ሰብዓዊ ቀውሶች በተፈጥሮ ወይም በሰው ሰራሽ ምክንያቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ብዙ ሰዎች ምግብ፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ወይም ደህንነቱ የተጠበቀ መጠለያ የማያገኙበት ሁኔታ ሊከሰት ይችላል ፡፡ በዚህም ለዘርፈ ብዙ አደጋ ተጋላጭ ይሆናሉ።
custom mlb jerseys
custom nfl jersey
custom jersey
custom softball jerseys
custom team jerseys
design jerseys online
custom basketball jersey
custom apparel
custom nfl jerseys
customize football jersey
custom design jerseys
custom baseball jerseys
custom soccer jersey
custom jersey maker football
custom jerseys football
personalized jerseys
custom baseball jersey
custom team jerseys
custom uniforms
custom basketball uniforms
custom jersey maker baseball
custom basketball jerseys cheap
football jersey online
custom jerseys
best nfl custom jersey
custom nba jerseys
custom jerseys football
cheap football jerseys
custom hockey jerseys
custom baseball jerseys
customized jerseys
custom football jersey
custom hoodies for men
custom jerseys soccer
custom basketball jerseys
custom nfl jersey china
custom apparel
custom team jerseys
custom jerseys near me
cheap soccer jerseys
custom nba jerseys
እነዚህ ሰብዓዊ ቀውሶች ለመከላከልም ሆነ ከተከሰቱ በኋላ ለመቆጣጠር ማንኛውም የመንግሥትም ሆነ የሰብዓዊ ተቋም ሰብዓዊ እሴቶችን መሠረት ባደረገ መንገድ፤ በፍቅር እና ከዚህ በሚመነጭ ፅናት መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን ለማድረግ ዓለም አቀፍ መርሆዎች ያስገድዳሉ ።
የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ 46/182 እና 58/114 እንደሚያመለክተው፤ ድርጅቱ ሰብዓዊ ቀውሶችን በጊዜያዊነትም ሆነ በዘላቂነት ለመፍታት በሚያደርጋቸው ጥረቶች ከሚከተላቸው አራት መርሆች በዋነኝነት የሚጠቀሰው ሰብዓዊነት ሲሆን አለማዳላት፣ ገለልተኝነት እና ነፃነት ሌሎቹ ናቸው ፡፡
የሰብዓዊነት ትርጉሙ ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ሰብዓዊነትን መሠረት ባደረገ መንገድ ከፍ ያለ ትኩረት በመስጠት ችግር በተከሰተባቸው አካባቢዎች ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት እና በማገዝ ሰዎችን መታደግ ነው፡፡ ቀውሱ የፈጠረውን ችግር በመቆጣጠር በሰዎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ አቅም በፈቀደው ሁሉ መቀነስ፤ ርዳታ ፈላጊ ሰዎችን ያለምንም ገደብ መርዳትን በዋንኛነት ያካትታል፡፡
ከዚህ የተነሳም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት በሚደርሱ ቀውሶች ወቅት በማንኛውም ምክንያት ለሰዎች ርዳታ እንዳይደርስ ለማስተጓጎልና ለማደናቀፍ በሚጥሩ ሃይሎች ላይ ሰብዓዊ መብትን ታሳቢ በማድረግ ማዕቀብ የሚጥልበት አሰራርም አለው፡፡ ይህም የረድኤት ሠራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ርዳታ ፈላጊ ሰዎችን ያለገደብ ርዳታ እንዲደርሳቸውና ጉዳት እንዳያጋጥማቸው ለመከላከል የሚያስችል ነው፡፡
