የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ከትናንት በስቲያ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን የአንድ ዓመት የሥራ ቆይታ ‹‹ከመጋቢት እስከ መጋቢት›› በሚል ርዕስ በሚሌኒየም አዳራሽ ደማቅ ዝግጅት አድርጓል። በዚህ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ኢትዮጵያዊ አንድነትን እንዲጎለብት ይሰ ራል›› በማለት መናገራቸው ይታወሳል።
‹‹ኢትዮጵያውያን ሰይፍ ያስፈልገናል›› ሲሉም የእርቅና የሰላም ጉዳይ ላይ አፅንኦት ሰጥተዋል። በመሆኑም ይህን እቅዳቸውን ሕዝብ እንዴት ተረዳው? የዜጎች ሚናስ ምን ሊሆን ይገባል? ወይዘሮ አምሳለገነት አባቴነህ ይባላሉ በኢትዮጵያ ጥንታዊት አርበኞች ማህበር ሠራተኛና የአርበኛ ልጅ ናቸው። እርሳቸው እንደገለፁት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ከያ ዙበት ጊዜ አንስቶ ስለኢትዮጵያ አንድነትና ሁላ ችንም አንድ እንድንሆን መክረውናል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ኢትዮጵያዊ አንድነት ሲናገሩ አባታቸውን እንደሚያስታውሳቸው የሚ ገልጹት ወይዘሮ አምሳለ ‹‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ ውስጥ ሁሌም ኢትዮጵያን አያለሁ። እርሳቸውን ሳይም ሀገሬ ቁጭ ብላ የምታስተምረኝ ነው የሚመስለኝ። አባቴም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለአንድነት የሚነግሩንን ነበር እያስተማረ ያሳደገን›› ይላሉ። ‹‹በትምህርት ቤት፣በጎረቤትና በአካባቢያችን ያሉትን እንደ እህትና ወድም እንድናያቸው ነው የመከሩን። ስለዘር ሳይሆን ስለ ሰዎች መዋደድ እና መከባበር ነው የነገሩን። አባቴ በውስጤ ያሳደሩት የሰው ፍቅር ዛሬ በውስጤ አለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለኢትዮጵያዊነት ሲናገሩም የበፊቱ ሊመጣ ነው? እንዴ እያልኩ በደስታ ጮቤ እረግጣለሁ›› ሲሉ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያዊ አንድነት ላይ ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት የሚሉት ወይዘሮ አምሳለ በዚህ ዙሪያ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መፎካከራቸው በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ችግር መፍጠር የለበትም ሲሉ ይመክራሉ። አንዳንዶችም ወደ አንድ እየመጡ በመሆኑ አንድነት ላይ ይሰራሉ ብለው እንደሚያምኑ ጠቁመዋል። ለውጡን የማይ ደግፍ ሰው አለ ብለው እንደማያምኑም ወይዘሮዋ ተናግረዋል። በባህልና ቱሪዝም ላይ የሚሰሩት ጋዜጠኛ ዘሪሁን ግርማ እንዳሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊ አንድነት ዛሬ የተጀመረ አስተሳሰብ ነው ብለው አያምኑም።
አንድነት የኢትዮጵያውያን መገለጫና ዓለምም የመሰከረው መሆኑን ይገልጻሉ። የተለያየ ሀሳብ እንኳን ቢኖር በኢትዮጵያዊነት ላይ ልዩነት እንደሌለ ይናገራሉ። ጋዜጠኛ ዘሪሁን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸረሸረ የመጣው የኢትዮጵያ መገለጫ የሆኑት መልካም እሴቶች ናቸው ይላሉ ። በሥራቸው አጋጣሚ ያስተዋሉትን እንደገለጹት ከ80 በላይ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ብሄሮችና ብሄረሰቦች የየራሳቸው የሆነ መገለጫ አላቸው። እነዚህን ከማሳደግና ከማስተዋወቅ ይልቅ ባለፉት ዓመታት ሲሰራ የነበረው ‹‹እኛን ከእከሌ የሚለየን›› በሚል የራስን በማጉላት ላይ የቆየው ትርክት ነው ሲሉ ይወቅሳሉ። በዚህ ረገድ የሚጠየቁ ብዙ ሰዎች ይኖራሉም ብለዋል።
የታሪክ ምሁራን ብሄረሰቦችን መሰረት አድርገው የሚጽፏቸው የታሪክ መጽሐፍት መፈተሽ አለባቸው። አብዛኞቹ የየብሄረሰቡ አባላት ስለሚደርስባቸው የብሄር ጭቆና ነው የሚያወሱት። ይሄ አንዱ በሌላው ላይ ጥሩ አመለካከት እንዳይኖረውና ከአንድነት ይልቅ እንዲለያይ መንገድ የከፈተ ነው። በተለይ ደግሞ በፖለቲካ ቅኝት ሲታይ የኢትዮጵያዊ አንድነት መሰረት የሆኑትን ባህልና እሴት ማሳጣቱን ጋዜጠኛው ያስረዳሉ። በተለያየ ምክንያት እየተሸረሸረ የመጣው ኢትዮጵያዊ አንድነት እንደሚከነክናቸው የሚና ገሩት ጋዜጠኛው በፖለቲካው ውስጥ ያሉ አካ ላት ኢትዮጵያን በደንብ ማየት እንዳለባቸው ይመ ክራሉ።
