የኑሮ ሩጫና የመሻሻል ጉዞ እያደር አቀበት እየሆነ ነው። ሁሉም በየመስኩ እለታዊ የሆድን ጥያቄ ከመመለስ ጀምሮ በነገ ተስፋ ውስጥ የሚያጠራቅመውን ስንቅ ለመሙላት ይዳክራል። ሀብታም ድሃ፤ ወንድ ሴት አይልም፤ ሁሉም ወዲያ ወዲህ ይላል። እርሷም አለች፤ እርሷ የራሷን፣ የልጆቿን፣ የቤተሰቧን ነገ ተሸክማ፤ ያላትን ሸጣ የተሻለ ቀን ልትገዛ ከጎዳናው ሯጭ መካከል የምትገኝ። እርሷ፤ በመንገዱ ያየኋት ሴት። ወይዘሮ ገነት ግርማ አንዷ ናት።
የረር በር አካባቢ ከአንድ ግዙፍ ህንጻ አጥር በአንዱ ጥግ ሰማያዊ ሸራ ወጥራ ማልዳ ማጸዳዳት ትጀምራለች፤ አጸዳድታ ሲኒዋን አቀራርባ፣ ቄጠማዋን ጎዝጉዛ «ኑ ቡና ጠጡ» ትላለች። ያገኘኋት ጊዜ ነፍሰጡር ነበረች፤ የመጀመሪያውን የስድስት ዓመት ልጇን ተከትሎ መጣሁ እያለ ያለው ሁለተኛ ልጅ በማህጸኗ አካል ነስቷል። ያደሩ ሲኒዎችን እያጣጠበችና ቄጤማ ከተነጠፈለት ረከቦት እያኖረቻቸው እንዲህ አወጋችኝ። ወደ ቡና ማፍላት ሥራ የገባችው ሌላ ውጤታማ የሚያደርግ ሥራ ማግኘት ስላልቻለች ነው። ለምን? መነሻ የሚሆን በቂ ገንዘብ በእጇ ስለሌለ። ይህን ሥራ ከመጀመሯ በፊት ግን የጽዳት ሥራም ሠርታለች።
እንደውም በ1993ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ከትውልድ ስፍራዋ ሰላሌ ወደ አዲስ አበባ ስታቀና፤ ሰው ቤት በመሥራት ነው የጀመረችው። ከዛም በኋላ የጽዳት ሥራውን በያገኘችበት ስታቀላጥፍ ቆየችና ወደ ቡና ማፍላቱ ደግሞ ገባች። ክረምት ሲሆን ቀን ቡና አፍልታ ማታ ላይ ደግሞ በቆሎ እየጠበሰች ታቀርባለች። አንድ እርምጃ ወደፊት ለመራመድም አትታክትም፤ ብርቱ ናት። የወደፊት ሃሳቧን ጠይቄአት ነበር፤ «ወደፊት እግዚአብሔር ያውቃል፤ ምንም ተስፋ አድርጌ የምጠብቀው ነገር የለም» አለችኝ። ለውጧ ቀስ እያለም ቢሆን ለተመልካች በግልጽ የሚታይ ቢሆንም ለምታስበው ሥራ መነሻ ገንዘብ እስካላገኘች ድረስ ለእርሷ ጎልቶ አልታያትም። የንግድ ሥራዋን ከእለት ኑሮ መደጎሚያ ባለፈ አታየውም።
ማልዳ ወጥታ ሲመሽ ትገባለች፤ በቀኑ የሚያልፍ የሚያገድመው «ገኒ እንዴት አደርሽ?» ይላታል፤ በሙሉ ፈገግታ አላፊ አግዳሚውን፤ ደራሽ ሂያጁን ታስተናግዳለች። ጎዳናው እንደ ገነት ባሉ፤ ከኑሮ ጋር ትግል በገጠሙ ሰዎች የተሞላ ነው። አለፍ ስትሉ ቄጠማ ይዛ የተቀመጠች፣ ደግሞ በመደብ ጥቂት ድንችናሽንኩርት፣ ሎሚና ቃሪያ፣ ሰላጣና ጎመን ይዛ የምትገኝ አለች። እንዲህ ባለ እጅግ አነስተኛ ገቢ ባለው ሥራ ኑሮ እንዴት ይገፋል? ያውም ከተማ መሃል? ሌላ ጥያቄ ነው።
ወዲህ ግን እነዚህ ሴቶች ሥራ ከመሥራትና የየእለት ጉርስን ከመሸፈን፤ ልጆች ያሏቸውም ልጆቻቸውም ከማስተማር፤ ቤተሰብ የሚጦሩትም ከመጦር አልተገደቡም። ከትልልቅ ገበያ ሄዶ የመግዛት አቅም ላለው ሳይሆን ለማይችለው እነዚህ ሴቶች አሉ። ማሪያ ሚኒቲ የተባለች በአሜሪካ ኮክስ ዩኒቨርስቲ መምህርት እንዲሁም ዊማ ናዉድ የተባለ የጥናት ባለሙያ በጋራ ያዘጋጁት አንድ ጥናት አለ፤ ይህም በአዳጊ አገራት ያለውን የሴቶችን የንግድ ሥራ ፈጠራና ለውጥ የሚያስቃኝ ነው። ታድያ በዚህ ጥናት መሰረት ሴት አዲስ የንግድ ሃሳብ ያላቸው ሴቶች በብዛት የሚገኙት አድገዋል በተባሉ አገራት አይደለም። ይልቁንም ታዳጊ በተባሉና ገና በድህነት ውስጥ ባሉ አገራት ነው። እንደ ገነት ያሉ በርካታ ሴቶች ለተሻለ ኑሮ የተሻለ አማራጭ ፍለጋ ሲሉ አዳዲስ የሥራ ሃሳቦችን ያመነጫሉ።
