ሆዳምነት ከሰውነት ይነጥላል።የጥጋብ ጥግ አቅልን አስቶ አዙሮ ይደፋል።ማመዛዘን፤ የድርጊትን መጨረሻ ቀድሞ ተገንዝቦ ራስን ማትረፍ ከክፉ መጠበቅ ቀርቶ፤ የዕለትን ውሎ ስለማደር ማሰብ እስከማይቻልበት ደረጃ አዕምሮ ከተደፈነ ሰውነት ቀረ ማለት ነው።ሰውነት ሲጎድል ደግሞ ወደ እንስሳነት ያወርዳል።እንስሳትም ልዩነት አላቸው።የወረደ የተዋረደ እንስሳ መሆን ላይ ይደረሳል።
ለሰው ልጆች ክብርን መጠበቅ እና ነውር አለመፈፀም ግዴታ ሊሆን ይገባል ።ራስን እና ሌሎች ሰዎችን ማክበር ቀርቶ ወደ ተራ እንስሳነት መቀየር ከመጣ ደግሞ የተሻለ እንስሳ መሆን ይቻላል።መቼም እንስሳት ተራ ከተወረደ አንበሳ መሆን መልካም ነው።አንበሳነት ጀግንነት ሁሉን አንበርካኪነት ነው።
ጀግና አይልከሰከስም፤ክብሩን አይጥልም።አንበሳም ቢሆን ያው ነው።መንጋውን በጥንቃቄ ይጠብቃል፤ ቁጡ እና ሃይለኛ ቢሆንም ገራም እና ታማኝ ነው።ሲጠግብ የሚያንኮራፋው በዝግታ ነው፤ ተጫዋችነቱንም ዓለም ይመሰክርለታል።እናም ኢትዮጵያውያን በአብዛኛው በአንበሳ ይመሰላሉ። አንበሳ ያሰኛቸው ጀግንነታቸው ነው፡፡ ‹‹የእናት ሆድ ዥንጉርጉር›› እንዲሉ ሆኖ አሁን ላይ ከአንበሳነት ይልቅ በአይጥ ሊመሰሉ የሚገባቸው አስቀያሚዎች ብቅ ብለዋል።አይጥ ትንሽ ፍጥረት ናት።አጥፊነቷ ግን በእጅጉ ይከፋል፡፡በዘመናችን በእርሷ ለመመሰል የተዘጋጁ ብዙ ናቸው።
አይጥ ተግባሯ ከነመልኳ አስቀያሚ ነው።አንዳንዶች ሙሉ ማንነታቸው በእርሷ ውስጥ ሊመሰል የሚችሉ ሆነው እየታዩ ነው።ትንሽ ሆነው ኢትዮጵያን ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱ አይጦች፡፡እነዚህ ክፉ አይጦች ዛሬ መውጫ አጥተዋል። እንግዲህ ሰው ወደ አይጥነት ወርዶ በሁሉም የምትጠላዋ አይጥ ተራ ላይ ደርሶ ኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ የተሳሰሩበትን ገመድ ለመበጣጠስ ከተነሳ አይጥ ቢባል አይደንቅም።እናም አይጦች ኢትዮጵያውያን የተሳሰሩበትን ገመድ በገጠጠ ጥርሳቸው እያኘኩ ለመበጣጠስ ሙሉ አቅማቸውን በመጠቀም ላይ ናቸው።
ነገር ግን አይጦቹ የመተሳሰሪያ ገመዱን ለመበጣጠስ ቢሞክሩም ኢትዮጵያውያን ላይለያዩ ተጣብቀዋል።አይጦች እንደውም ገመዱን በጥርሳቸው እየነከሱ ጥርሳቸውን ሲያደክሙ እና ራሳቸውን ሲያዝሉ ኢትዮጵያውያን ግን ከምንጊዜውም በላይ ጠንክረው ቆመዋል። ያው አይጦች በገጠጡ ጥርሶቻቸው የገዛ ከንፈራቸውን የሚወጉ አስቀያሚ ፍጥረቶች መሆናቸው ዕሙን ነው።እና አረመኔዎቹም ከሰውነት ተራ ወርደው አይጥ ሆነው የገዛ ወገናቸውን እየወጉ ዕድሜያቸውን ለመግፋት ሞክረዋል፡፡
በእነሱ ድርጊት በመረገም ‹‹አይጦች›› ከማለት ውጪ ምርጫ የለንም። አይጥ የሰው የሆነውን ነገር በሙሉ በጥርሷ እየወጋች ታበላሻለች።በልታ ብትጠግብም በገጠጡ ጥርሶቿ በውድ ዋጋ የተገዛ ልብስን እያኘከች ከማበላሸት አትቦዝንም፡ ፡በየቀኑም ለማጥፋት አትደክምም። ከሰው ተራ ወርደው አይጥ ጎራ የተቀላቀሉት አረመኔ ፍጥረታትም በልተው፣ ጠጥተው፣ ዘርፈው እና አግዘው፣ ውድ የሕዝብ መገልገያዎችን አፈራርሰው እና አቃጥለው የአይጥ ባህሪ መላበሳቸውን አሳይተዋል።
በሃይለኛ የእብሪት ስካር ናውዘው ነፍስና ስጋቸውን አዋርደው፤ ከህፃን እስከ መነኩሴ አሮጊት ስሜታቸው ታዞላቸው ለመድፈር መብቃታቸው ሲታወስ በእርግጥ እነርሱን አይጥ ተራ ላይ መመደብ ራሱ ሊገልፃቸው አይችል ይሆናል።ይህ ስጋን ብቻ ሳይሆን ነፍስን የሚያረክስ ተግባር ደስታን ሊሰጥ የሚችለው ሳይጣን ቀመስ
ለሆነ እንደአይጥ አይነት ፍጥረት እንጂ መቼም ቢሆን የታማኝነት እና የእውነት ፤ የጀግንነት እና የአመዛዛኝነት ህሊና የተሰጠው የሰው ልጅ ድርጊቱን ሊፈፅም ቀርቶ ሊያስብ ይችላል ብሎ መገመት ያስቸግራል።ኧረ! እንደው እንኳን ሰው የትኛውም እንስሳ አይጥም ብትሆን ይህን ተግባር ሳትፀየፈው አትቀርም።
በእርግጥም ይህ ተግባር ከእንስሳትም በታች የመዝቀጥ ምልክት በመሆኑ ጀግንነትን ማድነቅ መሠልጠን ቢሆንም፤ እንዲህ አይነት ግፍ ፈፃሚዎችን መንቀፍ ደግሞ ሥራ ብቻ ሳይሆን ፅድቅ ነው።‹‹ጠላው ስላለቀ ጋን አይሰበርም›› አለ ዘፋኙ።አይጦቹ ቢሳካላቸው ጋን ለመስበር ከመትጋትም በላይ አልፈው ሔደዋል።
የበላበትን ወጪት ሰባሪ አልፎ ተርፎ እናት ለዛውም ዕድሜዋ የገፋ አሮጊት እናትን የሚደፍር አይጥን ብዙ ማለት ሳያስፈልግ አይቀርም።ደግነቱ አሁን አይጦቹ በሙሉ ማምለጫ ጉድጓድ አጥተው እየተራወጡ ነው፡፡ በየቦታው እየተቆራረጡ መከበባቸውም የሚያመልጡበት አጥተው በርሃብ እንዲሰቃዩ ሆኗል።ነገሩ ግፍ ይቆያል እንጂ ጊዜውን ጠብቆ ማስከፈሉ አይቀርም። አይጥ ምግብ ሲያገኝ አንዱን ብቻ በልቶ አይረካም።ገጣጣ ጥርሶቹን አስቀድሞ ሁሉንም ይለክፋል።አይጦቹ በአፋር እና በአማራ ክልል ያልለከፉት የለም።ነገሩ ሁለቱን ክልሎች አልን እንጂ የድርጊታቸው ፀያፍነት መላ ኢትዮጵያውያንን ሳይለክፍ አላለፈም።ከሕፃን እስከ አዋቂ ሁሉም አስቀያሚ ድርጊታቸውን ሲሰማ ስሜቱ እየተረበሸ ሁሉም ነገር ቀፎታል።ሕይወቱ ተረብሾበታል።ለነገሩ በእጅ አዙር በሌሎች ክልሎችም ጠባሳ ሳይጥሉ አላለፉም።የእነርሱ ክፉ ተግባር የስንት አትዮጵያውያንን ሕይወት እንዳጠፋ፤ ስንቱ አካሉ እንደጎደለ እና ንብረቱ እንደወደመ ሲታሰብ የአይጥ መንጋዎቹን በሆነ መርዝ መፍጀት ሳይሻል አይቀርም የሚል ሃሳብ በአዕምሮ ውስጥ መመላለሱ የግድ ነው። ነገሩ እውነትም ከዚህ በላይ መላው ኢትዮጵያውያንን እንዳይጎዱ ትልቅ መላ ሳያስፈልግ አይቀርም።በአይጦቹ የተለከፉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጎድተዋል።ኢኮኖሚውን ሲያቦኩት ኖረው አሁን ደግሞ እርሱንም መልከፋቸው መላው ዜጋን ዋጋ እያስከፈለ ይገኛል።
