ትንሽ ብቻ ዞር…

ማንበብ ስወድ ለጉድ ነው። ከዕለት ተዕለት ሱሶቼ መሐል በኩሩ ሆኖ እንደቡናና ትንባሆ ያዳክረኛል። የእውቀት ማረፊያው አእምሮ ነው። በልብ በኩል ደግሞ ስር ይሰዳል። የአእምሮ ብቻ መሆንና የአእምሮና ልብ መሆን የተለያዩ ማንነቶች ናቸው። የአእምሮ... Read more »

ጀምበር ግን ታድላ…

ኩርፊያ መልክ ቢኖረው ቁርጥ ሩታን ይሆን ነበር። ጠይም ዘለግ ያለ፣ አይኖቹ ከከዋክብት የተዋለዱ የሚመስሉ፣ ጸጉሩን ቁጥርጥር የተሰራ ኩርፊያ ለንቦጩን ጥሎ ካያችሁ አትጠራጠሩ ሩታን ነው። በዳመነ ፊት ከንፈሩን በጥርሱ እየበላ በአንድ የሆነ ቦታ... Read more »

 ወለፈንዲ

በተወለድኩ በአርባኛው ዓመት በሠላሳኛው ቀን ለዘመናት ካሸለብኩበት ሞት አከል እንቅልፍ የመጀመሪያውን መንቃት ነቃሁ:: በዚህች መከረኛ ምድር ላይ እንደ ሲራራ ነጋዴ አርባ ዘመን ስመላለስ ህሊና የሚባለውን ብልት ለምን ፋይዳ አውለው እንደነበር ባላውቅም ያን... Read more »

ከአፈር ወደአፈር

ከቤቴ ስወጣ አራት መንታ መንገዶች ያገጡብኛል። መሀል ላይ ክብ ቅርጽ ሰርተው ሃሳቤን ይቀሙኛል። አንዱ ወደመስኪድ፣ አንዱ ወደስላሴ ቤተክርስቲያን፣ የተቀሩት ሁለቱ ወደማፈቅራት ሴት ሰፈር እና መቼም ልሄድበት ወደማልፈልገው የሆነ ሰፈር። ወደማፈቅራት ሴት ሰፈር... Read more »

«የወርቅ እንቁላል»

እዚህ ከተማ ውስጥ ጠጅን እንደ ጠንክር የሚጠጣት ሠው አለ ቢሏችሁ እንዳታምኑ፡፡ ጠጅ ራሷ ጠንክር ካልጠጣት የተጠጣችም አይመስላት፡፡ ‹‹ልብስ መስቀያውን አገኘ›› እንዲሉ ጠጅም ብርሌዋን አገኘች ከተባለ ጠንክር ሰቦቃ ነው፡፡ ታድያ ጠንክር ጠጅ ብቻውን... Read more »

አሽሙር

ሹል አፍ.. ከስሟ ቀጥሎ፣ ሁሉም ከሚያውቀው ሰማያዊ ፈገግታዋ ቀጥሎ መታወቂያዋ ነው። ስም ከማንነት ጋር ልክክ ያለላት ሴት ናት። እድል ሳይሰጣት ባተሌ ሆና ቀረች እንጂ እግዜር ሲሰራት ለንግስትነት አስቦ ከመሰለኝ ሰንበትበት ብያለው። ባለሰማያዊ... Read more »

 ከጉርምስና እስከ ጉልምስና

አዲስ የገዛሁት ጫማ አቧራ ቅሞ ሳየው መሀረቤን ከኪሴ መዥርጨ አበስ አደረኩት። ወደእሷና ወደእናቴ ስሄድ ተሽቀርቅሬ ነው። እናቴ ፊት ጎስቋላ እሷ ፊት መሀይምና የማይረባ መምሰል አልፈልግም። በቸምቸሞ ጥቁር ጸጉሬ መሀል ያገጠጡ ያለጊዜያቸው የበቀሉ... Read more »

 ቀምጣላ ጣቶች

ቶሎ ቶሎ የሚርበኝ ነገር አለ። ከክፉ ገመናዎቼ አንዱ በቀን ስድስት ጊዜ መመገቤ ነው። እንደአመጋገቤ ግን አልፀዳዳም… ከሰው የበዛ በልቼ ከሰው ያነሰ ነው የምፀዳዳው። አንዱ የሚገርመውም ይሄ ነው፤ ሰው እንዳበላሉ አይፀዳዳም ነው የሚባለው... Read more »

ትስስር

ብዙ ነገር ያምረናል፣ ካማረን ውስጥ አንድ አስረኛውን እንኳን ርቆናል። ትላንትን ለብቻ ማለፍ፣ ዛሬን በራስ መሻገር..ነገን ለብቻ መጠበቅ አልድን እንዳለ የቆላ ቁስል የነፍስ ቁርጥማት ነው። ምን ሆነሃል ብሎ? እንደጠያቂ የነፍስ ወዳጅ የለም። ያጣንው... Read more »

ወዲያ ወዲህ

በህይወቴ የምቆጭባቸው ሁለት ነገሮች አሉ። የመጀመሪያው በነሶቅራጠስ ዘመን አለመወለዴ ነው። ሁለተኛው ደግሞ በእኔ ዘመን ሶቅራጠስን መሳይ ሰው አለመፈጠሩ ነው። የኦሾና የሶቅራጠስ ስለህይወት ያላቸው እይታ ይማርከኛል። ከእየሱስ ጋር አብረው ህይወትን የፈጠሩ ይመስል ህይወት... Read more »