እማ! አልኳት ወዳለችበት ራመድ ብዬ። እማ ነው የምላት..ተሳስቼ በስሟ ጠርቻት አላውቅም። እንዲህ እንደ አሁኑ እንድታስቸግረኝ ፊቷ ቆሜ አውቃለሁ። ‹ወዬ ጌታዬ! አለችኝ..ፊቷን በትንሽ ፈገግታ ሞልታ። በእሷ አፍ ጌታዬ ስባል ነፍሴ በደስታ በልቤ ውስጥ... Read more »
ማታ ሊሆን ትንሽ ሲቀረው..አስራ ሁለት ግድም ላይ ከቤት ወጣሁ ሳሮንን ላገኝ:: ሳሮን ከብዙ የእንገናኝ ውትወታ በኋላ ቃሏን የሰጠችኝ የመጀመሪያዋ ሴት ነች:: ደሞ እኮ አታምርም..ቆንጆ ሆና ብታለፋኝ አይቆጨኝም ነበር:: አስቀያሚ ናት..የሌለ:: በአስቀያሚ ሴት... Read more »
ልማድ አለብኝ ክፉ ልማድ..ጥፍሬን እበላለው፣ ጸጉሬን እቆነድዳለው። እኚህ ልማዶቼ በሰው ፊት አላሳነሱኝም። አንዳንድ ጊዜ እናቴ ‹እጅህን ከራስህ ላይ አውርድ ብላ በማማሳያ ከመማታቷና ጥፍርህን ለምንድነው የምትበላው? ከማለት ባለፈ ያን ያክል ሰው አፍ ላይ... Read more »
ሕይወት በእሾህ የታጠረች እንደሆነች የገባኝ አስራ ስምንት ዓመቴን ካከበርኩ በኋላ ነበር። ከዛ በፊት የነበረው ሕይወቴ እንደ ማር የጣመ ነበር። በድሎት የተኖረ። በሕይወት እሾህ እየተወጉ እኔን የሚያሞላቅቁ ወላጆች ነበሩኝ። ከእማዬ ካመለጥኩ አባዬ ጉያ... Read more »
አያቴ ጥቁር ቀለም አትወድም..ጠይም መሆኔ በጀኝ እንጂ እኔንም ልጄ አይደለም ብላ ልትክደኝ ትሞክር ነበር። ከቤታችን ውስጥ ለጥቁር የቀረብኩት ጠይሙ እኔ ነኝ..አብሬያት ስሆን ሌላ ወሬ የላትም ‹እንዳው በማን ወጥተህ ነው እንዲህ የጀበና ቂጥ... Read more »
አስባለው..ባለማሰብ ውስጥ። ላለማሰብ አስባለው..ለማሰብ አስባለው። ላለማሰብ ማሰብ ለማሰብ ከማሰብ በላይ አስጨናቂ እንደሆነ በእለት ተእለት ኑሮዬ ተለማምጄዋለው። አልጫ በጨው ይጣፍጣል፣ ቡና በስኳር ይጥማል የህይወት ማጣፈጫ ምንድነው? ህይወት ምን ጠብ ቢደረግባት ነው ስኳርና ጨው... Read more »
ከአምስት ዓመት በኋላ ከሮዛ ጋር ተጋባን።ያን ወፍ ዘራሽ ወንድነቴን ባሏ አደረገችው።ያን በተለያዩ ሴቶች ያደፈ ገላዬን አቅፋው ልትተኛ ነው..ያን በብዙ ሴት የተሳመ ከንፈሬን ልትስመው ነው። ወፍ ዘራሽ ነበርኩኝ እኮ..አብረን የሚያዩን አንዳንድ ሰዎች ወደ... Read more »
ወንድ አያቴ ጃጅቷል..ብቻውን እያወራ ብቻውን የሚስቅ ነው። ምን እንደሚል አይሰማኝም ግን ሁሌም ሲያወራ አየዋለሁ። ለመደመጥ የሚከብዱ፣ ለመሰማት ያልደረሱ ልጃገረድ ድምጾች ከአፉ በጆሮዬ ሽው ይላሉ..ሳልሰማቸው..ከአየሩ ጋር ይደባለቃሉ። ይሄ ብቻ አይደለም ጆሮውም ከድቶታል። ሹክሹክታ... Read more »
የምትፋጀውን ጸሀይ ለመሸሽ ስል ለረጅም ሰዐት ከቤት አልወጣሁም ነበር።ከሰዐት ወደ አመሻሽ ሲሳብ ቀን ሙሉ ካላየሁት ደጅ ጋር ተያየሁ።የጸሀይዋን ማረጥ ተከትዬ ብቻዬን ስሆን የምተክዘውን ትካዜ እየተከዝኩ ወደ አንድ ሄጄበት ወደማላውቀው ሰፈር አመራሁ።ትካዜ አቅል... Read more »
የነፍሴ ራቁት ሴትነቷን ለብሷል..ሀሳቤ ጀምሮ የሚያበቃው እሷ ጋ ነው። እሷን ሳስብ ባልሞት እላለው፣ ለዝንታለም ብኖር እላለው፣ ደጋግሜ ብፈጠር እላለው። እሷን ሳስብ..ሀሳብ ይጠፋኛል..ጥበብ ይርቀኛል..ደግሞም ሀሳብ ይሞላኛል..ጥበብ ይወረኛል። እሷን ሳስብ..ለብቻዬ እስቃለው..አፌ ውስጥ ሞልቶ የሚፈስ... Read more »