አሶሳ፡– በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአምስት አካባቢዎችና በሃያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በኦሮሚኛ ቋንቋ እየተሰጠ ያለው ትምህ ረት የሁለቱን ክልል ህዝቦች የሚያስተሳስር መሆኑ ተገለጸ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተ ዳድርና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በኦሮሚኛ ቋንቋ ትምህርት ከሚሰጥባቸው ትምህርት ቤች አንዱ የሆነውን የባምባሲ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰን ትናንት በትምህርት ቤቱ የጉብኝት ስነ ስርዓት ላይ እንደገለጹት። በክልሉ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ልጆቻቸው በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በመተከል ዞን በከማሺ፣ በማኦ ፣ኮሞና በአሶሳ በሃያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ትምህርቱ እንዲሰጥ ተደርጓል።
በአሁኑ ጊዜም የፀጥታ ችግር ካለባቸው የተወሰኑ አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛዎቹ በጥሩ ሁኔታ ትምህረቱ እየተሰጠ ይገኛል። እንደ ፕሬዚዳንቱ ማብራሪያ የፀጥታ ችግሩ እየረገበ በመሆኑ የማስተማሩ ሥራ ይጠናከራል።
ትምህርት ባልተጀመረባቸው አካባቢዎችም በሂደት ተሟልቶ ትምህረቱ ይሰጣል። ትምህርቱ በአንደኛ ደረጃ በአንደኛ ክፍል ቢጀመርም በሂደት ዝግጅቱን ከፍ የማድረግ ሥራ ይሠራል። በትምህርትና በሌሎችም የልማት ሥራዎች የሁለቱን ክልል ህዝቦች ማስተሳሰሩ የባለቤትነት ስሜት እንደሚፈጥር ርዕሰ መስተዳድሩ
አመልክተዋል።
በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደረጃ የግብርናና ገጠር ልማት ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ በበኩላቸው፣ ክልሉ የተለያዩ ምክንያቶችን ሳያቀርብ ለጥያቄው ምላሽ መስጠቱ እንደሚያስመሰግነው ገልዋል።
በክልሉ ብዙ የኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መኖራቸው በሰው ኃይል ወይም በመምህራን በኩል ችግር እንዳልገጠመው አስታውቀዋል። የኦሮሚያ ክል ልም የመማሪያ መሐፍትን አዘጋጅቶ በማቅረብና ለመምህራን ስልጠና ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።
በአሁኑ ጊዜ ከኦሮሚያ ክልል ውጪ ባሉ ኸረሪ፣ ሶማሌ እና ቢኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኦሮሚኛ ቋንቋ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን አመልክተዋል።
የባምባሲል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ተፈሪ ቱፋ እንደገለጹት፣ ትምህረት ቤቱ በ1943 ቢመሰረትም በትምህርት አሰጣጡ ለውጥ እያስመዘገበ የመጣው ከ1990 ዓ.ም ወድህ ነው።
እስከ ዛሬም በበርታኛ እና በአማርኛ ቋንቋዎች ሲያስተምር መቆየቱንና በ2011 ደግሞ በኦሮሚኛ ቋንቋ 165 ሕፃናትን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል። አምስት መምህራኖችም እንዳሉት አመልክተዋል። ትምህርት ቤቱ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል 2 ሺ 788 ተማሪዎች እያስተማረ እንደሆነም ገልጸዋል።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 1/2011
በ ለምለም መንግስቱ