አዲስ አበባ፡- የግንዛቤ ማዳበሪያ ፕሮጀክቱ በኢንዱስትሪ የተቀነባበሩ የትራንስ ፋቲ አሲዶችን ከምግብ አቅርቦት ውስጥ ለማስወገድ እገዛ እንደሚ ኖረው የጤና፣ልማትና ፀረ ወባ ማህበር አስታወቀ፡፡
የማህበሩ ምክትል ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ጌትነት በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት ፤የግንዛቤ ማዳበሪያ ፕሮጀክቱ ‹‹ካምፕዬን ፎር ቶባኮ ፍሪ ኪደስ›› ከተሰኘው የአሜሪካ ግብረሰናይ ድርጅት በተገኘ የ50 ሺ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከጥቅምት 2018 ጀምሮ ለስድስት ወራት ተግባራዊ ይሆናል፡፡ የህብረተሰቡን ግንዛቤና እውቀት በማስፋትም በተለይ በኢንዱስትሪ የተቀ ነባበሩ የትራንስ ፋቲ አሲዶችን በኢንዱስትሪ ከተቀነባበሩ ምግቦች ውስጥ ለማስወገድ ያግዛል፡፡
የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም በተመሳሳይ ጉዳዩን ተገንዝበው የህግ ማዕቀፍ እንዲያዘጋጁ ይረዳል፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘላቂ የልማት ግቦች ውስጥ የተቀመጠውን ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ምክንያት የሚከሰትን ያለ ጊዜ የሚከሰት ሞትን እንዲሁም የአለም ጤና ድርጅት በ13ኛው ጉባኤው ትራንስ ፋቲ አሲድን እ.ኤ.አ በ2023 ለመ ቀነስ የያዘውን ግብ ለማሳካት ፕሮጀክቱ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ምክትል ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በትራንስ ፋቲ አሲድ ላይ በርካታ ለውጦችን ያመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የገለፁት ምክትል ዳይሬክተሩ፤ ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ካለፈው ህዳር ወር አንስቶ ባሉት ሶስት ወራት ውስጥ ባለድርሻ አካላትን የመለየትና ትራንስ ፋቲ አሲድ በኢትዮጵያ ያለበትን ደረጃ በሚመለከት ያሉ የፖሊሲ ማዛመጃ ሥራዎች በባለሙያዎች ተሰርተዋል፤ወርክሾፖችን በማዘጋጀት ከባለድርሻ አላት ጋርም ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡
በቀጣይም የመንግሥት አካላት በትራንስ ፋቲ አሲድ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማስፋት ተከታታይነት ያላቸው ውይይቶች እንደሚደረጉ ጠቅሰው፣ የቅስቀሳ መሳሪያዎችን በተለይም ብሮሸሮችና ፖስተሮችን በማዘጋጀት ለህብረተሰቡና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በማሰራጨት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እንደሚሰሩ ምክትል ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡
አቶ አክሊሉ ከፕሮጀክቱ ፍፃሜ በኋላ የህ ብረተሰቡንና የህግ አውጪ አካላትን ግንዛቤ በማሳደግ በኢንዱስትሪ የተቀነባበሩ የትራንስ ፋቲ አሲዶችን ከምግቦች ውስጥ ማስወገድ እንደሚቻል አስታውቀዋል፡፡ የትራንስ ፋቲ አሲድን በመቀነስም ሆነ በማስወገድ ረገድ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ማሳደግ ከትራንስ ፋቲ አሲድ ጋር በተገናኘ የፖሊሲ ርምጃዎችን ለመውሰድ መንደርደሪያ እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤የትራንስ ፋቲ አሲድ በፋብሪካ ተቀነባብረው በሚመረቱ ፈሳሽ የምግብ ዘይቶች ላይ የሃይድሮጅን ንጥረ ነገሮች በመጨመር በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ እንዲደረጉ በማድረግ ሂደት የሚፈጠር ነው፡፡እንደነዚህ ዓይነቶ ቹን ምግቦች በተደጋጋሚ መመገብ ደም ወደ ልብና አንጎል እንዳይዘዋወር በማድረግ ለድንገተኛ የልብ ህመም አልያም ለአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ ምክ ንያት እንደሚሆን የጤና ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
አዲስ ዘመን የካቲት 26/2011
አስናቀ ፀጋዬ