ህይወት ፈተና ነች፤ ፈተናን ለማለፍ ደግሞ ጥንካሬና ጽናትን ይጠይቃል። ኑሮ እንደጋራ ከብዶ አልገፋ ቢልም ብልህ ተስፋ አይቆርጥም፤ አማራጮችን ያማትራል እንጂ። ስሙን የማላስታውሰው ፈላስፋ ህይወትን ሲገልጻት “ ህይወት ተስፋ ማለት ነች፤ ሰው ተስፋው የተሟጠጠ ዕለት በስጋው ቢቆምም በመንፈሱ ግን ሙት ነው” ይላል።
እውነት ነው ህይወትና ተስፋ እጅግ የተቆራኙ መሆናቸውን በርካታ ማሳያዎችን ማንሳት ይቻላል። የሰው ልጅ ነገን ተስፋ በማድረግ መውጣት መውረዱ፣ መቀመጥ መነሳቱ፣ ላይ ታች ማለቱ እንደው መዋተቱ ነገን አሻግሮ በተስፋ ማየት በመቻሉ ብቻ ነው። ሰውን ከሌላ እንሰሳ የሚለየው ዋናው ነገር ትላንትን በትዝታ ነገን ደግሞ በተስፋ መኖር በመቻሉ ነው። ነገን ተስፋ አድርገው ለሚጥሩ ሰዎች ጭለማው ቢበረታም ብረሃን መምጣቱ ግን አይቀርም።
ባለተስፋና በለራዕይ ከሆኑ እህቶቻችን መካከል ዛሬ አንዷን እናስተዋውቃችሁ። በመዲናችን አዲስ አበባ መሐል እምብርት በሆነው አራት ኪሎ አካባቢ ሻይ በማፍላት የምትተዳደረዋን ወጣት የዓለምዘርፍ ካሳሁንን። የዓለምዘርፍ፤ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት የሚገኘውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ የሰራተኞች ክበብ ህንፃን ተገን አድርጋ በጎዳና ላይ ዕለት ከዕለት ጣዕሙ የማይቀየረውን ቆንጆ ትኩስ ሻይ ለደንበኞቿ ለማቅረብ ትውተረተራለች። ምንም እንኳን ቦታው ምቾት የሌለውና ከፀሐይና ከዝናብ ሊታደጋት ባይችልም እንጀራ ነውና አረፍ የምትልበት እንኳን ከሌለበት ከዚሁ ከፕሬስ ህንፃ አካባቢ ውር ውር ስትል ላስተዋላት የስራን ክቡርነት ታስተምራለች።
የዓለም ዘርፍ፤ ተወልዳ ያደገችው ጎጃም ፍኖተ ሰላም አካባቢ ነው። በትውልድ ቦታዋ ፍኖተ ሰላም የአስረኛ ክፍል ትምህርቷን አጠናቅቃ በግል ኮሌጅ የክሊኒካል ነርሲንግ ትምህርቷን ቀጠለች። ይሁን እንጂ፤ ሁለተኛ ዓመት የኮሌጅ ተማሪ እያለች አንድ ዘመዷ ቤተሰብ ከምታስቸግሪ ከኔ ጋር እየሰራሽ ትማሪያለሽ በማለት የሁለተኛ ዓመት የኮሌጅ ትምህርቷን አቋርጣ ወደ ጅግጅጋ እንድታቀና ምክንያት ትሆናለች። የዓለም ዘርፍ፤ ኑሮን በጅግጅጋ ብታደርግም እንደተባለው ትምህርቷን መቀጠል ግን አልቻለችም። በመሆኑም ጉዞዋን ከጅግጅጋ ወደ አዲስ አበባ አቀናች።
ኑሮ በአዲስ አበባ እንዳሰበችው ቀላል ባይሆንም በልቶ ለማደር ያገኘችውን ስራ መስራት እንዳለባት በማመን በወር 1‚000 (አንድ ሺህ) ብር በግለሰብ ግምጃ ቤት ውስጥ ተቀጥራ መስራት ጀመረች። ይሁን እንጂ፤ የምታገኘው ገንዘብና የአዲስ አበባ የቤት ክራይ ዋጋ ፍፁም አልጣጣም በማለቱ ሕይወት ያንገዳግዳት ጀመር። በዚህ መሐል አንድ ጓደኛዋ ሻይ ቡና አፍልታ ብታዞር የተሻለ እንደሆነ ትነገራትና የመስሪያ ዕቃዎችን ገዝታ በመስጠት ስራውን እንድትጀምር ታደርጋታለች።
ለመጀመሪያ ጊዜ ሻይ በፔርሙዝ እያዞረች መሸጥ የጀመረችው እዚሁ አራት ኪሎ አካባቢ ነው። በመሆኑም ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ጋዜጣ የሚያወጡና በአካባቢው የሚገኙ ሰዎች ቀስ በቀስ ደንበኞቿ እየሆኑ በመምጣታቸው በየጊዜው ሻይ እንድታመጣላቸው እንደጠየቋትና አካባቢውንም በቀላሉ እንደለመደችው ትናገራለች። ታዲያ በዚሁ አካባቢ ካሉ ደንበኞቿ ጋር የምትገናኘው በእጅ ስልኳ በመሆኑ ሲደውሉላት ሻይና ብስኩቷን በመያዝ በተጠራችበት ሁሉ ብር እያለች ደንበኞቿን ታስተናግዳለች።
ሻይ የምታፈላበት ቦታ ምቹ ካለመሆኑም ባሻገር ደንብ አስከባሪዎች በየጊዜው እንድትነሳ ያስገድዷት እንደነበርና ስራውን ልታቆም እንደነበር የምትናገረው የዓለም ዘርፍ፤ ደንበኞቿ ሻይ ሲፈልጉ በእጅ ስልኳ የሚጠሯት በመሆኑና ሻይ የምታፈላበትንም ቦታ የኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ የሰራተኞች ክበብ በመፍቀዱ ስራውን መቀጠል እንደቻለች ትናገራለች። ለዚህም የኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲን የሰራተኞች ክበብ ኃላፊ ታመሰግናለች።
የዓለም ዘርፍ፤ የሻይና የብስኩት ደንበኞች እዚሁ አራት ኪሎ ብርሃንና ሰላም አካባቢ ከሚገኙ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲን ጨምሮ በአብዛኛው አዋሽ ባንክ፣ ድንቅ ስራ ህንፃ እንዲሁም የነጃጅ ማደያዎች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች እንደሆኑ ትናገራለች። ለነዚህ ደንበኞቿም አንድ ብስኩት ከአከፋፋዮች በሶስት ብር ከሃምሳ ሳንቲም ተረክባ ሃምሳ ሳንቲም በማትረፍ በአራት ብር ስትሸጥ አንድ ብርጭቆ ሻይ ደግሞ ሁለት ብር በመሸጥ በቀን ቢበዛ እስከ 200 መቶ ብር ገቢ እንደምታገኝ ትናገራለች።
ከአብዛኛው ደንበኞቿ መካከል የኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ ሰራተኞች እስከ ስድስተኛ ፎቅ ባለው ህንፃ ላይ ይገኛሉ። ለእነዚህ ሰራተኞች አገልግሎት ለመስጠት ደግሞ የወጣቷ ስልክ በተደጋጋሚ ይጠራል፤ ወጣት የዓለም ዘርፍ፤ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ለጥሪው ሁሉ መልስ ትሰጣለች። የስልኳ ጥሪ አጅጉን ቢበዛ አይሰለቻትም፤ ምክንያቱም ስልኳ በጠራ ቁጥር ሻይና ብስኩት የመሸጥ ዕድሏ እየሰፋ እንደሚሄድ ታውቃለችና በቀን ቢያንስ ከአምስት ጊዜ በላይ ከፎቅ ፎቅ በመመላለስ ፈገግታ በተሞላበት ገጿ ደንበኞቿን ታስተናግዳለች።
በሌሎች ህንጻዎች ደንበኞቿ አስከ ስምንተኛ ፎቅ ድረስ ያሉ በመሆናቸው ላይ ታች ማለቱ ምን ያህል አድካሚና አሰልቺ እንደሆነ ከፊቷ ገፅ ላይ ይነበባል። ያም ሆኖ ግን፤ እያንዳንዱ ደንበኛዋ ዘንድ ለመድረስ የምታደርገው ጥረት ብርታቷንና ጥንካሬዋን ይናገራል። ከዚህም ባሻገር ለስራ ያላት ጉጉት፤ ተነሳሽነትና ታዛዥነቷን ላስተዋለ፤ አሁን ካለችበት የተሻለና ምቹ የመስሪያ ቦታ ብታገኝ ነገ ከነገ ወዲያ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ የምትችል ጠንካራ ወጣት መሆኗን ይመሰክራል።
