የበጋው መብረቅ

‹‹ስም ከመቃብር በላይ ይውላል›› የሚባለው ዝም ብሎ አባባል ብቻ አይደለም፡፡ የሚናገረው ትልቅ መልዕክት ስላለ ነው፡፡ ከመቃብር በላይ የሚውለው ስም ከመቃብር በታች የሆነውን ሥጋ ሕያው ያደርገዋል፡፡ ‹‹ጀግና አይሞትም!›› የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ ጀግና አይሞትም... Read more »

የዶክተር ዐቢይ አሕመድ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት

ሌላኛው የዚህ ሳምንት ክስተት በዚሁ በመጋቢት 24 ቀን የተከናወነው የዶክተር ዐቢይ በዓለ ሲመት ነው። የዶክተር ዐቢይ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት መምጣት የኢትዮጵያን የፖለቲካ እንቅስቃሴ አዲስ ድባብ አላበሰው። ‹‹ፖለቲካና ኤሌክትሪክን በሩቁ›› ይባል የነበረው ተቀየረ፡፡... Read more »

ሁለቱ የመጋቢት 24 ክስተቶች

የዚህ ሳምንት ‹‹ሳምንቱ በታሪክ›› በአንድ ቀን ሁለት ክስተቶች ላይ ያተኩራል፡፡ መጋቢት 24 ላይ፡፡ ክስተቶቹ የሰባት ዓመታት ልዩነት አላቸው፡፡ የመጀመሪያው ክስተት ኢትዮጵያውያን በአንድ ሳምባ የተነፈሱበት የዓባይ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተጣለበት 12ኛ ዓመት ነው፡፡... Read more »

በአጼ ቴዎድሮስ የተፈሩት ራስ ዳርጌ

የንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ አጎት የሆኑትና በጀግንነታቸው ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስን ጭምር ያስጨነቁትና ያስደነቁት ርዕሰ መኳንንት ራስ ዳርጌ ሳህለሥላሴ ያረፉት ከ123 ዓመታት በፊት በዚህ ሳምንት መጋቢት 15 ቀን 1892 ዓ.ም ነበር፡፡ ራስ... Read more »

 ወታደሩ፣ ግዛት አስተዳዳሪው እና ዲፕሎማቱ

የመጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንታት ታሪኮችን እያስታወስን ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት ደጃዝማች ዑመር ሰመተርን አይተናል፡፡ የዚህ ሳምንት ክስተቶች በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በጦር አዋቂነት፣ በአስተዳዳሪነት፣ በዲፕሎማትነትና በታሪክ ፀሐፊነት፣ በአትሌትነት እና በብሔር ፖለቲካ አቀንቃኝነት የሚታወቁ የተለያዩ... Read more »

የደጃዝማች ዑመር ሰመተር የጀግንነት ገድል

‹‹ከአገሬ አፈር የሚደባልቅ ቤልጅግ እና ጎራዴ ይዤ እንጂ ጫት ተሸክሜ የምመጣ እንዳይመስልህ!›› የሚለው ንግግራቸው በቃል ጭምር ይነገርላቸዋል። ፋሽስቱን ጣሊያን መግቢያ መውጫ ካሳጡ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ጀግኖች አንዱ የሆኑት የምሥራቁ አርበኛ ደጃዝማች ዑመር... Read more »

የመተማ ጦርነት እና አጼ ዮሐንስ

 ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዚያት ከተለያዩ አገራት ጋር ጦርነት አድርጋ አሸንፋለች:: በቅርቡም የዓድዋን እና የሶማሊያን ወረራ ያከሸፈችበት የካራማራ ድሎች ተከብረዋል:: እነሆ በመጋቢት ወር መጀመሪያ ደግሞ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩት አጼ ዮሐንስ 4ኛ ሕይወታቸውን ያጡበትን... Read more »

የዓድዋ እና ካራማራ ድሎች

እነሆ የየካቲት ወር ገናናው ታሪኩ ላይ ደርሰናል። በዚህ ሳምንት ባሳለፍነው ሐሙስ የካቲት 23 ቀን የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የዓለም የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ የሆነውን የኢትዮጵያን የድል ቀን ዓድዋን በድምቀት አክብረናል። ዓድዋ ብዙ የተባለለትና ብዙ... Read more »

ጀግኖቹ፤ ራስ ደስታ ዳምጠው፣ደጃዝማች በየነ መርዕድ እና ደጃዝማች ገብረማርያም ጋሪ

ከዚህ በፊት በነበሩት ሳምንታት እንደገለጽነው ይህ የየካቲት ወር ታሪካዊ ክስተቶች የሚበዙበት ነው:: የካቲት 12 የሰማዕታት ጀግኖችን ተጋድሎ ዘክረናል:: በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ ኢትዮጵያን ስመ ገናና ያደረጋት የዓድዋ ድል አለ:: ይህ ሁሉ የሆነው በኢትዮጵያውያን... Read more »

የካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ

የየካቲት ወር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በተለይም በታሪክና ፖለቲካ ጉልህ ሚና ያለው ወር መሆኑን ባለፈው ሳምንት ጠቅሰናል፡፡ ከእነዚህ የየካቲት ወር ጉልህ ታሪካዊ ክስተቶች የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን እና ዓድዋ በደማቁ የሚታወሱ ናቸው፡፡ ዓድዋን... Read more »