ልጆች እንዴት ሰነበታችሁ፤ ሳምንቱ በጥሩ ሁኔታ አለፈ? ጥሩ ነበር እንደምትሉኝ እገምታለሁምክንያቱም እናንተ ጎበዝና ጥንቁቅ ስለሆናችሁ ነገሮችን በአግባቡና በእቅድ ታስሔዳላችሁበዚያ ላይ በደንብ እየተማራችሁ እንደሆነ አምናለሁጥናት ከአሁኑም ጀምራችኋልይህንን ካላደረጋችሁ ጥሩ አይደለምመደራረብ ሲበዛባቸው ብዙ ችግር ይገጥማችኋልከጭንቀት ባለፈ ሰነፍ ተማሪ ያደርጋችኋልእናም ጎበዝ መሆን ካሰባችሁ ጥናታችሁ በየቀኑ መሆን አለበትስለሆነም የተማራችሁትን ወዲያው ማንበብና ማጠናቀቅ አለባችሁ
ልጆች ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት ተረት ሲሆን፤ ጥሩ ግንዛቤ የምትጨብጡበት ነውተረቱን ያገኘሁት የኢትዮጵያ ተረቶች ከሚል ድረገጽ ላይ ሲሆን፤ ርእሱ እናት ጦጢትና አባት ዝንጀሮ ይላልበሉ ልነግራችሁ ነውተዘጋጃችሁ አይደል? አንብቡበአንድ ወቅት አንዲት ጦጣ እና አንድ ዝንጀሮ ተጋብተው ለረጅም ጊዜ አብረው ይኖሩ ነበርአብረው እየኖሩም ሳለ አንድ ጊዜ ክፉ ረሃብ ይገጥማቸውበዚህም መንደራቸውን ለቀው እማ ጦጢት ልጆቿን ሁሉ ይዛ ወደ ሌላ ቦታ ይሰደዳሉ በመንገድ ላይ እየሄዱ ሳለ እማ ጦጢት ላባ ስታገኝ አባት ዝንጀሮ ደግሞየሰላ ቢላዋ አገኘጦጢትም ለአባ ዝንጀሮ እንዲህ አለችው “ተመልከት የእኔ መተጣጠፍ ይችላል:: ያንተ ግን አይችልም፡፡” እሱም “እንለዋወጥ” ብሏት ካሳመነችው በኋላ እሱ ላባውን ሲወስድ እሷ ቢላዋውን ወሰደች፡፡
ከዚያም እየተጓዙ ሳለ በመንገዳቸው ላይ አንድ አህያና አንድ ላም አገኙጦጢት አህያውን ስትወስድ ዝንጀሮው ላሟን ወሰደነገር ግን ጦጣዋ እርቧት ስለነበር አህያውን በላሟ መለወጥ ፈለገችስለዚህ አህያውን ስትደበድበው ከቆዳው ላይ አቧራ ይነሳ ጀመርእሷም “ተመልከት! ይህ አቧራ አህያው ወፍራም መሆኑን ያሳያልያንተ ላም ግን ከሲታ ናትመትተሃትም ማየት ትችላለህ አለችውዝንጀሮውም ላሚቷን ቢመታት ምንም ነገር ስላጣ ወፍራሙን አህያ ሊወስደው ፈለገ“እንለዋወጥ ያንቺን ስጭኝና የእኔን ውሰጂ!” ብሎ ጮሆባት በመጨረሻም በግድ አህያውን ወሰደ ዝንጀሮውና ጦጣዋ መንገዳቸውን ቀጠሉ እየተጓዙም እያለ ሁለት ጎጆዎችን አገኙአንደኛው ጎጆ ዘጠኝ ቀዳዳዎች ያሉት ሲሆን፤ ይህንንም ጦጣዋ ወሰደችውዝንጀሮው ሌላኛውንና ምንም ቀዳዳዎች የሌሉትን በደንብ የተሰራ ጎጆ ወሰደሁለቱም ላማቸውንና አህያቸውን ይዘው ወደየጎጆአቸው ገቡጦጣዋም እንዲህ አለች “አየህ! የእኔ ጎጆ ዘጠኝ ቀዳዳዎች አሉትማታ አያ ጅቦ በአንዱ ቀዳዳ ቢመጣብኝ እንኳ በሌላኛውአመልጣለሁያንተ ጎጆ ግን ምንም ማምለጫ የለውም‹‹ የዚህን ጊዜ “ማታ አያ ጅቦ ቢመጣብኝ ምን አደርጋለሁ?›› አላትእርሷም ‹‹አዎ ትክክል ነህ እንቀያየር›› ስትለው ተስማሙ፤ ተቀያየሩም፡፡
