በዓይን ህመም ዙሪያ አብዛኛው ሰው ያለው እውቀት አናሳ ነው። በብዙ ጥያቄ እና መልስ እንደተረጋገጠው አብዛኛው ሰው ከምንም አካል ጉዳት በላይ ዓይን መጥፋት እንደሚያሳስበው ይናገራል። ነገር ግን የዓይን ሕክምና የሚያደርገው ሰው ብዛት እምብዛም ነው። የሚከተሉት ነጥቦች በቀዳሚነት የሚከሰቱትን የዓይን ህመሞች እና ምልክቶቻቸውን ይዳስሳሉ።
ዓይን ውስብስብ አካል ሲሆን የሚ ከተሉት አካላት ውህድ ነው፦
- ኮርኒያ (Cornea): የዓይን ውጨ ኛው ሽፋን
- አይሪስ (Iris): ቀለም ያለው የዓይን ክፍል
- ፒውፕል፡ አይሪስ መሃል ያለች ጥቁር ቀዳዳ። ዓይን ውስጥ የሚገባውን የብርሃን መጠን ትቆጣ ጠራለች
- ሌንስ፡ ዓይን ውስጥ ያለች ዲስክ።
- ሬቲና፡ የዓይን ጀርባ ያለ ሽፋን። ብርሃንን ወደ አእምሮ የሚላክ ኤሌክትሪክ መልዕክት ይቀይራል።
ግላኮማ
ዓይን ውስጥ በሚፈጠር ጫና የሚፈጠሩ የዓይን በሽታዎች በጥቅሉ ግላኮማ ይባላሉ። የተፈጠረው ጫና ኦፕቲክ ነርቭ ላይ ጉዳት ይፈጥራል። የእይታ መዳከም ይፈጠራል። ግላኮማ በሁለት ይከፈላል። ኦፕን አንግል የሚባለው የግላኮማ ዓይነት ብዙ ጊዜ የሚከሰተው ሲሆን ህመም የለውም። አንግል ክሎዠር ግላኮማ ሌላኛው የግላኮማ ዓይነት ሲሆን ሲከሰት ድንገተኛ ነው። ህመም እና የዓይን መቅላት አብረው የሚታዩ ምልክቶች ናቸው።
ግላኮማ እንደመፈጠሩ ብዙ ጊዜ ምልክት አያሳይም። የማየት ችሎታችንን ማዳከም ከጀመረ በኋላ ግን ጉዳቱ ዘላቂ ነው። ግላኮማ መፈጠሩ ሲታወቅ በዓይን ጠብታ እና ቀዶ ጥገና የበሽታውን እድገት ማዘግየት ወይም ማስቆም ይቻላል። ነገር ግን በሽታውን አስቀድሞ መያዝ ለውጤቱ የተሻለ ነው።
ግላኮማ በቤተሰባቸው ዘር ያለባቸው፣ በዕድሜ የገፉ እና ጥቁር ሰዎች ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው።
የዓይን ሞራ(Cataract)
የዓይን ሞራ ዓይን ላይ የሚፈጠር ህመም የሌለው ጉም መሰል ሽፋን ነው። ከዕድሜ ጋር የሚመጣ ህመም ሲሆን ዕድሜ በገፋ ቁጥር ሁሉም ሰው ላይ ይከሰታል። ስኳር በሽታ፣ የዓይን ጉዳት፣ አንዳንድ መድኃኒቶች እና ለአልትራቫዮሌት ጨረር መጋለጥ ለበሽታው ሌሎች መንስኤ ናቸው።
የዓይን ሞራ መፈጠሩን በቀላል ዓይን ምርመራ ማወቅ ይቻላል። የዓይን ሞራን የሚያጎላ መነጽር በማድረግ ወይም በቀዶ ሕክምና ማከም ይቻላል። በቀዶ ሕክምና ሙሉ በሙሉ መዳን የሚቻል ቢሆንም የቀዶ ሕክምና አስፈላጊነቱን እና አደጋውን ከዶክተር ጋር ተነጋግሮ ማወቅ ተገቢ ነው።
ከዕድሜ ጋር የሚመጣ የማኪውላ መዳከም (AMD)
ከዕድሜ ጋር የሚመጣ የማኪውላ መዳከም በየትኛውም ዕድሜ ሊፈጠር የሚችል በሽታ ቢሆንም ብዙ ጊዜ ዕድሜአቸው ከ60 በላይ የሆኑ ሰዎች ላይ ይፈጠራል። ይህ በሽታ ማኪውላ የሚባል ብርሃንን ለማተኮር የሚረዳ የዓይን ክፍል ላይ የሚፈጠር መዳከም ነው። ይህ በሽታ ዓይንን ባያጠፋም መሃል እይታን ይጋርዳል።