በተጨማሪ በተለይ በአፋር እና በአማራ ክልል በተቋማት ላይ ያስከተሉት ውድመት ጉዳቱ ዕለታዊ ሳይሆን ዓመታትን የተሻገረ እንዲሆን የሚያደርግ ነው።ኢኮኖሚያዊ ሲባል ከሆስፒታሎች፣ ከትምህርት ቤቶች ውድመት ጋር ተያይዞ ከተነሳ ኪሳራው የሕብረተሰብ ጤናን እስከማወክ ይደርሳል።
ከንብረት ውድመት በተጨማሪ በሕዝቡ ስነልቦና ላይ የፈጠሩት ጫና ይጠቀስ ከተባለ ጉዳቱ እጅግ ከፍተኛ ነው።በርካቶች እነዚህን ክፉ አይጦች እርጉም የሰይጣን ግልገሎች ሲሉ የሚጠሯቸውም ለእዚህ ነው።ለሆዳቸው ሲልከሰከሱ አገር አምሰዋል።ከአገር ጠላት ጋር አብረው ፤ የእነርሱ መሳሪያ በሆነው ሕዝባቸው ላይ ቀልደዋል።
የገዛ ወገናቸውን መሳሪያ ተኩሶ ከመግደል አልፈው ከኋላው በማረድ አዕምሮ እንደሌላቸው አሳይተዋል። አይጦቹ የሚፈፅሙት ተግባር እጅግ ቢያሳቅቅም በሚዲያቸው የሚያስተላልፉት ፕሮፖጋንዳ ደግሞ ፈገግ ያሰኛል።በእርግጥም ሰው ስላለመሆናቸው ያረጋግጣል።እንደው መመዘን እና ማመዛዘን ብሎ ነገር የለም? እየተሸነፉ በአደባባይ አሸንፈናል ብለው ይለፍፋሉ።
አልፈው ተርፈው ያፈናቀሉትን እና የገደሉትን ሕዝብ እንወደዋለን ይላሉ።ግፍ ሲሰሩ ቆይተው ግፍ ተሰርቶብናል ብለው የዓይን ምስክር ያሏቸውን ያቀርባሉ።የዓይን ምስክር የተባሉት ደግሞ የአይጥ ምስክር ድንቢጥ እንደሚባለው ያለምንም እፍረት ‹‹መጀመሪያ አባቴን ገደሉት፤ ከዛ እኔን በር ላይ ሲያዩኝ ምሕረት ሞገስ እኔንም ገድለውኝ ሄዱ” ይላል።የትግራይ ቲቪ ያቀረበው የዓይን ምስክር፡፡እንግዲህ ይህ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ከሞተ በኋላ የተነሳ ምስክር ሳይሆን አይቀርም።ወደው አይስቁ! አሉ፡፡ ነገሩ ይህን ሁሉ ግፍ ለመፈፀም የተነሳሱት ፊት የሚሰጣቸው በዝቶ የውጪ ጠላትን ተማምነው እንጂ፤ ትንሽም ቢሆን ባልሞከሩት ነበር።
አሁን ግን አይጦቹ እየፈፀሙት ያለው እውነት ሲታይ ኢትዮጵያን የማፍረስ ፍላጎት አላቸው የሚባሉት የውጭ ጠላቶች ራሳቸው የአይጦቹን ያህል ግፍ በመፈፀም የመላው ኢትዮጵያውያንን አንጀት ያሳርራሉ ብሎ ለመገመት ያዳግታል።አንዳንድ አገራት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ክብር የሚጋፋ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ አይጦቹን ሲገፏቸው፤ እነርሱ ደግሞ ከገፊዎቹ በላይ ይጋፋሉ።