የትኛውም አካል ለሰብዓዊነት እና ለዚህ የተባበሩት መግሥታት ድርጅት መርህ ተገዢ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ በተለይም ርዳታ አቅራቢ ተቋማት እና መንግሥታት በየትኛውም ሁኔታና ቦታ ሊያከብሩትና ሊተገብሩት ይጠበቅባቸዋል ፡፡ ይህንን አለማድረግ ከሞራል ተጠያቂነት ባለፈ በዓለም አቀፍ ሕግ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል።
በቅርቡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነትም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ተፈጥረው ከነበሩ ግጭቶች ጋር በተያያዘ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ርዳታ ጠባቂ ሆነዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ መንግሥት ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ባስተላለፈው የርዳታ ጥሪ የርዳታ ድርጅቶች ለተረጂዎች አስፈላጊ የሚባሉ አቅርቦቶችን ሲያቀርቡ ቆይተዋል። አሁንም ብዛት ያላቸው ተቋማት እያቀረቡ ይገኛሉ።
ሚሊዮኖች ርዳታ ጠባቂ በሆኑበት ሁኔታ ሰብዓዊነትን መሠረት ያደረገ ርዳታ በየትኛውም ቦታና ሁኔታ እናደርሳለን የሚሉት ፤ የዓለም የምግብ ፕሮግራም እና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ ግን ‘ርዳታዎች ከታቀደላቸው ዓላማ ውጪ ውለዋል’ በሚል ሰበብ ርዳታ የማቅረብ ሥራቸውን ካቋረጡ ቀናት እየተቆጠሩ ነው፡፡
የረድኤት ድርጅቶች ሥራቸውን ለማቋረጥ ያቀረቧቸው ምክንያቶች ሰፊ የማጣራት ሥራን የሚጠይቁ ፤ ቢሆንም ተጣርቶ ተጠያቂነት ባልሰፈነበት ሁኔታ ውስጥ ድጋፍ የሚሻ በሚሊዮን የሚቆጠር ርዳታ ፈላጊዎችን የርዳታ አቅርቦት ማቋረጥ ከሰብዓዊነት መርህ ጋር የሚጋጭ ነው፡፡
ችግር ሲያጋጥም በሕግና እና በአሰራር ሥርዓት በማስተካከል መፍትሄ መስጠት እየተገባ በሚሊዮኖች ሕይወት መፍረድ ኢሰብዓዊነት ነው፡፡ ርዳታ የሚያስፈልገው ህዝብ ባልሰራው ወንጀል መቅጣት እና ሕዝብ በረሃብ የሚሞትበትን ሁኔታ መፍጠር ተቀባይነት የሌለው ኢሰብዓዊ ውሳኔ ነው ።
እነዚህ የርዳታ ድርጅቶች ከባድ ደም አፋሳሽ ጦርነቱ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ለዜጎች ሰብዓዊ ርዳታ ልናደርስላቸው ይገባል ሲሉ እንዳልነበርና በዚህም የሰብዓዊ ርዳታ አቅርቦት ተደናቀፈብን ሲሉም ማእቀብ እናደርጋለን እያሉ ሲዝቱና ሲያስፈራሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡
አሁን ሁኔታዎች በተስተካከሉበትና የርዳታ አቅርቦቶች በተሻለ መልኩ ለተረጂዎች የሚቀርቡበት ዕድል ሰፊ በሆነበት ሁኔታ የርዳታ አቅርቦቶችን ማቆም ከቆሙለት የሰብዓዊነት መርህ አንጻር በንፁሃን ሰዎች ላይ ሞት የመፍረድ ያህል የሚቆጠር ተጠያቂነቱም ከፍያለ እንደሚሆን ይታመናል፡፡ ተፈጠረ የሚባለውን ችግር የሚያጣራ ግብረ ኃይል በፌዴራል መንግሥትም ሆነ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በኩል ተቋቁሞ ወደ ሥራ በገባበት ሁኔታ የርዳታ ተቋማቱ የደረሱበት ውሳኔ ፤ በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡
ተቋማቱ የግብረ ኃይሉን ጥረት አግዞ ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርሳቸው ማድረግ ሲገባ ፤ ይሄንን አቋርጠው ሚሊዮኖችን ለከፋ አደጋ ተጋላጭ ማድረጋቸው ከሚገዙበት የሰብዓዊነት መርህ ጋር የሚጋጭ ነው፡፡ በመሆኑም ውሳኔውን ዳግም በማጤን ርዳታ የማቅረብ ሥራው ያለምንም መስተጓጎል ሊቀጥል ይገባል!፡፡
አዲስ ዘመን ሰኞ ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም