ወቅቱ ሰኔ ግም ያለበት፣ አርሶ አደሩ ማሳውን በዘር ለመሸፈን የሚታትርበት ነው። አርሶ አደሩ ሲሰነጥቅ፣ ሲያለሰልስ የቆየውን ማሳ በዘር የሚሸፍነው በአብዛኛው በዚህ ሰኔ ወር ነው። በአርሶ አደሩ መንደር የዘር ወቅት እስከሚያበቃ ድረስ ማሳን በዘር ለመሸፈን ከጊዜ ጋር ሽሚያው ይጠነክራል፤ ደቦው ይባዛል። ዝናብና ብርድ ብሎ ነገር የለም፤ እንዲያውም ተመስገን ነው የሚባለው። አርሶ አደሩ በዚህ ወቅት የሚያዳምጠው ዝናቡ፣ እርሻው፣ እቅዱ እንዳሰበው እየሄደ መሆኑን ብቻ ነው።
አንድ ሰኔ የገደለውን ብዙ ሰኔ እንደማይመልሰው ይገለጻል። በዚህ ወቅት ያልተሠራን ለማካካስ ብዙ ድካምንና ጊዜን የሚጠይቅ መሆኑን ለማስገንዘብ የሚነገር ነው። በአርሶ አደሩ ዘንድ በእዚህ ወቅት የጎደለን ማካካስ ይከብዳል። እናም አርሶ አደሩ ወቅቱ ፋታ የማይሰጥ የግብርና ሥራ ያለበት በመሆኑ ከሰኔና ከጊዜ ጋር ከፍተኛ ግብግብ ይገጥማል።
ይህ የአርሶ አደሩ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የሰኔ ወቅት ርብርብ አንድ ትልቅ አቅም ነው። እንደ ሃገር በተያዘው የግብርና ልማት መሠረት ግን አርሶ አደሩ ከዚህ ተለምዷዊ አሠራሩም በላይ ጠንክሮ መሥራት ይኖርበታል። ሃገር ከእጅ ወደ አፍ ግብርና ለመላቀቅ እየሠራች ነው። ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ለአርሶ አደሩም ለመላ ኢትዮጵያውያንና ለመንግሥታቸው ወሳኝ ጉዳይ ነው።
መንግሥት የግብርናውን ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግና የአርሶ አደሩንም የሃገርንም የምግብ ዋስትና አረጋግጦ፣ ግብርናውን ከእጅ ወደ አፍ ግብርና በማላቀቅ ኮሜርሻል ግብርናን እውን ለማድረግና የዘርፉን መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት እየሠራ ነው።
ለአፈር ማዳበሪያ ከፍተኛ መጠን ያለው ሃብት የመደበ ሲሆን፣ ዘንድሮ ለአፈር ማዳበሪያ 21 ቢሊዮን ብር መድቦ ግዥው ተፈጽሞ ለአርሶ አደሩ እያደረሰ ነው። በግብርና ሜካናይዜሽን ማሽነሪዎች አቅርቦት ላይ በስፋት እየተሠራ ይገኛል፤ ለግብርና ሜካናይዜሽንና የግብርና ባለሙያዎች ለአርሶ አደሩ ለሚያደርጉት ድጋፍ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር በታመነበት ኩታ ገጠም እርሻ ማስፋፋት ላይ በትከረት እየተሠራ ይገኛል። መንግሥት ለግብርናው ዘርፍ እየመደበ ካለው ከፍተኛ መጠን ያለው በጀት በተጨማሪ የፋይናንስ ዘርፉ ለአርሶ አደሩ የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርግ ማሳሰቡን ቀጥሏል። በዚህች ሃገር ግብርና ላይ በበጋ ስንዴ መስኖ ልማት አዲስ ታሪክ እየተመዘገበ ነው። በሀገሪቱ ግብርና ምርትና ምርታማነት ላይ እየታየ ያለው ለውጥ የዚህ ሁሉ ርብርብ ድምር ውጤት ነው።
ግብርናው ካለው እምቅ አቅም እንዲሁም ሃገሪቱ በዘርፉ መድረስ ከምትፈልገው ራዕይ አኳያ ሲታይ ግን ይህ ለውጥ ገና የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ያለ ሊባል የሚችል ነው። የሃገሪቱ ዓመታዊ የግብርና ምርት እቅድ፣ በዘር የሚሸፈነውም ማሳ እንዲሁ በኩታ ገጠምና በመደበኛ ማሳ እያለ እየጨመረ ይገኛል። የሚቀርበው የማዳበሪያ መጠንም እየጨመረ ነው።
በሜካናይዜሽን ማሽነሪዎች በኩልም ሰፋፊ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ፤ አርሶ አደሩ በግሉ በማሽነሪ ሊዝ እየገዛ ወደ ሥራ እያስገባ ነው፤ በኅብረት ሥራ ማኅበራቱና ዩኒየኖቹ ደረጃም እነዚህን ማሽነሪዎችና የሜካናይዜሽን አገልግሎት የሚሰጡ ኢንተርፕራይዞች እየተበራከቱ ናቸው። ፀረ ሰብል ተባይ የመከላከል አቅምም እየተገነባ ይገኛል። የሚትዮሮሎጂ መረጃዎች ግብዓት እየሆኑ ናቸው።
የ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን አስመልክቶ የግብርና ሚኒስቴር መረጃዎችን ዋቢ ያደረጉ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት፤ በሃገር አቀፍ ደረጃ በዚህ የመኸር ምርት ዘመን ከ508 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል። ለዚህም እንደ ሃገር በምርት ዘመኑ በክላስተርና በመደበኛ ግብርና ከሚሸፈነው 16 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ያህል ላይ ነው ይህን ያህል መጠን ያለው ምርት ለመሰብሰብ የታቀደው። ለመኸር ምርት ሥራም አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
የዚህ ዘመን የአርሶ አደሩ የግብርና ሥራም ይህን ሁሉ ርብርብ ታሳቢ ያደረገና የሚጠበቀውን የምርት መጠን የሚያሳካ ሊሆን ይገባል። እንዲመረት የሚጠበቀው ምርት መጠን ከፍተኛ በሆነ ቁጥር፣ ለምርቱ ሥራ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ግብዓቶችና ማሽነሪዎች እየጨመሩ በመጡ ቁጥር የአርሶ አደሩም እነዚህን ግብዓቶች አቀናጅቶ በመጠቀም የበለጠ ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ ርብርብም የተጠናከረ መሆን ይኖርበታል።
ይህ እንዲሆን አርሶ አደሩ የሚያደርገው የተጠናከረ ተግባር እንዳለ ሆኖ መንግሥት፣ አርሶ አደሩን የሚደግፉት የግብርና ባለሙያዎች፣ የአርሶ አደሩ የኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ ዩኒየኖችና የፋይናንስ ተቋማት ከአርሶ አደሩ ጎን ሆነው መሥራታቸውን በዚህ ታላቅ የመኸር እርሻ ወቅት ይበልጥ ማጠናከር ይኖርባቸዋል።
የሁሉም አካላት የዚህ ወቅት ቀዳሚ ትኩረት ግብርና ሊሆን ይገባል። ግብርናው በቀረበለት ልክ እንዲሠራበት ማድረግም ይገባል። በአቅርቦት በኩል ክፍተቶች ሲያጋጥሙ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ አሠራር መዘርጋትም ይኖርበታል። በዚህ ወቅት ለእነዚህ አካላት ከግብርናው በላይ ሌላ ትኩረት የሚፈልግ ተግባር ሊኖር አይገባም። ልክ እንደ አርሶ አደሩ ሁሉ፣ ሌሎች የግብርናው ዘርፍ ተዋንያን ግብርናው የሙሉ ጊዜ ሥራቸው ሊሆን ይገባል!
አዲስ ዘመን ሰኔ 18/2015
Clomiphene is thought to work as a selective estrogen receptor modulator SERM, acting as an estrogen antagonist at the hypothalamic- pituitary axis and stimulating Gn- RH secretion donde comprar priligy mexico Free Radic Biol Med 1998; 25 1006 12
Snasdxxxax.Snasdxxxax