የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ እና የፌዴራል ዳኞች ለማጥራት ተሻሽሎ የተዘጋጀው አዲስ ረቂቅ አዋጅ የፍትህ ስርዓቱ ወደ ተሻለ ደራጃ የሚያደርስ መሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ገለፀ፡፡
ዛሬ ጠዋት በካፒታል ሆቴል ተሸሽሎ በረቀቀው አዲሱ አዋጅ ላይ ውይይት በተካሄደበት ወቅት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ የፍትህ ስርዓቱ ለማሻሻል የሚያስችሉ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች በማዘጋጀት ህብረተሰቡ በፍትህ አካላት ላይ እምነት እንዲያሳድር እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
“ሰላምና ዲሞክራሲ ያለ ፍትህ ተቋማት ጥንካሬ ማራጋገጥ አይታሰብም፡፡” ያሉት ፕሬዚዳንትዋ የፍትህ አካላቱ ነፃና ገለልተኛ ሆነው እንዲዋቀሩና ያላቸው በጎ ሚና ለማጉላት ህጎችን ለማሻሻል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ የህግ ባለሙያዎችን ያካተተ የዳኝነት ስርዓት ማሻሻያ ጉባዔ በማቋቋም ማሻሻያ ረቂቅ አዋጆቹ በማርቀቅ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
ከሌሎች ሀገራት የፍትህ ስርዓት ተሞክሮ በመውሰድ የቀድሞ ህግ ያሻሽላል የተባለው አዲሱ ረቂቅ አዋጅ የተዘጋጀው ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች መሆኑ አመልክተዋል፡፡
አማካሪ ጉባዔው 17 አባላት ያቀፈና ሶስተ ንዑስ ኮሚቴዎች ያሉት ሲሆን በዳኞች አስተዳዳር ጉባዔ እና የፌዴራል ዳኞች ለማጥራት የተላዬ ማሻሻያ ህጎች በመመርምር ስያዘጋጅ መቆየቱ ተጠቁሟል፡፡
ቀድሞ የነበረውን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስልጣንና ተግባር የሚደነግገው አዋጅ 25/88 እና ማሻሻያዎቹን በመመርምር አዲስ አዋጆችን በማርቀቅ የዳኝነት ስርዓን ለማስተካከል የሚያስችል አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑ ገልፀዋል፡፡
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ የህግ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ሙያተኞቹ ቀድሞ የነበረውን ህግ በነጻነት በመመርምር ማሻሻያ ያደረጉበት መሆኑ ጠቁመው ህጉ በሚመለከተው አካላት እስኪፀድቅ ድረስ የህግ ባለሙያዎችና ጉዳዩ የሚመለከተው አካላት ማጠናከሪያ እነዲሰጡበት ለውይይት መቅረቡ ተናግረዋል፡፡
ተገኝ ብሩ