ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋ እንዲቆረቁዝ፣ እድገቷ እንዲቀ ጭጭ፣ የሕዝቦቿ የኑሮ ደረጃ የሰማይና የምድርን ያህል ልዩነት እንዲኖረውና የኑሮውድነት እንዲባባስ ካደረጉ ምክ ንያቶች አንዱ ምክንያት በድሮው የተሽሞነሞነ አጠራሩ ኪራይ ሰብሳቢነት ወይም ሙስና በአሁኑ ቁልጭ ያለ መጠሪያው ደግሞ ሌብነት ነው።
ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲመረጡ ለሕዝባቸው ቃል ከገቧቸው ጉዳዮች አንዱ ከሙስና እና ከሌብነት የጸዳ የአሠራር ሥርዓትን በአገሪቱ ማስፈን የሚል ነበር። እንደተናገሩትም ሙስና በሚል መሸፋፈኛ ቃል ሲሽሞነሞን የነበረውን ፀያፍ ተግባር ‹‹ሌብነት›› በሚል ርካሽ መጠሪያው እያስተዋወቁ ርምጃ መውሰድ መጀመራቸው የሚታወስ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን በያዙ ማግስት በሌብነት የበለጸጉ ግለሰቦችን እያደኑ ተጠያቂ የማድረግ አሠራርን ዘርግተው ጥቂቶች በህግ ጥላ ሥር መዋል እንደጀመሩ የጥቅም ትስስሩ ከታች እስከ ላይ ባሉ የመንግሥት መዋ ቅሮች ውስጥ የተንሰራፋና የተደራጀ ስለነበር ኩርፊያና አመጽ ማስነሳቱ አልቀረም።
በዚህም ምክንያት በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የተሰ ገሰጉት ሌቦችና ጥቅመኞች ከተጠያቂነት ለማምለጥ ሲሉ በየቦታው ድንገተኛ ግጭትና ረብሽ በማስነሳት ለመንግ ሥት ሌላ አጀንዳ እየፈጠሩ እድሜያቸውን ለማራዘም ይጥሩ እንደነበር የሚታወስ ነው። ያም ሆኖ መንግሥት ግጭቶችን በጥበብ እየተቆጣጠረ ሌቦችን ለፍርድ የማቅረ ቡን ሥራ መሥራቱን አላቆመም ነበር።
ይሁንና የሕዝብን እና የአገርን ሰላም ጥያቄ ውስጥ የከተተው የሰሜን ዕዝ ጥቃት መፈጠሩን ተከትሎ ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከሹማምንት እስከ ተራው ሕዝብ ድረስ ትኩ ረቱን፣ ጊዜውን፣ ጉልበቱን፣ ሀብቱን፣ ሕይወቱን ሳይቀር የአገሩን ሰላምና ደህነነት ለማረጋገጥ በሚያስችል ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ ላይ በማድረጉ የተጀመረው ሌቦችን የማጽዳት እና ሕጋዊነትን የማስፈን ርምጃ በታሰበው ልክ እንዳይሄድ ምክንያት ሆኗል።
ጭራሽ የብዙኋኑ አገር ወዳድ ኢትዮጵዊ ዓይን በአገሩ ሰላምና ደህንነት ላይ ማማተሩን ተከትሎ የቢሮ አይጦች ሀይ ባይ ስላጡ እንደፈለጉ እንዲቦጠቡጡ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸዋል።
አገር ወዳድ ዜጎች ዘንበል ያለውን የኢትዮጵያ ሰላም ለማቅናት ደፋ ቀና በሚሉባቸው ባለፉት ዓመታት በአ ንጻሩ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉት ሌቦች በአንድ እጃቸው እየሰረቁ በሌላው እጃቸው የግጭትን እሳት ይቆሰቁሱ እንደነበር ከማንም የተሰወረ አይደለም። ምክንያታቸው ምንድን ነው? ከተባለ ሰላም የሰፈነ እንደሁ ስርቆታቸው ይጋለጣል፤ ተጠያቂነት ይሰፍናል፤ ህልውና ቸው አደጋ ይገጥመዋልና ነው።
የኢትዮጵያ ሰላምና የሕዝቦች ደህንነት አንገብጋቢና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ስለነበር መንግሥት የአን ዱን ግንባር ጉዳይ ላጠናቅቅ በሚል አይቶ እንዳላየ ዝም ማለትን መርጦ እንጂ የአገራችን ሌቦች ጉዳይ ራሱን የቻለ ትግል የሚያስፈልገው አንድ ሌላ ግንባር እንደነበር ለማንና ችንም የተሰወረ አይደለም።
ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት መንግሥት ‹‹ቅድሚያ አገርን ማዳን›› ማለቱ ታዲያ ለሌቦች ‹‹ሰርግና ምላሽ›› ሆኖ ላቸው ከርሟል። ዓይናችን እያየ ከባዶ እጅ ተነስተው ከመቅጽበት ባለጸጋ የሆኑትን ቤቱ ይቁጠራቸው።
በሁሉም ዘርፍ ሙስና ስር የሰደደ የአገራችን በሽታ መሆኑ ቢታመንም በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከመሬት ጋር ተያይዞ የሚፈጸሙ ሕገ-ወጥ አሠራሮችን ያህል ሕዝብን ያማረረና የመንግሥትን ጥቅም ያሳጣ አለ ለማለት አያስደፍርም።
ባለንበት ዘመን ከመሬት ቀጥሎ በተቋማት ውስጥ ለሙስና መንሰራፋት እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ጨረታ ነው። በየተቋማቱ ሕጋዊ ከሆነ የግዢና የሽያጭ ሥርዓት ያፈነገጡና ለሙስና የተመቻቹ አሠራሮች ተዘርግተው ለባ ለስልጣኑ፣ ለባለሃብቱና ለደላላው ጥሩ የመጫወቻ ሜዳ ፈጥረዋል።
በተለይም ህዝብን እንዲያገለግሉ ኃላፊነት የተሰጣ ቸው አንዳንድ የመንግሥት አመራሮች አገሪቱ ሲያንዣብ ብባት የከረመውን ደመና ተከልለው ከባለ ሃብትና ከደላ ሎች ጋር እየተመሳጠሩ ሲዘርፉና ሲያዘርፉ መክረማቸው የሚታወቅ ነው።
‹‹ልጅ ከአባቱ ይማራል›› እንደሚባለው የመሪዎቹን ዓይን ያወጣ የዕለት ተዕለት ስርቆት የተመለከተው አን ዳንድ የማህበረሰብ ክፍልም የሕግ የበላይነት ይከበራል የሚል እምነት አጥቶ እርሱም በተሰማራበት ሥራ በአቋ ራጭ የሚከብርበትን መንገድ እያሰላ ሕገ-ወጥ ሥራ በመ ሥራት በኑሮ ውድነቱ መባባስ ላይ የራሱን አስተዋጽኦ ሲያ በረክት ሰንብቷል።
ከተራ የጉልት ቸርቻሪ እስከ ጅምላ አከፋፋይ፤ ከቤት አከራይ እስከ ምግብ ቤት፣ ከትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ህክምና መስጫ ተቋማት፣ ሁላችንም በየፊናችን በአቋራጭ የምንከብርበትን ሕገ-ወጥ መንገድ መከተልን ምርጫችን አድርገን ተገቢ ያልሆነ ዋጋ በማስከፈል በኑሮ ውድነቱ ላይ ቤንዚን እያርከፈከፍን ኑሯችንን እዚህ አድ ርሰነዋል።
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የህብረተሰቡን ባህሪ የቀ የረውና እኔ ብቻ የሚለውን ስግብግብነት ያመጣብን የባለ ስልጣኑ ውስልትና ስለመሆኑ ብዙ ማስረጃዎችን መጥቀስ አያስፈልገንም። ያው ገሃድ የወጣ ጉዳይ ነው።
ከፍ ያለ አቅም ያላቸው ነጋዴዎች የውጭ ምንዛሬ መጨመርን እና የነጻ ገበያውን ፖሊሲ ምክንያት በማድ ረግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ዋጋ በእጥፍ እንዲጨምር ሲያደርጉ ትንንሾቹም ነጋዴዎችና አገልግሎት ሰጪዎች የተ ለያዩ አሻጥሮችን ይሠራሉ። ጄሶን በእንጀራ ፣ ሙዝን በቅቤ፣ ሰጋቱራን በበርበሬ መልክ እያቀረቡልን ገዝተን የተመገብነው በዚህ የተነሳ ነው። የሰው ነፍስ እያጠፉ መኪናን ከነነፍሱ የሚሰርቁ ሌቦች እንዲበራከቱ አስተዋ ጽኦ ካደረጉ ጉዳዮች አንዱ በየተቋሙ ከጥቅም ጋር የተሳ ሰረ ሥራ የሚሠሩ ኃላፊዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣት ነው።
አርሶ አደሩ እያመረተ ከ20 ብር በታች የሚያስረክ በው አንድ ኪሎ ቲማቲም ደላሎች ባረዘሙት የንግድ ሰን ሰለት 80 ብር እስከ መሸጥ የደረሰው፣ የዳቦ ዋጋ፣ የሽንኩ ርት ዋጋ፣ የዘይት ዋጋ ሁሉም ከልክ በላይ እንዲጨምር ያደረገው ነጻው የንግድ ፖሊሲ ሳይሆን ሕገ-ወጥነት ነው። ለሕገ-ወጥነት ግንባር ቀደም ሚና የሚጫወቱት ደግሞ አገርና ሕዝብ የጣለባቸውን አደራ ትተው በሌብነት የተጠ መዱ ባልስልጣኖች መበራከት ነው።
ከሰሞኑ የፌደራል መንግሥት ከትግራይ ክልላዊ መን ግሥት ጋር ያደረገው የሰላም ስምምነት የብርሃን ወጋገን ፈንጥቋል። ብርሃኑ ጦርነቱ በፈጠረው የጨለማ ግርዶሽ ውስጥ ተደብቀው የአገር ሀብትን ሲመዘብሩ የነበሩ ባለስል ጣናትን ፍንትው እያደረገ ማሳየት ጀምሯል።
ያለንበት ወቅት የገባንበት የእርስ በእርስ ጦርነት ያደ ረሰብንን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ እንዲሁም የኑሮ ውድነቱ ያሳደረብንን ተጽዕኖ በመረዳዳት የምንሻገርበት በመሆኑ ሌቦች እየቦጠቦጡ ኪሳቸውን እንዲያደልቡ እድል የምንሰጥበት አይደለም።
ሕዝብን በአግባቡ እንዲያስተዳድሩ የተሰጣቸውን ኃላ ፊነት ለሃብት ማግበስበሻ የሚጠቀሙ ባለስልጣናት ከስር ቆታቸው በተጨማሪ የህዝቡን ተሳስቦና ተረዳድቶ የመኖር ባህል እየጎዱት ስለመጡ መንግሥት የያዘውን ሌቦችን የማደን ዘመቻ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
ሜላት ኢያሱ
አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 4 /2015