አዲስ አበባ፡- በአገሪቱ የሚስተዋለው ሁለንተናዊ ለውጥና ቀጣይ ምዕራፎች በመቻቻልና በመረዳዳት ላይ ብሎም ስለ ቀጣይ መልካም ነገሮችን በማስቀደም መጓዝ እንዳለበት የሚያስገነዝብ ‹‹ኢትዮ ጵያ ታመስግን›› በሚል መሪ ሃሳብ የምስጋና መርሐ ግብር ሊካሄድ ነው፡፡ ከመርሐ ግብሩ አዘጋጆች መካከልአቶ ባህሩ በቀለ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል እንደገለፁት፤ በአገሪቱ የሚስተዋለው ለውጥ እና አጠቃላይ እንቅ ስቃሴ ከቀረው ይልቅ እየተደረገ ያለው ትልቅ ትኩረት ስቧል፡፡
ይህ በመሆኑም ከወቀሳና ትችት ባለፈ ማመስገንና ከመጥፎ አተያዮች በመውጣት መልካሙን ማበረ ታታ ተገቢ ነው፡፡ የምስጋና መርሐ ግብር መጋቢት 21 ቀን 2011 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የሚዘጋጅ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም 15ሺ እስከ 20ሺ ሰዎች የሚሳተፉ ይሆናል፡፡ በመርሐ ግብሩ የእስልምና፣ ክርስትና እና የሌሎች እምነት ተከታዮች፣ አባ ገዳዎችና ከፍተኛ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ሌላኛው የመርሐ ግብሩ አዘጋጆች አቶ ሳሙኤል ዘገየ በበኩላቸው፤ ዕለቱ ከምስጋና በዘለለ ኢትዮጵያ የጀመረችው ለውጥ ለማፋጠን የሚያግዙ ተግባራትትኩረት ይሰጣቸዋል፤ ድጋፍም ያስፈልገዋል ነው ያሉት፡፡ ለአብነትም የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የጎዳና ተዳዳሪዎችን በማንሳት የተቃና ሕይወት እንዲኖራቸው በማሰብ የጀመረውን ፕሮጀክት ለመደገፍ የሚያስችል ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡ እስካሁን ባለው ሂደ ትም ለመርሐ ግብሩ መሳካት የከተማ መስተዳድሩ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
አዲስ ዘመን ቅዳሜ የካቲት 30/2011
በክፍለዮሐንስ አንበርብር