የኢትዮጵያ ምርቶች በኅብረተሰቡ ዘንድ ምን ያህል ተቀባይነት እንዳላቸው የሚያረጋግጡ ጥናቶች ባይኖሩም ተፈላጊነታቸው አሁንም ዝቅተኛ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ የምጣኔ ሃብት ባለሞያዎችም የምርቶቹ ተፈላጊነት ዝቅተኛነትን ለማከም ለጥራት ትኩረት መስጠትና ማስተዋወቅ ላይ በሚገባ መስራት እንደሚገባ ይጠቁማሉ፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህሩ አቶ ጆንሴ ባኔ የሃገር ውስጥ ምርቶች በሸማቹ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ ጥራታቸውን ማሻሻል እንደሚገባ በመጥቀስ፣ግብርናና የጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ምርቶችን የጥራት ደረጃ በማሻሻል ለገበያ ማቅረብ እንደሚያስፈልግ ይጠቁማሉ፡፡
እሳቸው እንደሚሉት ሸማቹ በውጪ ሀገር ምርቶች ላይ የሚያዘነብል ከመሆኑ አኳያ የተሻሉ ምርቶች በሃገር ውስጥ እንደሚመረቱ ለኅብረተሰቡ የመገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም የማስተዋወቅና የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች በስፋት መሰራት ይኖርባቸዋል፡፡ ሸማቹ ህብረተሰብ ምርቶቹን በስፋት ሊያገኝ የሚችልባቸውን የተለዩ ቦታዎች ማመቻቸትም ያስፈልጋልም ይላሉ፡፡
ጥራትን ከመጨምርና ምርቶችን ከማስተዋወቅ በተጨማሪ የሀገር ውስጥ ምርቶችን ተፈላጊነት ለመጨመር አምራቾች ላይ በስፋት መስራት እንደሚያስፈልግም የሚጠቁሙት አቶ ጆንሴ፤ ለአምራቾች ስልጠናዎችን በመስጠትና ብድር በማመቻቸት የተሻሉ ምርቶችን በብዛትና በጥራት እንዲያመርቱ እገዛ መደረግ እንደሚኖርበት ያስገነዝባሉ፡፡የአነስተኛና ጥቃቅን ዘርፍ ምርቶችን ለተጠቃሚ የሚያቀርቡ ማህበራት ገበያ እንደሌላቸው ተናግረው፣ የማህበራዊ የትስስር ገፆችን በመጠቀም በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር የገበያ ትስስር ሊፈጠረላቸው እንደሚገባ ይጠቁማሉ፡፡
እንደ እሳቸው ማብራሪያ፤ የመንግሥት ግዢዎች ሲካሄዱ ለሃገር ውስጥ ምርቶች ቅድሚያ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ምርቶቹ ገበያ እንዲያገኙ በተለያዩ መድረኮችና ስበሰባዎች ላይ ማስተዋወቅም ያስፈልጋል፡፡ ለሃገር ውስጥ ምርት አምራች .
ጦርነት ለዚህ ትልቅ ምሳሌ እንደሚሆንም ይጠቅሳሉ፡፡ ቻይና ከአሜሪካ ጋር የገባቸው እሰጣ ገባ በጣም የጎዳት በአገር ውስጥ ገበያዋ ላይ ምንም ባለመሥራቷና የወጪ ንግድን ብቻ ታሳቢ አድርጋ በመጓዟ መሆኑን በማመልከትም፣ ይህም በታሪፍና በመሳሰሉት አካባቢ ሲታወክ ንግዱ ወደ መቀዛቀዝ እንዲገባ እንደሚያደርገው ያብራራሉ። የአገር ውስጥ ገበያ በሰፊው መኖሩ ዓለም አቀፍ ገበያው አስተማማኝ በማይሆንበት ጊዜ አምራቾቹን ለመደገፍ እንደሚጠቅምም ያብራራሉ።
እንደ አቶ መሀመድ ማብራሪያ፤ አገር ውስጥ የሚሸጠው የ 1 ኪሎ ግራም ቡና ዋጋ ውጭ ከሚላከው በልጦ ሲገኝ ይህንን የገበያ መርህን ተከትሎ ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ደረጃውን የጠበቀ ቡና የሚያመርቱ አምራቾች የህብረት ሥራ ዩኒየኖችንና በአነስተኛ ማሳ የሚያመርቱ አርሶ አደሮችን በማበረታታት የተሻሻሉ ቴክኖሎጂ ቀመስ ዝርያዎችን በማብዛት ማመጣጠን ይቻላል።
‹‹የአገር ውስጥ የቡና ፍላጎት መጨመር ችግር ሆኗል ሊባል ይችል ይሆናል›› የሚሉት የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር ዶክተር ዘላለም እጅጉ፣ እሳቸው ግን በዚህ እንደማይስማሙ ይገልጻሉ።
‹‹የአገር ውስጥ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከለመድነው የማሽን እንዲሁም በየቤታችን ከምንጠጣው ባሻገር « የጀበና ቡና» እየተባለ በየመንገዱ እየተነገደ ነው›› ሲሉ ጠቅሰው፤ ይህ የፍላጎቱን መጨመር እንደሚያሳይ ነገር ግን እንደሚፈራው የወጪ ንግዱ ስጋት ሊሆን እንደማይችል ያመለክታሉ፡፡ ስጋት ሊሆን የማይችልበት ዋናው ምክንያትም ወደ ውጭ የምንልከው ቡና የተለያዩ ደረጃዎችን ያለፈና በርካታ መስፈርቶችን ያሟላ በመሆኑ ነው በማለትም የአቶ መሀመድን ሀሳብ ያጠናክራሉ።
