የሀሰን ናስራላህ ግድያ ፍትሐዊ መሆኑን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተናገሩ፡፡
እስራኤል ባሳለፍነው አርብ ሌሊት በቤሩት በፈጸመችው ጥቃት የሊብኖሱ ሄዝቦላህ መሪ ሼክ ሀሰን ናስራላህን መግደሏ ይታወሳል።
የሄዝቦላህ መሪው ሀሰን ናስራላህ እስራኤል በቤሩት በፈጸመችው ጥቃት መገደላቸውን ባወጣው መግለጫ አረጋገጧል።
በርካታ ሀገራት እና መሪዎች በሀሰን ናስራላህ ግድያ ዙሪያ አስተያየታቸውን እየሰጡ ሲሆን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ግድያው ለዓመታት በንጹሃን ላይ ለደረሱ ጥቃቶች ፍትህ ሲባል የጠፈጸመ ነው ብለውታል፡ ፡
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ሀሰን ናስራላህ አሜሪካዊያንን ጨምሮ እስራኤላዊያን እና ሊባኖሲያዊያን ንጹሃን ዜጎች እንዲገደሉ ምክንያት ነበር ሲሉም ተናግረዋል፡፡
እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት አላት ያሉት ፕሬዝዳንት ባይደን አሜሪካ እስራኤል ራሷን ከሐማስ፣ ሂዝቦላህ እና ሁቲ ጥቃቶች መከላከል የምትችልበት ቁመና እንዲኖራት ወታደራዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡
በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ሁኔታ እንዳይባባስ የአሜሪካ ጦር ዝግጁ እንዲሆን የመከላከያ ሚኒስትራቸውን እንዳዘዙም ፕሬዝዳንት ባይደን ተናግረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በሊባኖስ ያሉ የአሜሪካ ኢምባሲ ሰራተኞች ከቤሩት ያስወጣች ሲሆን አሜሪካዊያን ሀገሪቱን በፍጥነት ለቀው እንዲወጡም አሳስባለች፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የሂዝቢላህ ደጋፊ የሆነችው ኢራን እስራኤል ሀሰን ናስራላህን እንድትገድል ይሁንታ መስጠቷን አስታውቃለች፡፡
የኢራን ፕሬዝዳንት ማስኡድ ፔዜሽኪያን በግድያው ዙሪያ በሰጡት አስተያየት አሜሪካ በሀሰን ናስራላህ ግድያ ከሀላፊነት መሸሽ አትችልም ብለዋል፡፡
በጋዜጣው ሪፖርተር
አዲስ ዘመን ሰኞ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም