በትምህርት ሚኒስቴር የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት ባለሙያው አቶ ጳውሎስ ነሚ ከቡራዩ አዲስ አበባ እየተመላለሱ ነው የሚሰሩት። አቶ ጳውሎስ ከቡራዩ እስከ ሳንሱሲ በተለያዩ የትራንስፖርት አማራጮች እንደሚጓጓዙ ይናገራሉ። ከሳንሱሲ እስከ አራት ኪሎ ድረስ ደግሞ የሚጓጓዙት በፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት ነው ።
በፐብሊክ ትራንስፖርት አገልግሎት ከፍተኛ እርካታ እንደሚሰማቸው የሚናገሩት አቶ ጳውሎስ፣ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት መጠቀም ከጀመሩ ዘጠኝ ወራት ተቆጥረዋል። የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ከመሆናቸው በፊት በወር በጥቂቱ 90 ብር ያወጡ ነበር። አገልግሎቱ ይህን ወጪ አስቀርቶላቸዋል፤ ስራ በጠዋት እንዲደርሱ፣ ከስራ ሲወጡም በጊዜ ወደ ቤታቸው እንዲገቡም አስችሏቸዋል።
አቶ ጳውሎስ የአገልግሎቱ ተግዳሮቶች ያሏቸ ውንም ይጠቁማሉ። ድርጅቱ ለነፍሰ ጡሮች
ለአካል ጉዳተኞችና በእድሜ ከፍ ላሉ ወንበር ቅድሚያ እንዲሰጥ ቢያሳስብም በተጠቃሚዎች በኩል ትልልቅ ሰዎችን የማክበር ባህል እንደማ ይስተዋል ይጠቁማሉ። ወጣቶች ለትልቅ ሰዎች ወንበር የመልቀቅ ባህልን ማዳበር እንዳለባቸውም ይመክራሉ።
አገልግሎቱ እስከ ቡራዩ እንዲደርስላቸውም አቶ ጳውሎስ ይጠይቃሉ። ከቡራዩ የሚመላለሱ ተሳፋሪዎች ለድርጅቱ በደብዳቤ አገልግሎቱ ይራዘምልን ሲሉ በፈርማቸው ያቀረቡትን ጥያቄ በጥቅምት ወር አካባቢ ማቅረባቸውን አቶ ጳው ሎስ ያስታውሳሉ። ከመሥሪያ ቤታቸው ብቻ 20 የሚደርሱ ሠራተኞች ከቡራዩ እየተመላለሱ እንደሚሰሩ ጠቅሰው፣ ጥያቄውን የሚመለከተው አካል አይቶ ምላሽ እንዲሰጣቸውም ይጠይ ቃሉ።
የብሔራዊ ቲያትር ባልደረባው አቶ መኮንን አሰፋም የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት ፋይዳ ብዙ መሆኑን ይገልጻሉ። ሠራተኛው በሰዓቱ ሥራው ላይ እንዲገኝ ያደርጋል፤ ከእንግልት ይታደጋል፤ ለሌሎች የትራንስፓርት አማራጮች የሚወጣውን ወጪ ያስቀራል፤ ትራንስፖርት በመጠበቅ የሚጠፋውን ጊዜ ያስቀራል›› ሲሉ ያብራራሉ።
አቶ መኮንን ከዊንጌት ተነስተው መሥሪያ ቤታቸው ብሔራዊ ቲያትር ለሁለት ሩብ ጉዳይ አካባቢ ይደርሳሉ፤ ይህም ለሥራ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ አስችሏቸዋል፤ ‹‹አገልግሎቱ ባይኖር ጠዋትና ማታ ቢያንስ 15 ብር ገደማ አወጣለሁ፤ ይህ በሳምንት ሲሰላ ከ75 እስከ መቶ ብር፣ በወር ሲሰላ ደግሞ ቢያንስ 300 አወጣ ነበር›› የሚሉት አቶ መኮንን፣ በጊዜ ስራ መግባት ትኩረት ሰጥተው ሳይጨናነቁ እንዲሰሩ እንዳስቻላቸው ያብራራሉ።
በሰርቪሱ ላይ ሠራተኛው እንደ እኔ ተመሳሳይ ስሜት አለው የሚሉት አቶ መኮንን፣ የተለየ አመለካከት ያለው ተገልጋይ እንዳላጋጠማቸውም ይናገራሉ።
በሰራተኛው ዘንድ የሚስተዋሉ ችግሮችም እንዳሉም በመጥቀስ፣ አንዳንዴ ለመሳፈር ከመቸኮል የተነሳ መታወቂያ እንደማያሳዩም መታቂያ ይዘው የማይገኙ እንዳሉም ይጠቁማሉ። ተገልጋዩ ሰርቪስ ሲገባ መታወቂያውን እያሳየ ቢገባ መልካም እንደሆነም መክረው፣ አንዳንዴ በማይረባ ነገር ሲጨቃጨቁ እንደሚመለከቱም ነው የጠቀሱት።
እስካሁን እየሰጠ ያለው አገልግሎት ጥሩ መሆኑን ጠቅሰው፣ ‹‹በሰዓቱ ይነሳል በሰዓቱ ይደርሳል›› ይላሉ። አንዳንዴ ከሚያጋጥመው የትራፊክ መጨናነቅና መዘጋጋት ውጪ አሽከ ርካሪዎቹም ጥሩ አገልግሎት እንደሚሰጡ ነው የሚናገሩት። ብዙ አሽከርካሪዎች እንደሚቀያየሩ የአገልግሎት አሰጣጣቸው ግን ተመሳሳይ እንደ ሆነም ይናገራሉ።
