• ለ157 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው አደጋ መንስኤ እየተጣራ ነው
• አየር ላይ ከፍተኛ ጭስ፣ እሳት እና ድምፅ ነበረው
አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET 302 ቦይንግ 737 – 800 – ማክስ በደረሰበት የመከስከስ አደጋ 149 መንገደኞችና 8 የበረራ ሠራተኞች በድምሩ 157 ሰዎች ህይወት መጥፋት ተከትሎ መሪዎችና ልዩ ልዩ ተቋማት ኀዘናቸውን ገለጹ፡፡ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በበኩላቸው የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንና ውጤቱም ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡
አውሮፕላኑ የተከሰ ከሰው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በቢሾፍቱና ሞጆ ከተሞች መካከል ኤጀሬ በሚባል ሥፍራ ነው፡፡ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅዘውዴ አውሮፕላኑ አደጋ አጋጥሞት የመከስከሱን ዜና የሰሙት በከፍተኛ ድንጋጤና መሪር ኀዘን መሆኑን ገልፀዋል። ዛሬ ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ትልቅ የኀዘን ቀን ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ፣ በርካታ ዜጎችንና የሌሎች የአየር መንገዱ ደንበኛ የሆኑት መንገደኞች ላይ በደረሰው አደጋ ልባቸው መሰበሩን ገልፀዋል፡፡
በአደጋው ተጎጂ ለሆኑ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብም መጽናናትን ተመኝተዋል። አደጋው በደረሰበት ቦታ ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም በደረሰው አደጋ በራሳቸው፣ በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም ልባዊ ኀዘናቸውን ገልፀዋል።
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንም በደረሰውአደጋ ኀዘናቸውን በመግለፅ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች ቤተሰቦች እና ለመላው ኢትዮጵያውያ መፅናናትን ተመኝተዋል። የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳላሕ በበኩላቸው አደጋውን በከፍተኛ ድንጋጤ መስማታቸውን ጠቁመው፣ በደረ ሰው አደጋ የተሰማቸውን ኀዘን ገልፀዋል፡፡
ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦችም መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡ የዘጠኙ ክልሎች መንግሥታት እና የሁለት የከተማ አስተዳደሮች፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት፣ እና በውጭ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች፣ በኢትዮጵያ የአ ሜሪካ ኤምባሲና የአውሮፓ ህብረትም ኀዘናቸውን ገልፀዋል፡፡
የቦይንግ ኩባንያ በበኩሉ ኀዘኑን ገልጾ፣ የአውሮፕላን አደጋው መን ስኤ ለማጣራት የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታው ቋል፡፡ በሚቀርብለት ጥያቄ መሰረ ትም የአሜሪካን ብሄራዊ ትራን ስፖርት የደህንነት ቦርድ አቅጣጫን ተከትሎ ለኢትዮጵያ አየር መን ገድ የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋ ጀቱን ነው ያስታወቀው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም በበኩላቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ጠቁ መው፣ ውጤቱንም ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አመልክተዋል፡፡አቶ ተወልደ እንዳሉት አውሮ ፕላኑ ከቦይንግ ኩባንያ ከተገዛ ገና አራት ወሩ መሆኑን ጠቁመው፣ ቀደም ሲል ምንም ዓይነት ቸግር እንዳልነበረበት ገልጸዋል፡፡
አውሮፕ ላኑም ባለፈው ጥር 27 ቀን 2011 ዓ.ም ምርመራ ተደርጎለት እንደነበርም አስታው ሰዋል፡፡ በአውሮፕላኑ ላይ 32 ኬንያውያን፣ 18 ካናዳውያን፣ 9 ኢትዮጵያውያን መንገደኞችና 8 የበረራ ሠራተኞች፣ 8 ጋናውያን፣ 8 ጣልያውያን፣ 8 ቻይናውያን፣ 8 አሜሪካውያን፣ 7 እንግሊዛ ውያን፣ 7 ፈረንሳውያን፣ 6 ግብፃውያን ሲሆኑ፣ 5 ጀርመናውያን፣ 4 ህንዳውያን፣ 4 የስሎቫኪያ ዜጎች፣ 3 የኦስትሪያ ዜጎች፣ 3 ስዊድናውያን፣ 3 የራሻውያን፣ 2 የሞሮኮ ዜጎች፣ 2 ስፔናውያን፣ 2 ፖላንዳውያን፣ 2 እስራኤላውያን፣ 1 የቤልጄ ማዊ፣ 1 ኢንዶኔዥያዊ፣ 1 ኡጋንዳዊ፣ 1 የመናዊ፣ 1 ሱዳናዊ፣ 1 ሰርቢያዊ፣ 1 ቶጓዊ፣ 1 ሞዛንቢካዊ ዜጋ፣ 1 ሩዋንዳዊ፣ 1 ሶማሊያዊ፣ 1 ኖርዌያዊ፣ 1 የጅቡቲ ዜጋ፣ 1 አየርላንዳዊ እና 1 የሳኡዲ ዜጋ እንዲሁም 1 የተባበሩት መንግሥታት ፓስፖርት የያዙ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
አዲስ ዘመን በአደጋው ስፍራ ተገኝቶ ያነ ጋገራቸው የዓይን እማኞች እንደገለጹት፣ አውሮ ፕላኑ አየር ላይ እያለ ጭስና የተወሰነ እሳት እንዲሁም ከፍተኛ ድምጽ ነበረው፡፡በአፍንጫው ወደ መሬት በመከስከስ ጉድጓድ ቆፍሯል፡፡ ከአውሮፕላኑ ከፍተኛ ጭስ ይወጣ ስለነበር ቀርቦ እርዳታ ለማድረግ አስቸጋሪ ነበር ያሉት የአይን እማኞቹ፣ጭሱ እንደቀነሰ ግን የሰው አካል/አጥንት፣ አንጀት…/ ማየታቸውን ገልፀ ዋል፡፡ የሞቱት ሰዎች አስከሬን ለማግኘት ፍለጋ መጀመሩን እንዲሁም የአውሮፕላኑን ስብርባሪ አካላት እየተሰበሰቡ መሆኑንም በስፍራው የተገ ኘው ሪፖርተራችን አጎናፍር ገዛኸኝ ዘግቧል፡፡
አዲስ ዘመን መጋቢት 2/2011
በጋዜጣው ሪፖርተሮች