ልማት በራሱ ውጤታማ እንዲሆን ደግሞ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልን ጨምሮ ከሙስና የፀዳ ሀገራዊ ፖለ ቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ስርአት መፍጠር ወሳኝ ነው ። ለዚህ የሚሆን ትውልድም መፍጠር አስ ፈላጊነቱ ከፍ ያለ ነው ።
ለቀኝ ገዢ ባለመንበርከክ እና በነፃነት ፋና ወጊነት የምትታወቀው ኢትዮጵያ፤ አፍሪካውያን በሙሉ እና ታችን ብለው የሚጠሯት ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጆች መገኛ ቀደምት ምድር የምትባለው ኢትዮጵያ፤ የአለም ጭራ ሆና በድህነት የመዳከሩዋ እውነታ የአደባባይ ሚስጥር ነው ፡፡ይህንን ታሪክ ለመቀየር ትልቁ አቅም ደግሞ ልማት ነው ።
በቀደሙት ሶስት አስርት አመታት በሀገሪቱ ስለ ተከናወነ የልማት ስራዎች በስፋት ሲነገርና ሲዘከር ቢቆይም ከላይ የተጠቀሰውን አይነት ሀገራዊ ስርአት መፍጠር ባለመቻሉ እንደ ሀገር ከፍያለ ችግር ውስጥ ገብተናል ። የችግሩ ደረጃም የሀገርን ህልውና አስከመገዳዳር ደርሶም ታይቷል።
በተለይም ባለፉት ሁለት አስርት አመታት በሀገሪቱ ከመቻውም ጊዜ በከፋ መልኩ ተንሰራ ፍቶ የቆየው ሙስና /ሌብነት አገሪቷን ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ሲያንደረድራት፤ ከገባችም በኃላ ከገባችበት እንዳትወጣ መልሶ መላልሶ ሲጎትታት ተስተውሏል ፤ አንዱ እየለፋ እና እየደከመ በድህነት ሲቆራመድ፤ ሌላው ዘርፎ ሃብት በሃብት ላይ ሲደርብ ሃይ ባይ ጠፍቶ የህዝብ አንጀት እያረረ በዝምታ አመታት አል ፈዋል፡፡
በቀደመው ዘመን መሬትን ጨምሮ የአገሪቱና የመላው ህዝብ መሆን ያለበት ሃብት ሳይቀር በጥቂ ቶች ቁጥጥር ስር መውደቁ የብዙዎች ሕይወት ከእጅ ወደ አፍ እንዲሆን አስገድዶ ኖሯል፡፡ የተወሰነው መሬትን ተቆጣጥሮ ከበርቴ መሆኑን አውጁ ያለአግ ባብ ግብር ሲያስገብር በተለያየ መልኩ እጅ መንሻ ሲቀበል፤ ሌላው የገዛ የአገሩን መሬት እያረሰ ጭሰኛ ተብሎ ሲከፍል፤ የመሬት ላራሹን ጥያቄ እንዳስነሳ ታሪክ ምስክር ነው፡፡ጥያቄው አድጎ ለስርአቱ ወድቀት እንደሆነም ይታወቃል ፡፡
ልክ እንዲዚሁ ሁሉ በሙስና ሀገርን በከፋ ስጋት ውስጥ ከትቶት የነበረው የኢህአዴግ መንግስት በህዝ ቦች አመጽ ከስልጣን መወገዱ የትናንት ትውስታ ነው ።ያንን ነውር የተሟላን ስርአት ለማስቀጠል በተደረ ገው ጥረትም ሀገርና ህዝብ የቱን ያህል ዋጋ ለመክ ፈል እንደተገደዱ የሚታወቅ ፤ ገና ያልደበዘዘ እውነታ ነው ።
በርግጥ ከሁሉም በላይ መንግስት ከማንም በላይ ሙስናን/ ሌብነት የመከላከል/ የመዋጋት ከፍተኛ ሀላ ፊነት አለበት ።ይህን ሀላፊነቱን ለመወጣት የሚሄ ድበት ጥግ ሀገርን እንደሀገር ከመታደግ የሚተና ነስ አይሆንም። በተለይም በኛ ሀገር አሁናዊ እውነታ ጉዳዩን በዚህ ደረጃ እንድናስበው የሚያስገድደን ብዙ ተጨባጭ ነገሮች አሉ።