ጥናቱ የሚለው እንዲህ ነው፤ በአዳጊ አገር ወይም በአዳጊ ኢኮኖሚ ውስጥ ያሉ ሴቶች ብዙ ችግር ያጋጥማቸዋል። አንዱ ችግር መደበኛ በሚባለው አሠራር መሰረት ተቀጥሮ ለመሥራት ወይም በመደበኛ የቅጥር ሂደት ውስጥ ለማለፍ ብዙ መሰናክሎች ስላሉባቸው ነው። እዚህ ላይ በአዳጊ አገር ላይ እንደመገኘታችን ለዚህ ብዙ ማሳያ መጥቀስ ስለምንችል እናቆየው። ታድያ እነዚህ ሴቶች ሥራ የማያገኙ ከሆነ የራሳቸውን ሥራ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው። እናም በአዳጊ አገራት ላይ ይህ የሥራ ፈጠራ ከሥራ አጥነት እንዲሁም ከድህነት ማምለጫ መንገድ ሆነ ማለት ነው።
እዚህ ላይ ጥናቱ በማሳያነት የሚያነሳው በላቲን አሜሪካና ካሪብያን ያሉ ሴት የሥራ ፈጣሪዎችን ነው። እነዚህ ሴቶች በየጊዜው በግል ጥረታቸው አዳዲስ የንግድ ሀሳቦችን ያቀርባሉ፤ ያለምንም ማበረታቻና ተጨማሪ እድል ሥራውንም ይዘው ይቆያሉ። ጥናቱ ያክላል፤ በእነዚህ አገራት የሚገኙ ሴቶች በራሳቸው አብዝተው የሚተማመኑና ችሎታቸውን የማይጠራጠሩ ናቸው። እንደነገነት ቡናቸው ጣፋጭ ስለመሆኑ እርግጠኛ የሆኑ፣ የሚሠሩት ሹሩባ እንደሚያምር የማይጠራጠሩ፣ የሚያጥቡት ልብስ ንጹህ እንደሚሆን የሚያረጋግጡ፣ እየተንቀሳቀሱ የሚሠሩት የድግስ ወጥ እና የሚጋግሩት እንጀራ «እጅሽን ለአምባር» የሚያስብል ስለመሆኑ እርግጠኛ የሆኑ ናቸው። በአዳጊ አገር ያሉና ዝቅተኛ ገቢ አላቸው የተባሉ እነዚህ ጥናቱ የሚጠቅሳቸው ሴቶች፤ የተሻለ ገቢ አላቸው ከሚባሉት ጋር ሲነጻጸሩ ውድቀትን የማይፈሩም ሆነው ተገኝተዋል።
ጥናቱ የእነዚህን ሴቶች ጥንካሬ ያጎላል። ታድያ ምንም እንኳ ብዙ አዳዲስ የንግድ ሥራዎችና ሃሳቦች በሴቶች የሚወጠን ቢሆንም፤ በዓለም አቀፍ ደረጃም ጭምር በሴቶች ስር የሚገኙ ግዙፍ የንግድ ሥራዎች ግን በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። ለዚህ ምክንያት ሆኖ በጥናቱ የቀረበው፤ ይልቁንም በታዳጊ አገር ሴቶች ትንሽ የሚመስል የንግድ ሥራ ፈጠራቸውን ለማሳደግና በትልቁ ተደራሽ ለመሆን ጥረት አለማድረጋቸው ነው። እነዚህ የንግድ ሥራዎች እድገታቸው እጅግ አዝጋሚ ነው። አዲስ የንግድ ሥራ ከሚጀምሩ ወንዶች ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የበለጠ ይወርዳል። ለዚህ መንስኤ የሚሆኑ ውስጣዊ ያልሆኑ ተጽእኖዎች መኖራቸውን ሳንዘነጋ፤ ጥናቱ አንዱ መንስኤ ያለው ራሱን የድህነቱን ነገር ነው። በአዳጊ አገሮች የሚገኙ ሴቶች ንግድ ሥራ ላይ የሚሰማሩትም ሆነ አዳዲስ የንግድ ሥራ ሃሳቦችን የሚያመነጩት፤ በንግዱ ዘርፍ ለማደግና ስኬታማ ለመሆን ሳይሆን የእለት ኑሮን ለመግፋትና ለመኖር ነው። ይህ ደግሞ ምርጥና አዲስ የንግድ ሥራ ሃሳብ ቢኖራቸውም ሳያሳድጉት ቀርተው በጓዳ እንዲቀር ይሆናል።
እንደው ከእጅ ሥራ ወይም ጥልፍ ጀምሮ በሙያቸው አቻ የማይገኝላቸው ሴቶች አሉ፤ ይህን ችሎታ አስፍቶና ትልቅ ቢዝነስ ማድረጉ ላይ ታድያ ቅስቀሳና ንቅናቄ እንደሚያስፈልግ ግልጽ ነው። ስለንግድ ሥራ ይልቁንም በአፍሪካ ስላለው የሴቶች የንግድ እንቅስቃሴ የሚያነሳ «Doing Business: Women in Africa» የተሰኘ መጽሔት የተለያዩ የአፍሪካ አገራትን እያነሳ ከጥቂት ተነስተው ወደ ትልቅ ደረጃ የደረሱ ነጋዴዎችን አቅርቧል።
ሩዋንዳ በመጽሔቱ ከተጠቀሱ አገራት መካከል ናት። እንደምናውቀው ሩዋንዳ በጦርነት ሰበብ ልጆቿ እርስ በእርስ ተበላልተውባታል። ታድያ ይህ በሆነ ጊዜ በአገሪቱ በብዛት ቀርተው የነበሩትና ከሕዝቡ 70 በመቶ በላይ ሴቶች ነበሩ። ወደዱም ጠሉ እንደ ቤተሰብም ሆነ እንደ አገር ብዙ ኃላፊነት ተጭኖባቸው ነበር ማለት ነው። ታድያ በአገሩ የነበረውን የእጅ ሥራ ጥበብ ወደ ንግድ የሚለውጡ ሴቶች ተገኙ። እነርሱም የሚያዘጋጁት ቅርጫቶችን ነበር። ይህ የእጅ ሥራቸው በጦርነት ተደቁሳ ከተጎሳቆለችው ሩዋንዳ ወጥቶ ዘናጭ የሆኑት የአሜሪካ ሱቆች ውስጥ ተገኘ። ስኬት በስኬት ላይ እየተደራረበም ዓለም አቀፍ እውቅናን ተጎናጸፉ። ይህን የሰሩት እህትማማቾቹ ጃኔት እና ጆይ ነበሩ።
በአገራችን የ«ሶል ሬብልስ» መሥራች የሆነችውን ቤተልሔም ጥላሁን አንዘነጋም። በጥቅሉ የንግድ ሥራ ፈጠራን ከእለት ኑሮ መግፊያነት ባለፈ ትልቅ ድርጅት ለማድረስ ማሰብ እንደሚያስፈልግ ግልጽ ነው። እንደ ገነት ያሉ በየእለት በመንገድና በጎዳናው የምናያቸው ሴቶች፤ አብዛኞቹ ግን ከእለት ጉርስና ከሳምንት ወይም ከወር ገቢ ባለፈ፤ አቅማቸውን፣ ሙያቸውንና ችሎታቸውን ካሉበት ለላቀ ዓላማና ርዕይ ሲጠቀሙበት አናይም። ቄጠማ የምትሸጥ፣ «ሳንቲም ሳንቲም» እያለች የምትዞር፣ በፔርሙዝ ሻይ ይዛ በፌስታል ጮርናቄ ቋጥራ እርሷን ሸጣ ለመግባት ቁርስ የሚበላውን የምትጠብቅ፣ በመደብ ያስቀመጠችው ድንችና ቲማቲም እንዳይበላሸ ቀኑን ሙሉ ዝንብ እያባረረች ሸጣ መጨረስን የምትናፍቅ፤ ያየኋት ሴት ትግሏ የዛሬን ኑሮ ከማሸነፍ ነው። እንግዲህ የሴቶችን ቀን ያለና ሴቶችን ልደግፍ የሚል ይህን ርዕይ ለዚህች ሴት ከማሰነቅ የላቀ ውለታ ሊሠራ አይችልም።
አዲስ ዘመን የካቲት 29/2011
በሊድያ ተስፋዬ
молитва при нарушении психики кукла оберег пеленашка для чего сонник пьющий
отец
приснилось доить козу нумерология документов
рассчитать онлайн
камені за знаками зодіаку
фотографії богородичне правило з молитвами завантажити
дія магії на людину влюбчив ли козерог
еркебулан кумаров – аппак койлек скачать, скачать песню аппак койлек аппак полная версия терең көл қиын есеп, терең көл сөйлем құрау инбридинг уикипедия, өсімдіктерді сұрыптау азан
шақырып ат қою сөзінің мағынасы, азан шақырып ат қою на русском
farmaci da banco in Guadalupa Epifarma Namen vrije verkoop van medicijnen in België
колёса ваз 21099, ваз 21099 цена в
салоне чехлы для авто, чехлы на
машину алматы цены пәкістан мен үндістан арасындағы қақтығыстарын сипаттаңыз, пәкістан мен үндістан қысқа мерзімді бесик тойга арналган тилек, бесік жырында
айтылатын тілек сөздер
физическая работа для дома гринвей работа на дому
отзывы сотрудников ищу работу сиделка на дому подработка в интернете переводами