ኢትዮጵያ ከሶስት አመት ብኋላ እአአ በ2021 የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጪ መላክ እንደምትጀምር በማዕድንና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የነዳጅ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አስታወቁ ።የተፈጥሮ ጋዙ በዓመት እስከ አንድ ቢለዮን የአሜሪካ ዶላር ያስገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገለጹ፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ኳንግ ቱትላም በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ የሚያለማው የቻይና ኩባንያ ሲሆን፣ የተፈጥሮ ጋዙ ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ የሚጓጓዘው በቱቦ ይሆናል፡፡
ቱቦ የመዘርጋቱን ስራ ለማካሄድ ከኩባንያው ጋር ስምምነት መፈረሙንና ይህም ስራ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ሚኒስትር ዴኤታው አስታውቀው፣ ጅቡቲ በሚተከል ማቀነባበሪያ ከተዘጋጀ በሁዋላ ወደ ውጪ እንደሚላክም ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ፤የተፈጥሮ ጋዙ ወደ ውጪ በሚላክበት የመጀመሪያ አመት ለኢትዮጵያ እስከ አንድ ቢሊዮን ዶላር ያስገኛል፡፡ወደ ውጪ መላክ ከተጀመረ ከስድስትና ሰባት አመት በሁዋላ ደግሞ ገቢው በየአመጡ እየጨመረ ሄዶ ሰባት ቢሊየን ዶላር ይደርሳል፡፡
ለነዳጅ ማጣሪያው በጅቡቲ የሚገነባው ማቀነባበሪያ በዓመት ሶስት ሚሊዮን ኪዩቢክ ጫማ ጋዝ እንደሚያቀነባብር ዶክተር ኳንግ ተናግረው፣ በድሬዳዋም በዓመት ግማሽ ሚሊዮን ኪዩቢክ ጫማ የሚያመርት የጋዝ ማቀነባበሪያ እንደሚገነባም ገልጸዋል፡፡
ጋዙ ኢትዮጵያና ሞሮኮ በሽርክና (Joint venture) በድሬዳዋ ለሚገነቡት የማዳበሪያ ፋብሪካ እንድ አንድ ግብአት እንደሚያገልግልም ጠቁመዋል፡፡ለእዚህ አቅርቦትም ከኩባንያው ጋር ሰሞኑን የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን ጠቁመዋል ።
እስከ አሁን የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋና ልማቱ እስከ አንድ ሺ ለሚደርሱ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል መፍጠሩንም ገልጸዋል። ልማቱ እየሰፋ ሲሄድ የሠራተኞች ቁጥር እንደሚጨምር ጠቅሰው፣አካባቢው የበለጠ እንደሚለማና በተጓዳኝ ሎሎች የሥራ ዕድሎች እንደሚፈጠሩ አስረድተዋል ።
የተፈጥሮ ጋዝ ክምችቱ ከስምንት እስከ አስር ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ እንደሚደርስም ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል።
ኃይለማርያም ወንድሙ
ከሶስት አመት በሁዋላ የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጪ መላክ ይጀመራል