አሁን ላይ ሙስናን ማጥፋት ባይቻል እንኳ ትርጉም ባለው መልኩ የሙስና መጠን እንዲቀንስ በት ኩረት መስራት ካልተቻለ የሚያስከትለው ውጤት አስደንጋጭ ሊሆን እንደሚችል አያጠያይቅም፡፡ መንግ ስት የጀመረውን ልማት ቀጣይ እንዲሆን ፤ከዛም በላይ በልማቱ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማስፈን ሙስናንን ያለርህራሄ ሊዋጋ ይገባል፡፡
ለዚህም ህግ አውጪው፣ ህግ ተርጓሜውም ሆነ ህግ አስፈፃሚው አካል ተቀናጅተውና ተናበው መንቀ ሳቀስ ይጠበቅባቸዋል ፡፡ ለዚህ የሚሆን የሚታይ ቁር ጠኝነት መፍጠር ይኖርባቸዋል ።ከዚህ ቀደም ሲስ ተዋል እንደነበረው አሁን በሙስና ላይ የተጀመረው ዘመቻ ያለ ፍሬ እንዳይቀር የተፈጠረው ጸረ-ሙስና እንቅስቃሴ አቅም ገዝቶ የሚጓዝበትን አስቻይ ሁኔታ ማመቻቸት ይጠበቅበታል ።
ለዘመቻው ውጤታማነት መገናኛ ብዙሃኑን በአ ግባቡ መጠቀም ፤በፀረ- ሙስና ትግሉ በነጻነት የሚ ሳተፉበትን ሁለንተናዊ አስቻይ ሁኔታ ከመፍጠር ጀምሮ ፤ በጉዳይ የአሳሳቢነት ደረጃ ዙሪያ በቂ ግንዛብ መፍጠር ይኖርበታል። የምርመራ ዘገባዎ ችን ትኩረት አድርገው በብቃት እና በጥራት እን ዲሰሩ ማስቻል ለዘመቻው ውጤታማነት የሚኖረው ድርሻ ከፍ ያለ ነው።
የፀረ ሙስና ኮሚሽንን ማጠናከር እና በየተቋሙ ያሉ የፀረሙስና ክፍሎችን በአግባቡ መደገፍ እንዲ ሁም በሙስና ላይ ለሚሰሩ ዜጎች ከለላ መስጠት ተገቢ ነው፡፡ ይህም በራሱ የሚያመጣው ውጤት ቀላል አይ ሆንም፡፡ ሰሞኑን እየተወሰደ እንዳለው ዓይነት የተለያየ ኮሚቴዎችን በመሾም ስራውን በተጠናከረ መንገድ ማሰማራትም መልካም ነው፡፡
አሁን በሀገሪቱ በተጀመረው የፀረ-ሙስና ዘመቻ የሰረቀ አለቃና ምንዝር ከተያዘ እና ከተጠየቀ፤ ከመጠ የቅ አልፎ ተገቢው ቅጣት ከተሰጠው፤ ቢያንስ የብ ዙሃኑ ሌባ እጅ መሰብሰቡ አይቀርም፡፡ ከዚህ ባፈ ነገጠ መንገድ በሌቦች መካከል የተጠያቂነት ልዩነት መፍጠር ከጀመረ ነገሩ በእንቅርት ላ ጆሮ ደግፍ ከመሆን የሚለይ አይሆንም።
አንደኛው ዘራፊ ባለስልጣን ስለሆነ ወይም ባለስ ልጣን ዘመድ ስላለው፤ አሊያም የሆነ ብሔር ተወላጅ በመሆኑ አንዳንዴም የሆነ ሃይማኖትን ሰለሚከተል ሌብነት ከተፈቀደለት እና እንደፈለገ እንዲዘርፍ ከተመ ቻቸለት የተፈራው የሀገር ህልውና አደጋውስጥ የመግ ባቱ እውነታ ሩቅ ሳንጓዝ ሀገራዊ ስጋት ከመሆን አልፎ መከሰቱ የማይቀር ነው ፡፡
ሙስና የሃብት ክፍፍል ፍትሃዊ እንዳይሆን፣ የሥራ አጥ ቁጥር እንዲጨምር ብዙሃኑ ሕዝብ የበይ ተመልካች እንዲሆን ስለሚያደርግ ውጤቱ አገር እስ ከማፍረስ መዝለቁ ብዙም ለጥያቄ የሚቀርብ አይደ ለም ፡፡
አሁን ላለንበት ሀገራዊ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ሆነ ወደ ፊት ልንደርስበት ላለምነው ብልጽግና ስኬት አሁን የጀመርነውን የጸረ-ሙስና ትግል አጠናክሮ ከመ ቀጠል ውጪ ምንም አመራጭ የለንም። ስለዚህ ሙስናን መከላከሉ ሆነ ሙሰኞችን የመዋጋቱ ትግል የመላውን ህዝብ ተሳትፎና አመኜታ መሰረት ባደረገ መንገድ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ፡፡ ሰላም!
ምሕረት ሞገስ
አዲስ ዘመን ማክሰኞ ታኅሣሥ 11 ቀን 2015 ዓ.ም