ዕለት ዕለት ሻይ በመሸጥ በምታገኘው ገቢ የቤት ኪራይ በወር 1‚200 ብር እየከፈለች እራሷን የምታስተዳድረው የዓለም ዘርፍ፤ ከራሷ አልፋ ታናሽ እህቷን ለማስተማር ያደረገችው ጥረት ግን እንዳልተሳካ ትናገራለች። እርሷ እንደምትለው፤ ለትምህርት ካለኝ ጉጉት የተነሳ እህቴም እንደእኔ ትምህርቷን እንዳታቋርጥ በማለት እንድትማር ከፍተኛ ፍላጎት ነበረኝ። በመሆኑም ከማገኘው አነስተኛ ገቢ ለእኔ ሳይበቃ በወር አቅሜ የፈቀደውን እገዛ አደርግላት ነበር። ነገር ግን እሷም ትምህርቷን አቋርጣ ትዳር ያዘች። በዚህም እኔ ያጣሁት የትምህርት ዕድል ዳግም በታናሽ እህቴ ሕይወት ውስጥ ጠወለገ ትላለች።
የዓለም ዘርፍ፤ ዛሬ ሻይ በመሸጥ የምታገኘው ገቢ ከዕለት ጉርሷ፤ ከዓመት ልብሷና ከቤት ኪራይ የሚያልፍና በቂ የሚባል ገቢ ቢሆንላት በኢኮኖሚ ችግር ያቋረጠችውን ትምህርት የመቀጠል ሀሳብ እንዳላት ትናገራለች። ይህን ምኞቷን ለማሳካትም የያዘችውን ስራ ሳትንቅ አጥብቃ በመስራት ነገን የተሻለ ለማድረግ ባላት አቅም ሁሉ ጥረት እያደረገች ትገኛለች። ከትምህርት ቤት ጓደኞቿ እሷ ወደኋላ መቅረቷ የሚቆጫት በመሆኑ፤ “ይህን ቁጭቴን መወጣት የምትችለው ደግሞ ሁኔታዎች ተመቻችተውልኝ ትምህርቴን መቀጠል ስችል ነው” ትላለች።
ለዚህ ጥረት መሳካት ታዲያ የወጣቷ የግል ጥረት እንዳለ ሆኖ ውጫዊ የሆኑ የተለያዩ ችግሮች እንዳሉባት ትናገራለች። ከነዚህም መካከል የመስሪያ ቦታዋ ምቹ ባለመሆኑ ለዝናብና ለፀሐይ መጋለጧ፤ የስኳር ዋጋ መጨመሩና እንደልብ አለመገኘቱ ወዘተ. በዋናነት የሚጠቀሱ ችግሮች መሆናቸውን ታብራራለች። አሁን ባለው ሁኔታ እነዚህን ችግሮች በመጋፈጥ ለመኖር ያህል እየሰራች እንደምትገኝ ነገር ግን ከዕለት ጉርሷ አልፎ ያቋረጠችውን ትምህርት እንደማያስቀጥላት ትናገራለች።
ይሁንና የዓለም ዘርፍ፤ አሁን ባለችበት ሁኔታም ቢሆን የነገን ማንም አያውቅም በማለት ተስፋ ሳትቆርጥ ምኞቷን ለማሳካት ጥረት ታደርጋለች። ሌሎች ወጣቶችም ቢሆኑ ያላቸውን ዕድል በሙሉ አሟጥጠው በመጠቀም ስራ ሳይንቁና ተምሬያለሁ አልተማርኩም ሳይሉ ማንኛውንም ስራ ቢሰሩ ካሰቡበት ይደርሳሉ። በዚህም በቅድሚያ እራሳቸውን ይጠቅማሉ፤ በመቀጠልም ለቤተሰቦቻቸው ይተርፋሉና በተለይም በወጣትነት ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ በሙሉ ባገኙት አጋጣሚ ጠንክረው ቢሰሩ መልካም ነው በማለት ምክሯን ታካፍላለች።
አዲስ ዘመን ጋዜጣም ወጣት የዓለም ዘርፍ፤ እራሷን ለመለወጥ የምታደርገውን ጥረት እያደነቀ በቀጣይ የተሻለ ነገር እንዲገጥማትና ያቋረጠችውን ትምህርት ቀጥላ ካሰበችበት እንድትደርስ ይመኛል። ከዚህም ባሻገር ወጣቶች ማንኛውንም ስራ በየትኛውም ቦታና ጊዜ መስራት እንደሚቻል ከወጣቷ ሕይወት በመማር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚ ብትሆኑ መልካም ነው እያልን በዚሁ እናብቃ።
ጣ ወደ ጅግጅጋ እንድታቀና ምክንያት ትሆናለች። የዓለም ዘርፍ፤ ኑሮን በጅግጅጋ ብታደርግም እንደተባለው ትምህርቷን መቀጠል ግን አልቻለችም። በመሆኑም ጉዞዋን ከጅግጅጋ ወደ አዲስ አበባ አቀናች።

አዲስ ዘመን ግንቦት 14/2011
ፍሬህይወት አወቀ