ሁለት ዓይነት አለው፦ እርጥብ እና ደረቅ። እርጥብ ኤኤምዲ የሚፈጠረው ከሬቲና በስተጀርባ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ማደግ ሲጀምሩ ነው። የደም ቧንቧዎቹ ሲያድጉ ደም እና ፈሳሽ ያንጠባጥባሉ። በዚህ ሁኔታ የእይታችን መሃል ሊጠፋ ይችላል። በሽታው የደረቁ ዓይነት ሲሆን ደግሞ ማኪውላ ውስጥ ያሉት ብርሃን የሚቀበሉ ሴሎች ቀስ በቀስ ይፈርሳሉ።
የሬቲና መለያየት(Retinal Detachment)
የሬቲና መለያየት የሚፈጠረው ከዓይን ጀርባ ያለው ሬቲና ከስሩ ካሉ አካሎች ጋር ሲለያይ ነው። ከሬቲና ጀርባ የሚፈጠር የፈሳሽ ጥርቅም መለያየት እንዲፈጠር ያደርጋል። የሬቲና መለያየት ብዙ ጊዜ
ህመም የሌለው ሲሆን ምልክቶቹ በእይታ ላይ የሚፈጠር የብርሃን መብለጭለጭ ወይም የሚንሳፈፍ እና የሚጋርድ ነገር ናቸው። ለሬቲና መለያየት ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ከ25-50 ዕድሜ ክልል ያሉ የቅርቡ ለማየት የሚቸገሩ/ኒርሳይትድ/ የሆኑ ሰዎች እና የዓይን ሞራ በቀዶ ሕክምና ያስገፈፉ ሰዎች ናቸው። ለሬቲና መለያየት ሕክምናው የጨረር ቀዶ ሕክምና ነው።
ኮንጀንክቲቪቲስ (ፒንክ አይ)
ኮንጀንክቲቪቲስ የዓይን ሽፋን ላይ የሚፈጠር መቅላት እና መታመም ነው። ብዙ ጊዜ መነሻው በኬሚካል ወይም አለርጂ ምክንያት የሚፈጠር የባክቴሪያ ወይም የቫይረስ ኢንፌክሽን ነው።
አብዛኛው የኮንጀንክቲቪቲስ ኢንፌ ክሽን የቫይረስ ኢንፌክሽን እንደመሆኑ የአንቲባዮቲክ ሕክምና አያስፈልገውም። ኢንፌክሽኑ የባክቴሪያ ከሆነ በአንቲባዮቲክ ጠብታ ወይም ቅባት ማከም ይቻላል። ኮንጀንክቲቪቲስ ከፍተኛ የዓይን አር የሚፈጥር በሽታ እንደመሆኑ ለጠብታ ዓይንን መክፈት ሊቸግር ይችላል። በዚህ ጊዜ በንጹህ ጨርቅ የተጠቀለለ በረዶ ዓይን ላይ በማስደገፍ የዓይን አሩን ማስለቀቅ ይቻላል።
ኢንፌክሽኑ ወደ ሰው እንዳይተላለፍ እጅን በሳሙና መታጠብ እና ፎጣ፣ ኮዝሜቲክስ እና የዓይን ጠብታን ከሰው ጋር አለመጋራት ተገቢ ነው።
ዩቬቲስ
ዩቬቲስ ዩቪያ የሚባለው ዓይን መሃል የሚገኘው ክፍል ሲረበሽ የሚፈጠር በሽታ ነው። ዩቪያ ለእይታ የሚያስፈልጉ ደም ቧንቧዎችን የያዘ የዓይን ክፍል ነው። የዩቬቲስ መንስኤዎች ዓይን ላይ የሚፈጠር ጉዳት፣ ኢንፌክሽኖች እና ሌላ የሰውነት አካል ላይ የሚፈጠሩ ህመሞች ናቸው። የዩቬቲስ ዋና ምልክት ዓይን ላይ የሚፈጠር የህመም ስሜት ነው። ዓይን ይቀላል እናም እይታ ላይ ብዥታ እና ጠቃጠቆ ሊፈጠር ይችላል።
የዩቬቲስ ሕክምና በመንስኤው ይወ ሰናል። ጸረ-ቃጠሎ እና አንቲባዮቲክ መድኃኒቶች ከሕመም ማስታገሻ መድኃኒት ጋር ሊታዘዙ ይችላሉ።
የዓይን አለርጂ
ከባድ የዓይን አለርጂ ዓይን ላይ ከባድ ጉዳት ሊፈጥር ይችላል። አለርጂዎች ስር የሰደደ ቃጠሎ በማስነሳት የዓይን ኮርኒያ ላይ ዘላቂ ጉዳት ሊፈጥሩ ይችላሉ። የአየር ጸባይ መቀያየር፣ ኮዝሜቲክስ፣ አቧራ እና የተለያዩ መድኃኒቶች ለዓይን አለርጂ መነሳት መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ። አንቲሂስታሚን ወይም ዲኮንጄስታንትቶችን በውስጣቸው የያዙ የዓይን ጠብታዎች ህመሙን ያስታግሳሉ። ጠብታ ህመሙን ካልቀነሰው ዶክተር ማማከር ተገቢ ነው።
ምንጭ፡– Tenegna.Com
አዲስ ዘመን ቀርዳሜ ሰኔ1/2011