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለሥልጣን የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አቶ ዳንሳ ዳኒሶ እንደሚሉትም የአገር ውስጥ የቡና ፍላጎት መጨመር እንደ መጥፎ አጋጣሚ የሚታይ አይደለም። አንዳንድ አገሮች የአገር ውስጥ ፍላጎትን ለማሳደግ አቅደው ይሠራሉ፤ በእኛ አገር ግን ይህ ችግር አልገጠመም፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና ከፍተኛ መጠን ያለው ምርትም ለአገር ውስጥ ፍጆታ እየዋለ ነው፤ ይህ በራሱ ችግር ነው ተብሎ የሚወሰድ አይደለም።
አቶ ዳንሳ ፍላጎትን በተገቢው ሁኔታ ለማርካት የሚያስችል በቂ ምርት እንደሌለ ጠቅሰው፣ በዚህ የተነሳም አንዳንድ ጊዜ የወጪ ንግዱን የሚሻማበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ያመለክታሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ከዓለም የቡና ዋጋ በላይ የአገር ውስጥ የቡና ዋጋ ከፍ ይልና ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ጭምር ለውጭ ገበያ የተዘጋጀ ቡና ለአገር ውስጥ ፍጆታ ይውላል ሲሉ ያብራራሉ፡፡ ይህም በተዘዋዋሪም ቢሆን ጫና ማሳደሩ እንደማይቀር ጠቅሰው፣ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በተለይም የቡናን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ለውጭ ገበያ የተመረተ ቡና በአገር ውሥጥ እንዳይሸጥ የቡና ግበይትና ቁጥጥር አዋጅን በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ በማድረግ ይህንን ስጋት ለማስወገድ እየሠራ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ያመለክታሉ።
ኢትዮጵያ በጠቅላላው ከምታመርተው ቡና በአገር ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው ከ45 እስከ 50 በመቶ መሆኑን የባለፉትን 5 ዓመታት መረጃዎችን በመጥቀስ አቶ መሀመድ ይጠቁማሉ፡፡ ይህም የወጪ ንግዱን ግማሽ ያዘ እንደማለት መሆኑን ተናግረው፣ ሁኔታውን እንደ ስጋት ከመመልከት ይልቅ እንደ መልካም አጋጣሚ በመቁጠር ሁለቱንም የሚያቻችል የምርታማነት ሥራን ማከናወን ያስፈልጋል ይላሉ።
ዶክተር ዘላለም የአገር ውስጡንም የወጪ ንግዱንም በእኩሌታ ለማስኬድ ግን ዋናው መፍትሔ የቡናን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ ነው፡፡ ምርታማነት ካደገ ያለምንም ስጋት የአገር ውስጥንም የውጭውንም ፍላጎት ማርካትና ከሁለቱም መስኮች ተጠቃሚ መሆን ያስችላል ባይ ናቸው ፡፡
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ ባለፉት 5 ዓመታት ኢትዮጵያ ካመረተችው ቡና 52 ነጥብ 5 በመቶውን ለውጭ ገበያ፣ 47 ነጥብ 5 በመቶውን ደግሞ ለአገር ውስጥ ፍጆታ አውላለች። ባለፉት አራት ወራት ብቻ 91 ሺ 500 ቶን ቡና በመላክ 331 ነጥብ 2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ፣ በዚህም 76 ሺ 853 ቶን በመላክ 257 ነጥብ 3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ተችሏል።
ኢትዮጵያ ቡናን በብዛት የምታመርተው ለውጭ ምንዛሪ ማስገኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ከጥራት፣ በውጭ ገበያ ካለው የዋጋ መዋዠቅና ከገበያ ተደራሽነት ውስንነት ጋር በተያያዘ የሚፈለገው የውጭ ምንዛሪ እየተገኘም እንዳልሆነም ይታወቃል፡፡ ይህ በሚሆንበት ወቅት ታዲያ የቡና አምራቹን ፣ነጋዴውንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሲታደጋቸው የኖረው በአገር ውስጥ የተፈጠረው ገበያ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ባለሙያዎቹ እንዳሉት የቡና በሀገር ውስጥ ገበያ ላይ በስፋት መገኘት ስጋት ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም፡፡
ግብይቱ የውጭ ግብይቱን እንዳይገዳደር ህገወጥ አሰራርን መቆጣጠር ግን ያስፈልጋል፡፡ የቡና አቅርቦቱ የአገር ውስጥን ፍላጎት ሸፍኖ የውጭውንም ለማርካት የሚያስችል መደላድል ሊፈጠርለት ይገባል፡፡ ይህ ሲሆን የአገር ውስጡ ፍላጎት ስጋት መሆኑ ይቀርና ተስፋ ይሆናል።
አስናቀ ፀጋዬ