ወይዘሮ በላይነሽ ታከለ የራሳቸው የአካል ጉዳት ሳይገድባቸው ሌሎች አካል ጉዳተኞችን በመደገፍ ይታወቃሉ። የሰብአዊ መብት የአካል ጉዳተኛ ተሟጋች ናቸው። በአካላቸው ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት የተገለሉ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መብቶቻቸውንና ማስከበር ላልቻሉ አካል ጉዳተኞች ጥቅሞቻቸውን ማግኘት የሚያስችላቸውን እንቅስቃሴ በማድረግ በአማራ ክልል በስፋት ይታወቃሉ።
በግላቸው እነዚህን የሕብረተሰብ ክፍሎች እየሰበሰቡ በማስጠለል፤ ምግብ፤ አልባሳትና ሌሎች የሚያስፈልጉ ድጋፎችን ያደርጉላቸዋል። የጤናና ሌሎች አገልግሎቶች የማግኘት መብቶቻቸው እንዲከበሩም ያደርጋሉ። የሰብአዊ መብት እንቅስቃሴ ሥራዬ ብሎ በተሰማራው ክፍል ብቻ ሳይሆን በማንኛውም የሕብረተሰብ ክፍልና ግለሰብ ሊከበር ይችላል ይላሉ። በዚህ ተግባራቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተብለው የተሰየሙ ሲሆን በቅርቡ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተሸልመዋል። እውቅናና የምስክር ወረቀትም ተሰጥቷቸዋል።
ወይዘሮ በላይነሽ በተለይ ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸው የዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ኮንቬንሽን ስምምነት እንዲተገበር በብርቱ እንደሚታገሉ ይናገራሉ። ታዳጊ ወጣት ሰርኬ ባዩ ከነዚህ ከሚመደቡት ውስጥ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶችን ማግኘት እንዳስቻሏት ትናገራለች። ‹ወላጆቼ ሞተዋል። ከነሱ ውጪ ሌላ ቤተሰብ አልነበረኝም› የምትለው ታዳጊዋ በተፈጥሮ እጅና እግሯ የመንቀሳቀስ ችግር ኖሮባት መወለዷንና በዚህ ምክንያትም ወላጆቿ በሞት ሲለይዋት የሚንከባከባት ማጣቷን በዚህ የተነሳ የወላጆሽ ዘመድ ነኝ የሚሉ እሷን ከቤት ውስጥ አስወጥተው ጎዳና በመጣል በወላጆቿ ቤት ውስጥ ገብተው መኖራቸውን ታወሳለች።
በዚህ አጋጣሚ ጎዳና ላይ ያገኘዃት ወይዘሮ በላይነሽ ሰብስበው ቤታቸው ውስጥ ያስገቧትመሆኑንም ታስታውሳለች። ታዳጊዋ እንደምትለው ከዚህ በኋላ ወላጅ አልባ መሆኗን በቀበሌ አስመስክረው ነፃ ህክምና እንድታገኝ አደረጓት። ከሕክምናው በኋላ በመጠኑ በዱላ እየታገዘች መንቀሳቀስ ጀመረች። እጇም እግሯም እየተፍታታ መጣ። እስከ 10 ዓመቷ ድረስ በአካሏ ጉዳት ምክንያት ትምህርት ቤት ባትገባም ትምህርት ቤት በማስገባት ፊደል እንድትቆጥር አደረጓት። አሁን የአራተኛ ክፍል ተማሪ ነች።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል የሴሚናር አድቮካሲና ኮሚኒኬሽን ኦፊሰር ወይዘሮ ቃል ኪዳን ተስፋዬ የአካል ጉዳተኛ መብቶች በተለይ ሀገራችን ተቀብላ ያፀደቀችው የተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብት ጥበቃ ስምምነት በተቋማት ብቻ ሳይሆን በግለሰቦችም እየተተገበረ እንደሚገኝ ይናገራሉ። ተቋማችን እነዚህን ግለሰቦች በመሸለምና በመደገፍ ያበረታታል ያሚሉት ወይዘሮ ቃል ኪዳን በዚህ መንገድ ከሚደገፉትና ከሚበረታቱት ወይዘሮ በላይነሽ አንዷ መሆናቸቸውንም ያወሳሉ።
ተቋማቸው ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ሽልማትና ዕውቅና መስጠቱንም ይናገራሉ። በተጨማሪም እንደገለፁት ተቋማቸው ስምምነቱ እንዲተገበር ለተፈፃሚነቱ በጽኑ ይታገላል። አካል ጉዳተኞች የጤና፤ የትምህርትና ሌሎች ማህበራዊ፤ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መብቶቻቸው እንዲከበር ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል። ሰብአዊ መብት ተሟጋች ግለሰቦችን ከማበረታታትና ከመደገፍ ባሻገር የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማትን ያቋቁማል። ከRነሱም ጋር አብሮ ይሰራል።
የኢትዮጵያ ሴት ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ጥምረት አብሯቸው ከሚሰራ ተቋማት ይጠቀሳል። ከተቋሙ ጋር በተለይ የሴት አካል ጉዳተኞችን መብት በማስጠበቁ ረገድ የሚንቀሳቀስበት ማሳያ ነው። ለአብነትም ሴት አካል ጉዳተኞች የጤና እና የትምህርት አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል። ይሄም ስኪሪብቶና ደብተርን ጨምሮ የቁስና አልባሳት እንዲሁም የምግብ ድጋፎችን ይጨምራል። ተቋማቸው አሁን ላይ የኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ተቋምን እያቋቋመ መገኘቱን የሚያነሱት ወይዘሮ ቃል ኪዳን በሕብረተሰቡ ዘንድ ሰፊ ግንዛቤ ተይዞ ስምምነቱ እንዲተገበር ለማድረግ የአካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ለተለያዩ በሰብአዊ መብት ጉዳይ ላይ ለሚሰሩ ተቋማትና የሕብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥም ያወሳሉ። በተቋቋመ በሁለት ዓመት ውስጥ አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ከ300 በላይ ሰዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል። በተለይ 20 የሚደርሱ ለአካል ጉዳተኞች የላፕቶፕ ድጋፎችንም አድርጓል።
የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ በኢትዮጵያ እጅግ በርካታ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችንና ሌሎች የሕግ ማዕቀፎችን በማውጣት በሰፊውና በልዩ ትኩረት እየተሰራበት መገኘቱን የሚናገሩት ደግሞ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞች የአድቮካሲና መብት ጥበቃ ዴስክ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ጥላሁን ናቸው። እንደ አቶ ሲሳይ ከነዚህ ውስጥ አንዱና ትልቁ በተለይ የዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ኮንቬንሽን የሚባለው ነው። የተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብት ጥበቃ ስምምነት በኢትዮጵያ አቆጣጠር በአዋጅ 676/2002 ፀድቆ የሀገራችን የሕግ አካል ሆኗል። እንደ ሀገር ሥራውን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ወስዶ ያስተባብረው እንጂ አዋጁ ሁሉም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችና ተቋማት አካል ጉዳተኞችን በተገቢው መንገድ አካትተው እንዲሰሩ የሚያስገድድ ነው። በዚህ መሰረት እየሰሩ ከሚገኙት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልና የኢትዮጵያ ሴት ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ጥምረት ይጠቀሳሉ። ተቋማቱ የአካል ጉዳተኞችን ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አካታች በሆነ መልኩ አየሰሩ ይገኛሉ።
ለምሳሌ በተደራሽነረት ወስደን ብናይ ተደራሽነት በብዙ መልኩ ይገለፃል የሚሉት አቶ ሲሳይ ህንፃው ለአካል ጉዳተኞች ጉዳተኞች ምቹ ነው ወይ? ፤በተቋሙ መስማት የተሳናቸው ወገኖች አገልግሎት ያገኛሉ ወይም? አገልግሎት የሚያገኙበት ሁኔታ ተመቻችቷል ወይ?፤ ሥራ ቅጥር ሲወጣ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ አድርጎ ነው ወይ?፤ ፈተናውና አጠቃላይ ውድድሩን ፍታዊ ነበር ወይ?፤ ይሄን አልፈው በትክክል ይቀጠራሉ ወይ? የሚለው ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራበት ይገኛል። ፖሊሲና አዋጆች ለአካል ጉዳተኛ ምቹ ናቸው ወይ? የሚለውም ላይ ያተኮራል። በተለይ አንቀጽ 25 ጤና ተቋማት አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም ማህበረሰብ እኩል የጤና አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆኑ የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸውና አካል ጉዳተኞችም የጤና አገልግሎቱን ከሌላው ማህበረሰብ እኩል የማግኘት መብት እንዳላቸው ይደነግጋል።
ይሄንና ሌሎቹን በስምምነቱ የታቀፉትን ሕጎች ሳይሸራረፉ እንዲተገበሩ ለማድረግ ሀገራችን ስምምነቱን ከፈረመች በተለይም ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ከሁሉም ተቋማት የተውጣጣ ቤሄራዊ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራበት ይገኛል። ከኮንቬንሽ አፈፃፀም አንፃር በተጨባጭ ሲታይ ዘንድሮ እንደ ዕቅድ የተያዘው የተቋማት አፈፃፀምን ወደ 60 በመቶ ከፍ ማድረግ ነው። በቀጣይም ሁሉም ተቋማት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት እንዲሰጡ በማድረግ ኢትዮጵያ የፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች መሬት እንዲወርዱ ይሰራል ሲሉም ሃሳባቸውን አጠቃለዋል።
የአሜሪካና የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ አዛዦችም ትናንት በሰጡት መግለጫ ከሰሜን ኮሪያ ሊቃጣ የሚችል ማንኛውም ጥቃት ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል።
ፒዮንግያንግ በዚህ የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ 63 የባለስቲክ ሚሳኤሎችን አስወንጭፋለች። ይህም ካለፈው አመት ከሁለት እጥፍ በላይ መሆኑን ነው የደቡብ ኮሪያው ዮንሃፕ የዘገበው። አሜሪካ በበኩሏ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና ሌሎች የቀጠናው ሀገራትን በማስተባበር ትንሿን ሀገር አደብ ለማስገዛት ጥረት ማድረጓን ቀጥላለች።
ከሀገራቱ ጋር የምታደርገውን የምድር፣ የባህር እና አየር ሃይል ልምምድም ገፍታበታለች። ይህ ወታደራዊ ልምምድን እንደ ብሄራዊ ደህንነት ስጋት የምትመለከተው ፒዮንግያንግ ቁጣዋን እንደተለመደው በመድፍ ተኩስና በሚሳኤል ማስወንጨፍ እየገለጸች ነው ሲል አል ዐይን ዘግቧል።
ቁጥር በ52 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየም ይነገራል። በአጠቃላይ በኢሚሬትስ 2 ሺህ 577 ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ የተሳተፉ ሲሆን የ114 ሀገራት ዜግነት ያላቸው ሰዎችም በሀገሪቱ በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተው እንደሚኖሩ አል ዐይን ዘግቧል፡፡
ሰላማዊት ውቤ
አዲስ ዘመን ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም