለፍበት ችሏል፡፡ ውሳኔውን ለመስጠት የተሰየመው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 7ኛ ምድብ ወንጀል ችሎት ግራ ቀኝ የቀረቡትን የቅጣት አስተያየቶች ከግምት አስገብቶ ተከሳሹን በ16 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

አስመረት ብስራት

አዲስ ዘመን ሰኔ 1/2016 ዓ.ም

 

 

 

Recommended For You