ማታውንም አያ ጅቦ መጥቶ የዝንጀሮ ጎጆ ውስጥ ገባአህያውንም እንደያዘው ዝንጀሮው በአንዱ ቀዳዳ አምልጦ ወጥቶ የጦጣዋ ጎጆ ጣሪያ ላይ ተደበቀዝናቡም በመጣ ጊዜ ዝንጀሮው በጣም ተቸገረበዚህም ጊዜ ጦጣዋ ላሚቷን አርዳ ከልጆቿ ጋር በጎጆዋ ውስጥ እየበላች ነበርበሌላው ጎጆ ውስጥ ደግሞ ጅቦቹ “ሃ!ሃ!ሃ!” ብለው እየሳቁ አህያዋን ይመገባሉበነጋ ጊዜም ጦጣዋ ትጨነቅ ጀመር“አሁን ምን ብዬ ነው ለዝንጀሮው የምነግረው? እንዳታለልኩት ስለሚያውቅ አንገቴ ላይ ቆሞ አንቆ ይገለኛል›› እያለች ታሰላስል ጀመርከዚያም አንድ ሃሳብ መጣላትዝንጀሮው ከጣሪያ ወርዶ እስኪመጣ ድረስ አንድ ድቡልቡል ድንጋይ በእሳት አጋለችየጋለውንም ድንጋይ በስጋ ሸፍና አዘጋጀች፡፡
“የአምላክ ያለህ!” ብላ በመጮህ ልቧን ትደቃ ጀመር“በጣም ታሳዝናለህ! ምግብ አዘጋጅቼልሃለው::” ስትለው አፉን በከፈተ ጊዜ በስጋ የተጠቀለለውን የጋለ ድንጋይ አፉ ውስጥ ስትከትበት ወዲያው ሞተወዲያውም የቀረውን ስጋ ከልጆቿ ጋር ተመግባ የሞተውን ዝንጀሮ አስከሬን ከቤቷ ኋላ ቀበረችውበሶስተኛው ቀንም
ነብር ወደሷ መጣነብሩንም ባየችው ጊዜ በጣም ፈርታ ነበርእሱም እንዲህ አላት “አያ ጦጢት እዚህ አካባቢ ብዙ ፍየሎች ስላሉ ከሁሉ ትልቁን ይዘሽልኝ ነይ!” ብሎ አዘዛትእሷም “አያ ነብር ምንም አያሳስብህ:: በጣም ትልቁን ፍየል አመጣልሃለውነገር ግን ትልቁ ፍየል አንተን ባየ ጊዜ ስለሚሸሽ ልይዘው አልችልምስለዚህ ምን ባደርግ ይሻለኛል? ፊትህን አዙረህ ጀርባህን ብታሳየው ጭራህን ከፍየሉ ጭራ ጋር አስረውና አንተም ፍየሉን በጭራህ እየጎተትክ ወደ ዋሻህ ትመለሳለህ፡፡” አለችው፡፡
ነብሩም በዚህ ተስማማእሷም ወደ ቤቷ ኋላ ይዛው ሄዳ ፊትህን አዙር አለችውና ጭራውን ከሞተው ዝንጀሮ ጭራ ጋር ቋጥራው አሁን በል እሩጥ አለችውነብሩም የሞተውን ዝንጀሮ እየጎተተ ወደ ዋሻው ሄደእዚያም እንደደረሰ ዞር ብሎ ሲያይ ዝንጀሮውን አየየዝንጀሮውም አፍ ተከፍቶና ሰውነቱ አብጦ ነበርነብሩ ባየው ጊዜ ደንግጦ “ምን አይነት ትልቅ እንስሳ ነው?” በማለት ወደ ጫካው ተመልሶ ሲሸሽ ከተራራው ላይ የወዳደቁ ድንጋዮች ደብድበው ገደሉትከዚህም በኋላ ጦጣዋና ልጆቿ በሰላም አብረው መኖር ጀመሩልጆች የዚህ ታሪክ ቁምነገር ለችግሮች እንዴት መፍትሄ ማበጀት እንደሚቻል ማሳየት ነውብልሀተኛ ከሆናችሁ ሁሉንም ችግሮቻችሁን መፍታት ትችላላችሁለዛሬ በዚህ እንሰነባበት ሰላም!
ጽጌረዳ ጫንያለው
አዲስ ዘመን ጥቅምት 14/2014