የኢትዮጵያ ግብርና ብዙ የሰው ኃይል የተሰማራበት፤ የኑሮ መሰረት፣ የገጠርም ስራ እድል መፍጠሪያ የሆነ፤ ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝ፤ ለአገሪቱ ኢንዱስትሪዎች ጥሬ ዕቃ የሚያቀርብ፤ በአገሪቱ ጥቅል ምርት ውስጥ ድርሻው እያደገ የመጣ ነው፡፡ ግብርናው ለአጠቃላይ ምርት 35 በመቶ አስተዋፅኦ ማድረጉንም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ሆኖም እንዲያበረክት ከሚጠበቀውና ከተቀመጠው እቅድ አኳያ እድገቱ አነስተኛ ነው፡፡
ምክንያቱም ዛሬም ድረስ በገጠር አካባቢ በቂ ምግብ የማያገኙ 25 ሚሊዮን ዜጎች አሉ፤ ከ18 ሚሊዮን የማያንሱ ዜጎችም በዕለት ደራሽ እርዳታና ልማታዊ ሴፍቲኔት ታቅፈዋል፡፡ ግብርናው የአገር ውስጥ ፍላጎቱን ባለማሟላቱም ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ በማውጣት የግብርና ምርቶች ከውጭ ይገባሉ፡፡ ይህ ደግሞ ከግብርና ወደ ማኑፋክቸሪንግ ንዑስ ዘርፍ የሚደረገውን ሽግግር ዘገምተኛ አድርጎታል፡፡
በመሆኑም ግብርናውም ውጤታማና ምርታማ እንዲሆን ማስቻል ተገቢና አመራሩም በዚህ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ የሚያስችለው አገር አቀፍ መድረክ ሰሞኑን በአዳማ ተካሂዷል፡፡ የመድረኩ ተሳታፊዎችም በዚህ መልኩ በጋራ ችግሮችን ለይተውና የጋራ አቅጣጫ ይዘው በመግባባት መቋጨቱ በቀጣይ የግብርናውን ዘርፍ ውጤት እንዲያመጣ ከማድረግ አኳያ ጉልህ ሚና እንዳለው፤ እነርሱም በየአካባቢያቸው ይሄንኑ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡
አቶ አብዱልሰላም አብዱላሂ፣ በሶማሌ ክልል ኤረር ዞን የፊቅ ወረዳ የአርብቶ አደርና እንስሳት ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ናቸው፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት፤ ውይይቱ ጥሩና የግብርናውን ዘርፍ ችግሮችን በመለየት የቀጣይ ስራዎች ምን መሆን እንዳለባቸው የጋራ አቅጣጫ የተያዘበት ነው። በወረዳው ያለውን ግብርና በተለይም የእንስሳት ሃብት በተገቢው መልኩ ማልማትና አርብቶ አደሩ ተጠቅሞ ለአገርም መጥቀም የሚችሉበትን እድል ለመፍጠር እንዲያስቡ አድርጓቸዋል፡፡ በክልሉ ላለው ሰፊ የእንስሳት ሀብት ምርታማነትም ከጤናም ሆነ ከመኖ አኳያ ጥሩ ስራ በመስራት ከእስካሁኑ በተለየ መልኩ ህብረተሰቡ የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋገጥ፤ የእንስሳት ሃብቱም ለውጭ ገበያ የሚቀርብበት እድል ተመቻችቶ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ሂደት በተግባር ለማሳየት ተዘጋጅተዋል፡፡
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስዩም መስፍን በበኩላቸው እንደሚሉት፤ ቀደም ሲል ባሉት ዓመታት የግብርናው ዘርፍ ተረስቷል ማለት ይቻላል፡፡ አሁን የተጀመረው ስራም ምንም እንኳን ዘግየት ቢልም የዘርፉን ትንሳኤ የሚያበስር ይመስላል፡፡ ሰዓቱም የመኸር ምርት ስራ ወቅት እንደመሆኑ፤ የምርት ዘመኑን ምርታማነት ከማሳደግ አኳያ ችግሮቹን ከመለየትና የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም በማስቀመጥ ምን መሰራት እንዳለበት የጋራ ግንዛቤ ያስያዘ፤ ከግብዓትና ቴክኖሎጂ አቅርቦት ጀምሮ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የተደረጉ ውይይቶች ፍሬያማ ነበሩ፡፡
አቶ ስዩም እንደሚሉት፤ የግብርናውን ውጤታማነት ለማረጋገጥ አመራሩ ሃላፊነት ወስዶ ሚናውን እንዲወጣ መደረጉ በየደረጃው ያለው አመራር በትኩረት እንዲሰራ፤ ከፌዴራል መንግስት እስከ ቀበሌ ያለው ትስስር ጠንክሮም ህብረተሰቡን አቅፎ እንዲጓዝ የሚ ያደርገው ነው፡፡ ከአመራሩ እንደተደመጠውም አሁን በተጀመረው አግባብ የተሻለ ስራ ለማከናወን ሁሉም ተዘጋጅቷል፡፡ እርሳቸውም በወረዳቸው ይሄንኑ ያደርጋሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ የክልልም ሆነ እንደ ፌዴራል የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት ከእነርሱ የሚጠበቁ ድጋፎችን በተገባው ቃል መሰረት መተግበር፤ የግብዓት ግብይትና ማጓጓዝ ስራው እንዲቀላጠፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ አርሶ አደሩም የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈጸም የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር የእርሻ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሳኒ ረዲ በበኩላቸው እንደሚሉት፤ የመድረኩ “ለግብርና ትራንስፎርሜሽን የአመራሩ ሚና የላቀ ነው” በሚል ሀሳብ የተካሄደ ሲሆን፤ ዓላማውም ግብርናውን ለማዘመንና ለማሳደግ ትኩረት እንደሚሹ የተለዩ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ፈጥሮ ሁሉም የድርሻውን ወስዶ ወደስራ ለመግባት ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በመድረኩ በግብርናው ዘርፍ ያሉ ችግሮችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫዎች የተቀመጡበትና የስራ መመሪያ የተላለፈበት ስኬታም መድረክ ነበር፡፡
እንደ አቶ ሳኒ ገለጻ፤ ግብርናን ለማዘመንና እድገቱን ለማፋጠን ወሳኝ የሚባሉ የመንግስትንና የአመራርን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ተለይተዋል። ለምሳሌ፣ ግብርና ኢንቨስትመንት ይፈልጋል። በዝናብ ጥገኛ የሆነ ግብርና ተይዞ ግብርናው ሊዘምን አይችልም፡፡ ስለዚህ ለአነስተኛና መካከለኛ መስኖ ትኩረት በመስጠትና ሀብትም በመመደብ፤ የመስኖ አጠቃቀምን የሚያሻሽሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ደረጃ በደረጃ ከዝናብ ጥገኝነት አንድ ጊዜ ከማምረት ወደ መስኖና ወደ ሁለት ጊዜ ወደማምረት መሸጋገር ያስፈልጋል፡፡ አመራሩም ይሄን አውቆ በየደረጃው ሀብት መመደብ አለበት፡፡
ምክንያቱም ቴክኖሎጂን ማመንጨት፣ ማባዛትና ማሰራጨት ሀብት ይፈልጋል፡፡ ባለው ሁኔታ ግን ከግብርና ምርምሮች የወጡ የቆላም፣ የወይና ደጋም ሆነ የደጋ በርካታ ዝርያዎችን አሟጥጦ ወደ አርሶ አደሩ ማድረስ ባለመቻሉ የምርጥ ዘር አጠቃቀሙ አድርሰን አልተጠቀምንም። በምርጥ ዘር አጠቃቀሙ ከ30 በመቶ አልዘለለም። ይህ ማለት ደግሞ በዘር ከሚሸፈነው መሬት 30 በመቶው ብቻ ነው ምርጥ ዘር የሚያገኘው፡፡ የዚህ ዋናው ችግር ደግሞ የማባዛት አቅም ችግር በመሆኑ የመንግስት የዘር ብዜት ድርጅቶችም ሆኑ የግል ዘርፉ ኢንቨስትመንት በብድርም ይሁን በቀጥታ የበጀት ድጋፍ ይፈልጋል፡፡
በተመሳሳይ የአየር ንብረት ለውጡን ተከትሎም በሽታዎችና ተባዮች እየጨመሩ መጥተዋል፡፡ በሽታዎቹን ለመከላከልም ኬሚካል ያስፈልጋል። ይሄንንም በአገር ውስጥ ለማምረትም፣ ከውጭ ለማስገባትም ሀብት ይፈልጋል፡፡ የግብርና ሰብል ልማት ምርታማነቱን ለማሳደግ፣ የመሬትን ለምነትም ለማሻሻል፣ ማዳበሪያና ውህድ ኖራ ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም የመሬታችን 40 በመቶ በአሲዳማነት ተጠቅቷል፡፡ ለዚህ ደግሞ አሁን ባለው የቴክኖሎጂ አቅርቦት ውህድ ኖራ በአንድ ሄክታር ከ20 እስከ 30 ኩንታል አምርቶ በአፈር ላይ መቀላቀልን ይጠይቃል፡፡ ይሄም ትልቅ ኖራ የማምረትና የማጓጓዝ አቅምን ይጠይቃል፡፡
ማዳበሪያም ቢሆን በሌሎች አገራት በሄክታር የሚጠቀሙት በጣም ከፍተኛ ነው። አፈሩ የጎደለውንና ሰብሉ የሚፈልገውን ማሟላት የሚቻለው ደግሞ በማዳበሪያ ነው። በእስካሁን ሂደትም ከ40 በመቶ ያልበለጠውን የማዳበሪያ አጠቃቀምም ወደ 70ና 80 በመቶ ማድረስ፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ማምረትና ማጓዝ ካልተቻ ግብርናው ሊያድግ አይችልም፡፡ ይሄም ኢንቨስትመንት ይፈልጋል፡፡
በሌላ በኩል የመሬት ይዞታ ያለው አርሶ አደር እያረጀ ከመምጣቱና መሬት የሌለው ወጣት ከመብዛቱ ጋር በተያያዘም፤ ወጣቶች በአነስተኛ ወጪ ብድር የሚያገኙበት፤ የተሻሉ ቴክኖሎጂዎች ደግሞ የሚተሳሰሩበት፤ ራሱን ሊገለገልበትና ለሌላውም አገልግሎት ሊሰጥ የሚችልበት እድል መፍጠር ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ዘርፍ ደግሞ መንግስትም፣ የግል ዘርፉም መስራት አለበት፡፡ ለዚህም የፋይናንስና ኢንቨስትመንት ስርዓቱ መታየት አለበት፡፡
የመድረኩ መካሄድም በዚህ ላይ እንደየ ስልጣን እርከኑ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ፌዴራል መንግስቱ በዓመታዊ በጀታቸው የተለየ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተገኙበት እንደመሆኑም በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ተገቢው መልዕክት የተላለፈበትና በየደረጃውም መግባባት የተደረሰበት ነው፡፡
አቶ ሳኒ እንደሚሉት፤ የግብርና ባለሙያዎች የሚያደርጉት ጥረት ከየትኛውም ሴክተር በላይ በአርሶ አደር ማሳ ላይ እየተንቀሳቀሱ አርሶ አደር የማሰልጠን፣ በገበሬ ማሰልጠኛ ማዕከሎቻቸው ሰርተው እያሳዩ አይቶ እንዲያምን የሚያደርጉ፣ የቴክኖሎጂ ተስማሚነት ሙከራ የሚያደርጉ፤ በጥቅሉ ትልቅ ጥረት የሚጠይቅ ስራ እየሰሩ ያሉ ናቸው፡፡ ይሄ ባለሙያ ደግሞ ሞራሉ ተገንብቶና ኢኮኖሚው ሊፈቅድ የሚችለውን የደመወዝ ክፍያ ስርዓት ኖሮ እንዲተጋ መሆን አለበት፡፡ ለዚህም እንደ አገርም ወጥ የሆነና ከክልል ክልል የማይለያይ እንደ ጥረቱ የሚከፈል ስርዓት እንዲኖር ማድረግን ይጠይቃል፡፡ በዚህ ረገድም እንደ አገር በክልሎች መካከል የአሰራር ወጥነት እንዲኖረው ለማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት የአመራር ትኩረት ባለማግኘቱ የተቀዛቀዘው ግብርናም በወቅት የሚመራ እንደመሆኑ ወቅቱን መሰረት ያደረገ ስራ ማከናወን ይጠይቃል፡፡ ለዚህ ደግሞ የአመራር፣ የባለሙያና የአርሶ አደሩ ብሎም አርብቶ አደሩ እንዲሁም የባለሃብቱ ሚና በተቀናጀና በሚመጋገብ መንገድ መፈጸም አለበት፡፡ እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች የሚመለከቱ የንቅናቄ መድረኮችም በተለያየ ምዕራፍ ተዘጋጅቷል፡፡ የአዳማው መድረክም አመራሩ በዚህ በኩል የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ የሚያደርግ እንደመሆኑ፤ ለግብርና ትራንስፎርሜሽን የመንግስት በተለይም የአመራሩ ሚና ተኪ የሌለው ታውቆ መስራት እንደሚገባም ግንዛቤ ተይዟል፡፡ በዛው ልክ እንደሚሰራም መነሳሳትን የፈጠረ ነው፡፡
በመድረኩ የተባሉ ነገሮች ወደተግባር ስለመቀየራቸው በየደረጃው የማረጋገጥ ስራ የሚከናወን ሲሆን፤ የግብርና ሚኒስቴር ከክልሎች ጋር ተቀናጅቶ ድጋፉን ወረዳና ቀበሌ ላይ ማዕከል ለማድረግ በመስማማት ወደስራ ተገብቷል፡፡ የቀበሌ ባለሙያዎችንም በጋራ ማሰልጠን ተጀምሯል። አንዳንድ ክልሎችም የአርሶ አደር ስልጠና ጀምረዋል። ሚኒስቴሩም ይሄን እየተከታተለና እየደገፈ ሲሆን፤ አሁን በተወሰነው መሰረትም በአዲሱ በጀት ዓመት በጀት ሲያዝ ምን ያክል በጀት ለግብርናው ተመደበ፤ ለባለሙያዎችስ የደመወዝና ጥቅማጥቅም አሰራሩ ምን ያክል ተግባራዊ ሆነ፤ ግብዓት ለማቅረብስ ክልሎች፣ ዞኖችና ወረዳዎች እንደየስልጣን እርከናቸው እየተንቀሳቀሱ ነው? የሚለው በትኩረት የሚታይ ይሆናል፡፡ በመድረኩም በዚህ ላይ ከመግባባት ተደርሷል፡፡
በታች በአሸዋ ሥር በተቀበሩ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ ካርበን ውስጥ ጥቂት ብቻ በየዓመቱ የካርበን ዑደት በማጠናቀቅ በእሣተ ገሞራ አማካኝነት ወደ ከባቢ አየር ይለቀቃል። እንደ ከሰል፣ ነዳጅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ የማውጣትና በማቃጠል ተግባራት ላይ ያሉ ሰዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ካርበን እንዲለቀቅ በማድረግ የተፈጥሮው የካርበን ዑደት እንዲዛባ ያደርጋሉ፡፡
የግሪን ሐውስ ጋዝ ተጽዕኖን ስንመለከት፣ የኢንዱስትሪ አብዮት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሰው ሠራሽ ምክንያቶች የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ማስተዋል ይቻላል። በከባቢ አየር ውስጥ ያለው ክምችትም ጨምሯል፡፡ በከባቢ አየር ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የግሪንሀውስ ጋዝ ክምችት መኖር ወደ ህዋ ተንፀባርቆ ይመለስ የነበረው የፀሐይ ብርሃን ሙቀት በምድር ከባቢ አየር ውስጥ እንዲቀር ያደርጋል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ የዓለም የሙቀት መጠን እንዲጨምርና የአየር ንብረት ለውጥ መከሰት ምክንያት ይሆናል፡፡ ከፀሐይ ኃይል ውስጥ ግማሽ ያህሉ በከባቢ አየር ውስጥ በማለፍ በምድር ገጽ ይሰበሰባል። ከዚያም የምድር ገጽ የሙቀት ኃይሉን መልሶ ወደ ህዋ ያንፀባርቀዋል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የሙቀት ኃይሉ በአብዛኛው በከባቢ አየር ውስጥ በሚገኙ የግሪንሀውስ ጋዞች ሞሎክዮሎች ይሰበሰባል፡፡ የዚህ ሂደት ውጤትም የምድር ገጽ ሙቀት እንዲኖረውና የሙቀቱም መጠን ሕይወት በምድር ላይ ለመኖር በሚያስችል ደረጃ ብቻ እንዲገደብ ያደርጋል፡፡ ወደ ከባቢ አየር ከፍተኛ የሆነ የካርበን ልቀት የሚኖር ከሆነ ግን ይህ ከባቢ አየርን የሸፈነው የግሪንሀውስ ጋዞች ክምችት ከሚፈለገው መጠን በላይ እንዲሆን በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የፀሐይ ሙቀት እንዲፈጠር ያደርጋል። የዓለማችን አማካይ የሙቀት መጠን መጨመርም በዓለም የተፈጥሮ ሥርዓቶች ላይ ብዙ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ያስከትላል። በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚፈጠሩ ተጽእኖዎችን ለመከላከልና ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ ለመኖር ደግሞ የደኖቻችንን ከጥፋት መታደግና የደን ሽፋንን ማሳደግ የግድ ይላል፡፡
አዲስ ዘመን ግንቦት 26/2011
ወንድወሰን ሽመልስ