የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በተለያዩ ከተሞች ‹‹ስለኢትዮጵያ›› የተሰኘ መድረክ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ በመድረኮቹ በተለያዩ አገራዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ በነዚህ መድረኮች ለውይይት በሚቀርቡ ርዕሰ ጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ትልልቅ ሰዎችም የውይይት መነሻ ሀሳቦች ይቀርባሉ፡፡ በመድረኩ ሲነሱ ከቆዩ በርካታ ጉዳዮች መካከል ኪነ ጥበባዊ ይዘት ባለው መልኩ በግጥም የተላለፉ ሃሳቦችም ይገኙበታል። እኛም በዛሬው የዘመን ጥበብ ዓምዳችን ቅርበት ያለውን እና በአንድ መድረክ ላይ የቀረበውን የአቶ መስቀሉ ባልቻን ግጥሞች እንደሚከተለው ሙሉውን አቅርበነዋል፡፡
ሰው አልለው አውሬ
ተፈጥሮ ባገሬ
የራሱን ሞት ሞቶ መርዶ ያረዳኛል
ምሰሶና ካስማ ዋልታ ለሀገሩ
የዜጋ ጥላውን የሀገር ጠበቃውን
ሰሜን እዝን መታሁ እያለ ያቅራራል
የራሱን ሞት ሞቶ መርዶ ያረዳናል
መብረቅ ምት-መታሁት ብሎ ይፎክራል፡፡
ጉድ አሰኘንኮ ከሰው ተራ ውሎ
የተንቤኑ ተኩላ በሰው ተመስሎ
የአካሄድ መስመሩ ቋሚ መፈክሩ፤
ቤቱን ዱር አረጉ ወግ ማዕረጉን ሻሩ
ሚስት ከባሏ ፊት
ልጅን ከአባት እቅፍ ነጥቃችሁ ድፈሩ
እህል ስታገኙ ከቻላችሁ ብሉ
ተክል ካያችሁም እንዳያድግ መንጥሩ
የሚተርፍ ከሆነ በእሳት አቀጣጥሉ
የመኖሪያ ዕቃ ሰባብሩና ጣሉ
ምን ያረጋል ወንበር ሶፋ አልጋ ቅብጥሩ
ሰው መሆንን ጥሎ ከአውሬው መተባበር
የተንቤኑ ተኩላ የራሱ መፈክር
አጥፍቶ መጥፋት ነው ዜማ የሱ መዝሙር
ደግሞ ትምህርት ቤት
ምን ያረጋል ትምህርት
ጤና ጣቢያ ብሎ ሕክምና
አልጋ ማዋለጃ
ላቦራቶሪ ብሎ የሰው ማታለያ
ንቀሉና ጫኑ ኮምፒውተር አይተረፍ
እነሱ ይብቃቸው ከተንቤን ይታረፍ
የሰው ምስል የለው የተንቤኑ ተኩላ
ለመቀነስ እንጂ ደርሶ ለመጨመር ምንም የለው መላ
ድሮ የቀረ ስልት
ቤተ መቅደስ መስጂድ ምን ያረጋል እምነት
በኩነኔ በጽድቅ አስፈራርቶ መግዛት
ድሮ ቀርቷል
ሽማግሌ አሮጊት ለምን ይከበሩ
ለምንስ ይኑሩ
ክብር ውርደት ብለው ምግባር ከሚቆጥሩ
ለምንስ ይኑሩ
ይወገዱትና ሌሎች ይፈጠሩ
ያልኖሩ ይኑሩ
የተንቤኑ ተኩላ እንዲህ በልቶ በልቶ
እንዲህም አስልቶ
እፎይ ይላል በቃ አገርን አራቁቶ
ዕውቀትን ለመቅበር ትግሉ ተሳክቶ
በትግል አይጨምሩ ታግለው ያጎላሉ
የተንቤኑ ተኩላ እንዲህ ጉድ ያዘሉ
ከሰው ተራ ወጥተው ታጋይ ነን ይላሉ፡፡
ፍቅር ሰብዓዊነት ምን ያረጋል ስብከት
ጽድቅና ኩነኔ ያልሰከነ ኮተት
እንደ ዶሮ ፈንግል ፈንግለህ ተቀበል
ፈንግለህ ተበቀል፡፡
እቺ እኮ ናት ትግል
ምንም አታወላውል
እቺን ካልተገበርክ
ስምነው የተሸከምክ
እምኑ ላይ ታገልክ
ብሎ ሲወሰወስ
የተንቤኑ ተኩላ በሰው ተመስሎ
ጉድ አሰኘን እኮ ከሰው ተራ ውሎ
አያፍር አይነውር
በፀያፍ መፈክር ሀሳብ ሲሰነዝር
“ከእንስሳት ተጣላ ተኩስና ግደል
እሱ እየኖረ ነው እኛ የምንበደል
ነፃ አወጣ ምድሪቱን ዱር አድርገህ መንጥር እንኳን ሳይቀር
ጠላት ናቸው ብለህ እንስሳትን አባር
ጋንጃህን አሽትተህ ኃይልህን አጠናክር
ስበር ገነጣጥል የይሉኝታን አጥር
ከቻልክበት ሥፈር
አቅራራና ፎክር
የተንቤኑ ተኩላ የተንቤን እፉኚት
ጠባ ጠብ ቆስቁሰህ መግባባት አሽቀንጥር
ተንቤን የጉድ ሠፈር
ተንቤን የጉድ መንደር
አለው ልዩ ምክር አለው የሚዘከር
ውለታን እንዳትቆጥር
መግደል ምን አለበት
ማንም ሰው ይገላል
እስኪ ተመራመር
አዲስ ነገር ፍጠር
ከገደልክ በኋላ
አስከሬን ላይ ጨፍር
ቀሚስ ካየህ አትማር
መነኩሲቷን ድፈር
ሃይማኖትና እምነት ከምንም አትቁጠር
ስሜትህን ኰርኩር በስሜት ተሣፈር
ከጠባቧ ጐጆህ ከእኩያኑ ሠፈር
አታሞህን ደልቅ መዝሙርህን ዘምር
ዜማህን አንቆርቁር
ቁልቁለት ተንደርደር
ከባዕድ ነው መምከር!
ትልቅ ምን ያደርጋል ከትንሽ ተፋቀር
ከተንቤን ነው ማደር
ያው መጥፊያህን ቆምር
ኢትዮጵያ ሰማሽ የተንቤንን ዜማ
ልበ ትንሽ ልጅሽ ከባዕድ ሲስማማ
ዜጋሽን ሲያደማ
የአድዋ የዶጋሊ ታሪክሽ ላይሠማ
አልወርስም ሲል አየሽ?
ከታሪክሽ ሲሸሽ
ከዜሮ ሲጀምር የተንቤኑ ተኩላሽ
ባለ ዜሮ ድምር እፉኚቱ “ልጅሽ”?
የጀግኖችሽ አፅም ይጮሀሉ ከሩቅ
ከተንቤኑ ተኩላሽ ምንም አይጠበቅ፡፡
ካህኑም ማለለ ማለ አማማለ
በስምሽ ላይቀድስ ገዘትኳችሁ አለ፡፡
አንቺ ማህፀነ ለምለም
ታላቁ ሲታመም ታናሹን ነው ማከም
ወጣ ምንም ቢሆን ታሪክሽን አይረሳም፡፡
አይደልለው ጥቅም፡፡
ትውልድን ነው ማከም።
በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
ለደሴው ለተካሄደው
የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ
ታኅሣሥ 10 ቀን 2014 ዓ.ም
ሽሽጉ አድማስ
አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ.ም