የሀሰን ናስራላህ ግድያ ፍትሐዊ መሆኑን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተናገሩ

አሜሪካ ሻህራም ፑርሳፊን ለጠቆማት 20 ሚሊዮን ዶላር እንደምትከፍል ገለጸች።

የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ሻህራም ፑርሳፊ የተባለውን ግለሰብ ለጠቆማት 20 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ አስታውቃለች።

ሻህራም ፑርሳፊ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጦር አባል ሲሆን፤ የአሜሪካ ባለስልጣናትን ለመግደል በማሴር ላይ መሆኑ ተገልጿል።

እንደ አሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ማስታወቂያ ከሆነ ሻህራም ፑርሳፊ ዋና ተፈላጊ ሰው ሲሆን፤ በተለይም የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የደህንነት አማካሪ የሆኑት ጆን ቦልተንን ለመግደል የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ተደርሶበታል ተብሏል።

መህዲ ሪዛዪ እና ሻሂን ፑርባክሽ የሚሉ ስሞች እንዳሉትም የሚጠራው ይህ ኢራናዊ ጆን ቦልተንን የሚገድል ሰው በመመልመል እና ተልዕኮውን ለፈጸመ ሰው 300 ሺህ ዶላር እንደሚከፍል እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ እንደተደረሰበት ተገልጿል።

ሻህራም ፑርሳፊ በተለይም በፈረንጆቹ 2021 እና 22 ዓመት ላይ በጡረታ ላይ ያሉት ጆን ቦልተንን ለመግደል የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ ተገኝቷል ተብሏል።

አሜሪካ ይህንን ሰው ያለበትን ያየ ወይም ለጠቆመኝ 20 ሚሊዮን ዶላር ወሮታ እንደምትከፍል አስታውቃለች።

ዋሸንግተን ከዚህ በፊት በተመሳሳይ የሂዝቦላህ ኮማንደር የነበረው እና ከሁለት ሳምንት በፊት በእስራኤል ጥቃት በቤሩት ለተገደለው ኢብራሂም አኪልን ለጠቆመኝ ሰባት ሚሊዮን ዶላር እንደምትከፍል ገልጻ ነበር።

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ ዘመን ሰኞ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You