በምድር ላይ ለስጋቸው፣በሰማይም ለነፍሳቸው እጅግ እርኩስ ድርጊት ይሠራሉ። አሁንማ በሮች በሙሉ ላይከፈቱ ተዘግተዋል።መውጫ ይሉት የለም።አሁን አይጦቹ ከግራ ወደቀኝ ከጥግ እስከ ጥግ ወዲያ ወዲህ እያሉ ቢዋከቡም መላ የላቸውም።ዝቅጠታችውን እንደማሳየታቸው ዝቃጭ ተግባራቸውን ደግሞ በእነርሱ ላይ ለመፈፀም ሞራል ባይኖርም፤ እያንዳንዱ ተግባራቸው በትንሹም ቢሆን ዋጋ ያስከፍላቸዋል።አሁን ላሊበላ፣ ጋሸና እና ቆቦ አካባቢዎች ላይ ተቆርጠው ተበታትነዋል።
የተበተኑት ደግሞ መግቢያ ቀዳዳ አጥታ እንደምትዋከብ አይጥ ጉድጓድ መፈለግ አድክሟቸው እየተልፈሰፈሱ መሞታቸውን ቀጥለዋል፡፡ አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግሥት ያሳየው ትዕግስት ፅዋው እየሞላ ነው።የኢትዮጵያ ኃይሎች በቀረው የአይጦች ሐይል ላይ በድሮን የታገዘ የተቀናጀ የማጥቃት ኦፕሬሽንን በደማቅ ድል እያጀበ ቀጥሏል።የጋሸና ተራሮች አሁን በአይጦች ሳይሆን በአንበሶች እጅ ውስጥ ናቸው።ደጋግመው እየተሰባሰቡ አካባቢውን ለመቆጣጠር ቢያስቡም ፈጽሞ አልሆነላቸውም።አሁን በጭንቀት ብዛት እስትንፋሳቸው ልትቋረጥ ደርሳለች።ነገሩ ያ ሁሉ የግፍ እንባ ድርጊታቸውን ፈፅመው ሳይጨርሱ ጎርፍ ሆኖ ባይወስዳቸውም የኢትዮጵያ አምላክ ታክሎበት ዕልፎች ዕድሜያቸው እያጠረ ነው።
‹‹እድሜው የሚያጥር ልጅ አንገቱ ረዥም ነው›› ይባል አይደል? እናም ግፍ ፈፃሚዎቹ ለአካለ መጠን ያልደረሱት ትንንሾቹ አይጦች ደርሰናል ብለው በአዛውንቶች ላይ እጃቸውን በመሰንዘራቸው ዕድሜያቸው እያጠረ ነው።አሁን ከተቆረጡበት ለማምለጥ መሞከር አጉል መላላጥን ከማምጣት ውጪ ትርፍ የለውም።ወደ ጉድጓድ መግቢያ ቀዳዳ ማግኘትም ቀላል አይደለም።ምርጫው አንድ እና አንድ ብቻ ነው።መቼም አልሸነፍም ብሎ ጥይት ጠጥቶ መሞት ጀግንነት ነው።ይህን ጀብድ ደግሞ ለአንበሶቹ ቢተውት መልካም ነው ።ምክንያቱም ይህንን ጀግንነት በፍፁም አይጢት ፈጽሞ ልትሞክረው አትችልም፡፡ አይጥ ተሸነፍኩ ብላ ራሷን አታጠፋም።
ሕይወቷ የሚጠፋው በመርዝና በመርዝ ብቻ ነው።ስለዚህ ለእነሱ መፍትሔው እጅ መስጠት ብቻ ይሆናል ። ያው እኛ እንደፈረደብን እንደነርሱ ጭካኔ አይጥ በጫማ ተቀጥቅጣ እንደምትገደለው፤ አናታቸውን ለመጨፍለቅ ሞራሉ የለንም።ወይንም በወጥመድ ተይዛ ውሃ ውስጥ ተከታ እንደምትንፈራፈረው ሁሉንም ማፈን አንችልም።
እንደፈረደብን አስረን እንቀልባቸዋለን።ስለዚህ አሁን መውጫ ያጡት አይጦች ጥይት ከሚያስጨርሱን፣ አልያም በራሳቸው ድካም ከሚያበዙ በጊዜ እጃቸውን ቢሰጡን ይሻላል።ያለበለዚያ ፍጻሜያቸው በጫማ ተቀጥቅጣ እንደምትሞተው አይጥ ይሆናል።ተቀጥቅጠው፣ተረግጠው፣ ሕይወታቸው ሳይወጣ በቁመናቸው ወደ ተመኙት ሲኦል የሚወርዱበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡በጣም ቅርብ ነው፡፡ በጣም ቅርብ።
ምሕረት ሞገስ
አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 7/2014