በኢትዮዽያ መንገዶች ባለሥልጣን መዝገብ ውስጥ ሲሠሩ ያገኘዋቸው አንዲት ሠራተኛም ከሳሪስ እስከ ለገሀር በፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት ይጓጓዛሉ። አገልግሎቱን እሳቸውም ጥሩ ሲሉ ይገልጹታል።በዚህም በቀን ሊያወጡ የሚችሉትን አሥር ብር እንዳስቀረላቸውም ያመለክታሉ።
የፐብሊክ ትራንስፖርት አውቶብስ ካፒቴን/ አሽከርካሪ/ አበበ ካብትይመር ከሽሮሜዳ ስድስት ኪሎ አራት ኪሎ መገናኛ ቦሌ ሜክሲኮ ያለውን ረጅም መስመር እንደሚሸፍኑ ይናገራሉ።
ተገልጋይ የመንግሥት ሠራተኞች መታ ወቂያ አሳዩ ሲባሉ መብታቸውን የነካህ ይመስ ላቸዋል የሚሉት ካፒቴኑ፣ አታቀኝም ወይ ብሎ የሚጨቃጨቅ እንዳለም ይገልጻሉ። መሥሪያ ቤቱ ከሚሰጠው ሥልጠና ብዙ ትም ህርት ቀስመዋል፤ ችግር ሲገጥማቸው በትዕ ግሥት ያልፋሉ። እየተሳደቡም ከአውቶብሱ የሚ ወርዱም እንዳሉ ይጠቁማሉ።
የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የትራንስፖርት ኦፕሬሽን አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል ተዘራ እንዳሉት፤ ድርጅቱ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 298/2006 ተቋቁሞ ከመስከረም 5ቀን2007 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት እየሠጠ ይገኛሉ።
አገልግሎቱ የመንግሥት ሠራተኛውን የዘመ ናት የትራንስፖርት ችግር የቀረፈ፣ እንግልትን ያስቀረ፣ ሠራተኛው በሰዓቱ ሥራው ላይ እንዲገኝና ባለጉዳዮችም በፍጥነት የመንግሥት አገልግሎት የሚፈልገውን የፌዴራልና የአዲስ አበባ አስተዳደር ሠራተኛ እንዲስተናገዱ የረዳ ሲሉ ፋይዳውን ያብራራሉ። ሠራተኛውም ከሥራ መልስ ወደ ቤቱ ትራንስፖርት ሃሳብ ሳይሆንበት ተረጋግቶ እንዲሄድ ያስቻለ ነው ሲሉ ያብራራሉ።
በየጊዜው እየጨመረ የሄደው የትራንስፖርት ዋጋ በሠራተኛው ምጣኔ ሀብት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያደርስ እንደነበር አስታውሰው፣ ሥራው ሲጀመር የመንግሥት ሠራተኛው ፍላጎት የመለየት ተግባር መከናወኑንም ይገልጻሉ።
አቶ አማኑኤል እንደሚናገሩት፤ አገልግሎቱ የተጀመረው በ55 አውቶቡሶች የነበረ ሲሆን፣ አሁን የአውቶብሶች ቁጥር 410 ደርሷል፤ ዘወትር 390 አውቶቢሶች ለሠራተኛው አገልግሎት ለመስጠት ይሰማራሉ። በቀን 130 ሺ ሠራተኞችን ያጓጉዛል። ለአገልግሎቱ 11ነጥብ 25 ብር በየቀኑ ወጪ እንደሚደረግና በዓመት ለአንድ ሠራተኛ 2ሺ835 ብር እንደሚከፍል ያስረዳሉ ።
እንደ የካ አንድ፣ የካ አባዶ፣ ቦሌ አራብሳ፣ ቱሉ ዲምቱ፣ ኮዬ ፈጬ፣ ቂሊንጦ የመሳሰሉ አካባቢዎች የገቡ ሠራተኞች ብዙ እንደነበሩ አስታውሰው፣ እነዚህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሰራተኞች ጭምር የትራንስፖርት አገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ መሰራቱን ይገልጻሉ።
ለጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በርካታ ተሽከርካሪዎች ተመድበው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ጠቅሰው፣ የካ አባዶ ወደ 11 ቦሌ አራብሳ 10 ተሽከርካሪዎች ተመድበው እየሰሩ መሆናቸውን ይጠቁማሉ።
አገልግሎቱን ለማስፋትና ከተሳፋሪዎች ጥያቄ ቢቀርብ ለመፍታት አለመቻሉን ጠቅሰው፣ ወደፊት የመሥሪያ ቤቱ ማቋቋሚያ ደንብ በማሻሻል የአገልግሎቱን ፈላጊዎች ጥያቄ ለመመለስ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞች አገልግሎት ለመስጠት መታሰቡን ይጠቁማሉ።
አዲስ ዘመን መጋቢት 10/2011
በ ኃይለማርያም ወንድሙ Mz7u�M=U