ለረጅም ዓመታት ከሀገር ርቀው የቆዩና ታሪክንም ሳያገናዝቡ በድፍረት ከመናገር ተቆጥበው ከፖለቲካቸው ጋር ማራመድ እንዳለባቸው ይና ገራሉ። ‹‹ሁለት ኢትዮጵያ ያለች ነው የሚመስለኝ። ከፖለ ቲካው ውጭ ያለውና በገጠር የሚኖረው ማህበረሰብ ጋር ኢትዮጵያዊነትን ጠብቆ እየኖረ ነው። ሰለጠነ በሚባለው ጋር ስለኢትዮጵያ የሚቀነቀነው ሌላ ነው።ይሄ መስተካከል አለበት›› በማለት እርሳቸው በግላቸው ሥራቸውም ከባ ህልና ቱሪዝም ጋር የተያያዘ በመሆኑ ልጆቻቸው መልካም ዜጋ እንዲሆኑ የበኩላቸውን ለመወጣት ጥረት እያደረጉ መሆኑን አመልክተዋል።
‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በንግግራቸው የተለያዩ ማንነቶች አሉን። ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የተለያዩ መጠሪያ የሆኑ ስሞች አሏቸው። ግን እነዛ ስሞች ብቻቸውን ኢትዮጵያን ነጥለው ሲያወጡ የተሟላ እንደማይሆንና ለምሳሌም የአፋር ተወላጆች በተለያየ ቦታ እንደሚኖሩና ግን ኢትዮጵያዊ አፋር የተለየ እንደሆነ፣ ኦሮሞም እንደዚያው በኬኒያ የሚኖሩ ኦሮሞዎች እንዳሉ፣ ኦሮሞን ለየት የሚያደርገው ግን ኢትዮጵያዊ እንደሆነ አጉልተው ነግረውናል›› በማለት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት ሃሳባቸውን የሰጡን ዶክተር ጌታቸው ድንቁ ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንድነት ላይ ብቻቸውን የሚያደርጉት ጥረት በቂ እንዳልሆነና ኢትዮጵያዊነት ሁሉንም አንድ የሚያደርግ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም እንደዜጋ ኃላፊነት እንዳለበት መምህሩ ይገልጻሉ። ‹‹ኢትዮጵያዊ አንድነት እና ሰላም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየአጋጣሚው በሚያደርጉት ንግግር ብቻ አይቀየርም። በሁላችንም እጅ ያለ ጉዳይ ነው። በትምህርት ቤት፣ በቡና ላይ በእድር እና በሌሎችም በማህበራዊ መገናኛዎች መጎልበት አለበት›› የሚሉት ዶክተር ጌታቸው ግድፈቶችን ፊትለፊት በመጋፈጥ ማረም እንደሚገባ ይናገራሉ።
መንግሥት ‹‹እንደ እከሌ ሀገር ትሆናላችሁ›› እያለ እንዲናገር እንደማይጠበቅም ጠቁመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተአምር እንዲያመጡ እንደማይጠበቅ የሚናገሩት ዶክተር ጌታቸው የተካረሩ ፖለቲከኞች እና ፓርቲዎች መነጋገር መጀመራቸው፣ህዝብም በነጻነት ሀሳቡን መግለጽ መጀመሩን ከለውጡ መካከል የሚጠቀሱ እንደሆኑ ተናግረዋል። ይህም ኢትዮጵያዊ አንድነትን በማጠናከር ለውጡን እየገነቡ መሄድ እንደሚገባ በአስተያየታቸው ገልጸዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያዊ አንድነት ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት እንደሚደግፉ የተናገሩት በኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ ፀሐፊ መጋቢ ሚስጥር ፍሬስብሀት ‹‹እግራቸውን ለጠጠር ደረታቸውን ለጦር ሰጥተው የሀገራቸውን ዳር ድንበር ያስከበሩ ጀግኖች አባቶችና እናቶች ያወረሱን የሀገር ፍቅር ነው።ያንን መዘንጋት የለብንም ።የነበረውን ታሪካችንን መመለስ አለብን›› ሲሉ ገልጸዋል።
ሀሰተኛ ታሪክ ለትውልድ የሚያሸጋግረውን ማጋለጥ እንደሚገባና ከእርሳቸው ጀምሮ ትው ልድ በመቅረጽ ላይ መስራት እንደሚጠበቅም አመልክተዋል።እርሳቸው በሚያገለግሉበት የእም ነት ተቋማት እና በማህበራዊ አገልግሎቶች ማህበ ረሰቡን በማስተማር ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆኑ ሲያስረዱ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን እንዲያበረክትም ጥሪ በማቅረብ ነው።
አዲስ ዘመን መጋቢት 26/2011
በለምለም መንግሥቱ