መንግስት የፌዴራል አስፈፃሚ አካላትን በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 እንደገና ሲያዋቅር ቀደም ሲል በአዋጅ ቁጥር 916/2008 ከተቋቋሙት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒኪና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ እንዲሁም ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ደግሞ የሳይንስ ዘርፍን በመያዝ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ተብሎ ተቋቁሟል፡፡ በስሩም የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂክ ማዕከል፣ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኢንስቲቲዩት ተጠሪ ተቋማት ሆነው ተሰይመዋል፡፡
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ከተቋቋመ በኋላ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከትምህርት ተደራሽነት፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት እንቅስቃሴና አዳዲስ ግንባታ በተመለከተ፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እንቅስቃሴ እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካባቢ የክትትልና ቁጥጥር ስራ አከናውኗል፡፡ በተጨማሪም ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደት ለማረጋገጥ፣ የትምህርት ጥራት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የሀብት አጠቃቀም ላይም በርካታ ስራዎችን አከናውኗል፡፡ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ያቀረቡት የዘጠኝ ወራት ሪፖርት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የትምህርት ተደራሽነት
የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥና ፍትሀዊ ተሳትፎን ለማጎልበት በተሰራው ስራ እስካሁን 50 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በማስተማርና በምርምር ስራዎች ላይ የሚገኙ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 45 ዩኒቨርሲቲዎች ተጠሪነታቸው ለሚኒስቴሩ ነው፡፡ ቀሪዎቹ ደግሞ ለተለያዩ ተቋማት ተጠሪ ናቸው፡፡ በአገሪቱ 174 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ይገኛሉ። የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትን በሁሉም ወረዳዎች ተደራሽ ለማድረግ በታቀደው መሰረት አስር ተቋማት በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡
የነባርና አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታና የመሰረተ ልማት አቅርቦት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን የአስራ አንድ ዩኒቨርሲቲዎች አንደኛ ምዕራፍ ህንፃ ግንባታ ወደ መጠናቀቁ ተዳርሷልታቦቱ ከዋሻው ውስጥ ከመውጣቱ በፊት በእምብርክክ የሚያስኬደውን መንገድ ቁልቁል መውረድና ሽቅብ መውጣት ይጠይቃል፡፡ በ2010 ዓ.ም መጨረሻ የተጀመሩ ህንፃዎች አፈፃፀማቸው በአማካይ 73 በመቶ፣ ጊዜያዊ የተማሪዎች ማደሪያ አፈፃፀም 93 በመቶ፣ የአዳቡልቱ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ 17 በመቶ እንዲሁም የቦረና ዩኒቨርሲቲ ግንባታ 30 በመቶ ደርሷል፡፡ ለዩኒቨርሲቲዎቹ ለውሃ አቅርቦት የሚሆኑ ግንባታዎች ባይጠናቀቁም ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የውሃ አቅርቦት አግኝተዋል። የዋና ዋና መሰረተ ልማት ግንባታ ስራ የመጀመሪያ ምዕራፍ ከአዳቡልቱና ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲዎች በስተቀር አብዛኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡
በ2010 ዓ.ም የመሰናዶ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲ የሚመደቡትን መደበኛ ተማሪዎች ቁጥር 149ሺ 233 ማድረስ ተችሏል፡፡ በመንግስትና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ ፕሮግራሞች የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ተሳትፎ በግል 94ሺ 692፣ በመንግስት 778ሺ 316 በአጠቃላይ 873ሺ 8 ማድረስ ተችሏል፡፡ የግል ከፍተኛ ትምህርት የሚተላለፉትን የተማሪዎች ቁጥር መረጃ በየጊዜው ተለዋዋጭ በመሆኑ በዚህ ዙሪያ ያለውን ችግር ማስተካከል እንደሚገባ ባለፉት የዘጠኝ ወራት እንቅስቃሴ ውስጥ ታይቷል፡፡
በመንግስትና በግል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አዲስ ሰልጣኞች ለማሰልጠን በመንግስት ኮሌጆች 275ሺ 671፣ በግል ኮሌጅ 92ሺ 254 በድምሩ 367ሺ 925 ሰልጣኞች ከደረጃ አንድ እስከ አምስት በመቀበል እየሰለጠኑ ይገኛሉ፡፡ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የተቋም ውስጥ አሰልጣኝ ለማፍራት በተሰራው ስራ 23ሺ 006 አሰልጣኝ እንዲሰለጥኑ ተደርጓል (የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል)፡፡ ብቃታቸው በምዘና የተረጋገጠ የኢንዱስትሪ ውስጥ አሰልጣኞችን ለማፍራት በተደረገው ጥረት 27ሺ 803 አሰልጣኞች እንዲመዘኑ ተደርጓል፡፡ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲቲዩት አዲስና ነባር መደበኛ አሰልጣኞች፣ በአመራርና ኢንዱስትሪ ቴክኒሻን ስልጠና ሰልጣኞች በተቋሙ በተለያዩ የትምህርት መርሃ ግብሮች እየሰለጠኑ የሚገኙ ሲሆን በዲግሪ 903፣ በሁለተኛ ዲግሪ 421፣ በክረምት ዲግሪ መርሃ ግብር አንድ ሺህ 569፤ እንዲሁም በክረምት ሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር 101 ተማሪዎች ይገኛሉ፡፡
