በህዝቦች ተሳትፎ እየተገነባ ያለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ለሌሎች
አፍሪካ ሐገራት አስተማሪ መሆኑን ከዙባቤዌ፣ ሞዛምቢክ እና ዴሞክራቲክ ኮንጐ የመጡ ልዑካን ቡድኖች አስታወቁ፡፡
ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በህዝቦች ተሳትፎ መሆኑ የሚያኮራና የሚያስመሰግን መሆኑን ለልምድ ልውውጥ ከዙምባብዌ፣ ሞዛምቢክ እና ዴሞክራቲክ ኮንጐ የመጡት ልዑካኖች አሳውቀዋል፡፡
ከዴሞክራቲክ ኮንጐ የመጡ ሙዙንጉ ዲያከሎ እንዳሉት ከግንባታው ግዙፍነት አንጻር ህዝቡ በዚህ ስራ ግንባታ ድጋፍ ተሳታፊ መሆኑ የባለቤትነት ስሜት የሚፈጥርና አስተማማኝ የፋይናንስ አቅም መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ እዚህ ባየሁት ነገር ለሌሎች አፍሪካ ሃገራት ታላቅ ሃገራዊ ብሮጀክት የህዝቦች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ማሳያ ነው፡፡
የዚምባቤው የሃይልና የልማት ሚኒስቴር የሆኑት ኢ/ር ቤንሰን ኚያራቲ እንዳሉት ይህንን መሰል ታላላቅ ኘሮጀክት በአፍሪካውያን መገንባት እንደማይችል ነበረ የሚታሰበው፡፡ ነገር ግን እዚህ በኢትዮጵያ የተመለከትነው ነገር እጅግ በጣም ተገርሜያለሁ፡፡ አፍሪካውያን ከተባበርን ታላላቅ ኘሮጀክቶችን ለራሳችን አቅም መገንባት እንደምንችል መውሰድ ችያለሁ ብለዋል፡፡
የዛምቢያው የሃይል ሚኒስትር በበኩላቸው እዚህ የመጣነው ኢትዮጵያ የሃይል ማመንጫ ግድቧን እንዴት እየገነባች እንዳለ ለማየትና እኛም ለመገንባት ላሰብነው የሃይል ማመንጫ ግድብ ልምድ ለመውሰድ ሲሆን በተለይ የግንባታው ወጪ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ድጋፍ መሆኑ ለኛ እጅግ በጣም ጠቃሚ ልምድ ነው፡፡ በዚህ ስራ የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ የወሰዱት ቁርጠኛ ተግባር እጅግ በጣም የሚያስደንቅ ነው ብለዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ ከኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመልሰዋል፡፡
መረጃው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህ/ተ/አስተባባሪ ብ/ም/ቤት ፅ/ቤት ነው፡፡