ልጆች እንዴት ናችሁ፤ ሰሞኑን በተከታታይ አስተማሪ ተረቶችን፣ አንዳንድ እውነታዎችን ስናቀርብላችሁ ቆይተናል። ዛሬም እንደተለመደው ስለእንስሳት አንዳንድ እውነታዎችን በጥቂቱ ይዘንላችሁ ብቅ ብለናል። እስከዛሬ እድሉን ላላገኛችሁ ልጆች የዛሬው መነሻ ይሁናችሁና በሚገባ አንብቡት። ነገር ግን አስተያየትና የተለያዩ ጽሁፎችን ለእኛ ማቀበል ለምትፈልጉ ልጆች አድራሻችን ይህንን ይመስላል።
ስልክ 011-1-26-43-26 ሲሆን፤ ኢሜል ደግሞ mihretchanyalew@ gmail.com ብላችሁ ብትልኩልንም ይደርሰናል። • ሰጎን በፍጥነት ከፈረስ ይበልጣል ፣ ወንዱ ሰጎን የአንበሳን ድምፅ አስመስሎ ማግሳት ይችላል። • ካንጋሮ ጅራቷ ሚዛን መጠበቂያዋ ነው፣ ጅራቷ መሬት ካልነካ መዝለል አትችልም። • ነብር ላይ የምናየው መስመር የተሰመረው ፀጉራቸው ላይ ብቻ አይደለም። መሥመሩ እስከቆዳቸው ይዘልቃል፣ ሆኖም የአንዱ ነብር መስመር ከሌላኛው
ነብር ጋር በጭራሽ አንድ አይሆንም፤ • ድመት በእያንዳንዱ ጆሮዋ ላይ 32 ጠንካራ ጡንቻዎች አሏት። ለሁለቱም 64 መሆኑ ነው ይህም ነገሮችን ከርቀት ለመስማት ያስችሏታል። • ቢሄፈር የሚባለው የአይጥ ዘር በህይወት እስካለ ድረስ ጥርሱ ማደጉን አያቆምም። ስለዚህ ጥርሡን ለመቆጣጠር ጠንካራ ነገሮችን መንከስ የዘወትር ተግባሩ ነው። • ጉንዳን በህይወቱ እንቅልፍ የማይተኛ እና ሳንባ የሌለው ብቸኛ ፍጡር ነው። • ዝሆን ውሃን ከ3 ማይል ርቀት ማሽተት ይችላል፤ እድሜው ሲገፋ ከሰው ልጅ እና ከአሣ ነባሪ ቀጥሎ የእርጣት ዘመን የሚያስተናግድ እንስሳ ነው። ምንጭ፡- Animal Facts