የትምህርት ጥራት እና ሰላማዊ የማስተማር ሂደት
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተሰጡ ያሉ ስልጠናዎች ተገቢነት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ከማድረግ አንፃር የቅድመ ምረቃ እና የድህረ ምረቃ የትምህርት ስልጠና ፕሮግራሞችን በመለየት በመጀመሪያ ዲግሪ 216፣ በሁለተኛ ዲግሪ 457 እና በሶስተኛ ዲግሪ 210፤ በድምሩ 883 የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች መረጃ እንዲደራጅ ተደርጓልታቦቱ ከዋሻው ውስጥ ከመውጣቱ በፊት በእምብርክክ የሚያስኬደውን መንገድ ቁልቁል መውረድና ሽቅብ መውጣት ይጠይቃል፡፡ በዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች የስራ አውደ ርዕይ የተካሄደ ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ የስራ ኤክስፖ ተዘጋጅቷልታቦቱ ከዋሻው ውስጥ ከመውጣቱ በፊት በእምብርክክ የሚያስኬደውን መንገድ ቁልቁል መውረድና ሽቅብ መውጣት ይጠይቃል፡፡በኤክስፖ 29ሺ 300 ተማሪዎችና ከ200 በላይ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ቀጣሪ ተቋማት ተሳትፈውበታል፡፡
በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በሚገኙ 167 የግል ከፍተኛ ተቋማት ቅርንጫፍ ማዕከላት ላይ በተደረገ ድንገተኛ ዳሰሳ በ46 ተቋማት ላይ ችግሮች ታይተዋል፡፡ ከችግሮቹ መካከል ያለ እውቅና ፈቃድ ተማሪዎችን መዝግበው በማስተማር የሚገኙ 27 ተቋማት፣ በርቀት ፈቃድ የመደበኛ እና በመደበኛ ፈቃድ የርቀት የሚያስተምሩ አራት ተቋማት፣ የእውቅና ፈቃድ ሳያድሱ የሚያስተምሩ ስድስት ተቋማት፣ ሳያሳውቁ ህንፃ የቀየሩ ሶስት ተቋማት፣ ባልተሰጠ ስያሜ የሚጠቀሙ ሶስት ተቋማት እንዲሁም መረጃ ላለመስጠት ዘግተው የጠፉ ሶስት ተቋማት ይገኙበታል፡፡ በህግ ጥሰት ተግባራቸው ከተለዩት ቅርንጫፍ ማዕከላት መካከል 24ቱ ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ የተደረገ ሲሆን በተቀሩት ላይ የማጣራት ስራ በማከናወን እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል፡፡ የህግ ጥሰት በፈፀሙ ሶስት ኮሌጆች ላይ ክስ የመመስረት ስራው የተጀመረ ሲሆን፤ አንድ ኮሌጅ ላይ ክስ ተመስርቶ ክትትል እየተደረገ ይገኛል፡፡
በየትምህርትና ስልጠና ተቋሞች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲረጋገጥ ከፌዴራል፣ ከክልሎችና ከዞን አስተዳደር የተወጣጡ የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል፡፡ ተማሪዎች የማህበረሰብ አገልግሎት ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል መመሪያ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ በየወሩ ቅዳሜ ቀን ተማሪዎች የማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉታቦቱ ከዋሻው ውስጥ ከመውጣቱ በፊት በእምብርክክ የሚያስኬደውን መንገድ ቁልቁል መውረድና ሽቅብ መውጣት ይጠይቃል፡፡ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተከታታይ የሆኑ የስነ ልቦናና የማነቃቂያ እንዲሁም ስኬት ማላበሻ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡
ቀሪ ስራዎች
የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አብዱዋሳ አብዱላሂን፤ አገሪቱ ለያዘችው ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ሽግግር ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ከፍተኛ ድርሻ ያለው ቢሆንም ለዘርፉ የሚመደበው በጀት አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተቻለ አቅም ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንዲወጡ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ጥራት ያለው ቴክኒክና ሙያ ሰልጣኝ ለማፍራት የአሰልጣኞች ብቃት ማደግ አለበት የሚሉት ዶክተር አብዱዋሳ፤ ከየተቋማቱ የሚወጡ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መፈተሽ እንዳለባቸው አመልክተዋል። በተጨማሪም የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኢንስቲቲዩቶችን ተደራሽ ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናውን ጠቅሰዋል፡፡
የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚካሄዱና አዳዲስ የሚገነቡ ተቋማት ግንባታ መጓተቶች፣ የላቦራቶሪ እቃዎችና አጋዥ መፃህፍት እጥረት የተፈጠረው በግዥ መጓተት መሆኑን አስረድተዋልታቦቱ ከዋሻው ውስጥ ከመውጣቱ በፊት በእምብርክክ የሚያስኬደውን መንገድ ቁልቁል መውረድና ሽቅብ መውጣት ይጠይቃል፡፡ በየተቋማቱ የሚታዩ የግዥ ክፍተቶችን ለመፍታት መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑን በመጥቀስ፤ የኦዲት ክፍተቶችን ለመቅረፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አመራር ማጠናከር፣ የህግ ክፍተቶችን መቅረፍና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የቦርድ አመራር ውስጥ የዞን አስተዳዳሪ ወይም የከተማ ከንቲባ እንዲካተት መደረጉን የገለፁት ዶክተር ሳሙኤል፤ በአንዳንድ አካባቢዎች የዞን አመራሮች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ላይ ጫና የመፍጠር ሁኔታዎች እንደሚስተዋሉ ጠቁመዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች አስተዳደራዊ ነፃነታቸው መከበር እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
አዲስ ዘመን ግንቦት 5/2011
መርድ ክፍሉ