ልጆች እንዴት ናችሁ? በዚህኛው አምድ ላይ ታዋቂ ፈላስፋ ዎችን፣ ጀግና፣ አገር መሪዎች፣ ሳይንቲስ ቶችን፣ ተመራማሪዎችና ለዓለም ስልጣኔ የበኩላቸውን ድርሻ የተወጡ ሰዎችን እናስ ተዋውቃችኋለን። እስቲ ልጆች የዓለም ስልጣኔ እዚህ እንዲደርስ ትልቅ ድርሻ አላቸው የምትሏቸውንና ከዚህ ቀደም እናንተ ከምታውቋቸው ሰዎች መካከል ጥቂቶችን አስታውሱ።
በግዜው ብዙ ሴቶች የትምህርት እድል በማያገኙበት ወቅት ተምረው ሀገራቸውን ከጠቀሙ ጥቂት ሴቶች መካከል አንዷ ናቸው። በህግ ትምህርት ኮሌጅም በሚማሩበት ወቅት ብቸኛ ሴት ተማሪ ነበሩ። ነገር ግን ብርቱና ለዓላማቸው ጠንካራ ስለነበሩ ከትንሽ የገጠር መንደር ተነስተው ዓለምን ማገልገል ችለዋል። እንዲሁም ከተማሩ በት የትምህርት ዘርፍ ውጭ በበርካታ ስራዎችን በመስራት ሀገራቸውን አገልግለ ዋል።
የትውልድ ዘመናቸው እ.አ.አ በ1965 ሲሆን ተወልደው ያደጉት ደግሞ አሶሳ ነው። የትምህርት ዝግጅታቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በህግ ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተ ዋል። እንዲሁም ከአሜሪካ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ተከታትለዋል። የዛሬዋ ተጽዕኖ ፈጣሪ እንግዳዬ ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ ናቸው።
• በበርካታ መስሪያ ቤቶች ከሰራተ ኝነት እስከ ከፍተኛ ሃላፊነት አገልግለዋል
• በከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ በመሆን ለብዙ ዓመት ሰርተዋል፣
• የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በሚፀድቅ በት ጊዜ በአማካሪነት አስተዋፅኦ አበርክተዋል። እንዲሁም በህገ መንግስቱ የሰብአዊና የሴቶች መብት በተሻለ መልኩ እንዲካተት ጥረት አድርገዋል፣
• የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር መስራች ናቸው፣
• በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ውስጥ በሃላፊ ነት ደረጃ ሰርተዋል፣
• በሀራችን የመጀመሪያ የሆነውን በሴቶች የተመሰረተውን እናት ባንክ መስራችና የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ናቸው። እናት ባንክ የተመሰረተው በመቶ ሃያ ሚሊዮን ካፒታል ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ ባንኩን ትርፋማ በማድረግ ስኬታማ እንዲሆን ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፣
• ከሀገራችን አልፈው በአፍሪካም ትልቅ ተቀባይነት ያገኙና በመላው ዓለም ተፅዕኖ ፈጣሪም ሆነዋል።
• በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ሀገርና ህዝብን በማገልገል ላይ ናቸው። ይህም ስራቸው አርአያ እንዲሆኑ አድር ጓቸዋል፣
አዲስ ዘመን ሰኔ 2/2011
ሞገስ ፀጋዬ